Health Benefits of Lemon – የሎሚ የጤና ጥቅሞች

Health Benefits of Lemon – የሎሚ የጤና ጥቅሞች

ከሎሚ የጤና ጥቅሞች መካከል የጉሮሮ መመረዝን ለማከም፣ የምግብ አለመፈጨትን፣ የሆድ ድርቀትን፣ የጥርስ ችግሮችን፣ እንዲሁም ትኩሳት፣ የውስጥ ደም መፍሰስን፣ የመገጣጠሚያዎች ሪህን፣ ቃጠሎን፣ ውፍረትን፣ የመተንፈሻ አካል ችግሮችን፣ ኮሌራን እንዲሁም ከፍተኛ የሆነ የደም ግፊትን ለማከም የሚረዳ ሲሆን ጸጉርና ቆዳን ለመንከባከብ ይጠቅማል:: ለዘመናትም በመድሀኒትነት ባህርይው የታወቀ ነው፣ ሎሚ የመከላከል አቅምን ለማጠናከር ይረዳል፣ ሆዳችንንም ለማጽዳት ይጠቅመናል፣ እንዲሁም ደምን የሚያጣራ እንደሆነ ይታወቃል::

በተለይ ከሎሚ ጭማቂ ጋር የተያያዙ በርካታ ጥቅሞች አሉ:: የኩላሊት ጠጠርን በማከሙ ይበልጥ ይታወቃል እንዲሁም ደግሞ ስትሮክን ከመቀነስ እና የሰውነት ሙቀትን በመቀነስም ይታወቃል:: እንደ መዝናኛ መጠጥም፣ የሎሚ መጠጥ ተረጋግተን እና ዘና ብለን እንድንቆይ ይረዳናል::

የሎሚ የጤና ጥቅሞች ምክንያትም ያሉት ጠቃሚ ንጥረ ነገሮች ናቸው ከእነዚህም ውስጥ እንደ ቪታሚን ሲ፣ ቪታሚን ቢ6፣ ቪታሚን ኤ፣ ቪታሚን ኢ፣ ፎላቴ፣ ኒያሲን ቲያሚን፣ ሪቦፍላቪን፣ ፓንቶቴኒክ አሲድ፣ ኮፐር፣ ካልሲየም፣ ብረት፣ ማግኒዚየም፣ ፖታሲየም፣ ዚንክ፣ ፎስፈረስ እና ፕሮቲን ይገኛሉ:: ሎሚ በውስጡ ፍላቮኖይድ የሚገኝበት የፍራፍሬ አይነት ነው፣ ይህም አንቲ ኦክሲደንት እና ካንሰርን የመዋጋት ባህርይ ያለው ድብልቅ ነው:: የስኳር በሽታን ለመከላከል፣ ለሆድ ድርቀት፣ ለከፍተኛ ደም ግፊት፣ ለትኩሳት፣ ምግብ አለመፈጨት እንዲሁም ሌሎች ችግሮችን ለመከላከል እና የቆዳ፣ የጸጉር እና የጥርሳችንን ውበት ለማሻሻል ይረዳል:: በአሜሪካን ዩሮሎጂካል ማህበር በተካሄደ ጥናት በጉልህ እንዳስቀመጠው የሌሞንዴ ወይም የሎሚ ጭማቂ የኩላሊት ጠጠር እንዳይፈጠር የመሽኚያ ሲትሬትን በመመስረት እንዲወገድ ያስችለዋል፣ ይህም ክሪስታሎች እንዳይመሰረቱ ይከላከላል::

ሌሞንዴን ለማዘጋጀትም ሰወች የሎሚ ፈሳሽን ከውሀ ጋር በማደባለቅ ይጠቀማሉ:: አብዛኛው ሰውም ሎሚን እንደ የጽዳት ግብዐት ይጠቀሙበታል፣ ምክንያቱም እድፍን በማስወገድ ብቃቱ ነው:: የሎሚ ሽታም ትንኞችን ማባረር ይችላል፣ እንዲሁም የሎሚ ጭማቂ ከ ኦሊቭ ዘይት ጋር በማድረግ መጠቀም የሀሞት ጠጠርን ለማስወገድ ይረዳል:: ሎሚ የታወቀ የመድሀኒትነት ሀይል ያለውና በተለያየ መንገድ ጥቅም ላይ የሚውል ነው:: በሪህ በሽታ መዘክር የሚገኙት ጥናታዊ ዘገባወች እንደሚያመላክቱት፣ ሎሚ ከኢንፍላማቶሪ ፖሊአርቲስ እና አርትሪቲስ መከላከልን የሚያስችለን ነው::

የሎሚ የጤና ጥቅሞች

በርካት የሆኑት የሎሚ የጤና ጥቅሞች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል:

ለምግብ አለመፈጨት እና ድርቀት: የሎሚ ጭማቂ ከምግብ አለመፈጨት እና ከሆድ ድርቀት ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለማዳን ይረዳል:: በምግብዎት ላይ ጥቂት ጠብታ ሎሚ በመጨመር(ተጠንቀቁ፣ ከወተት ጋር አብሮ አይሄድም)፣ እንዲሁም ለምግብ መፈጨት ይረዳል:: ደምን የሚያጠራ እና የሚያጸዳ ወኪል በመሆን የሚተገብር ነው፣ ስለዚህም ከምሳ ወይም ከራት በኋላ ጥሩ የሆነ መጠጥ የሎሚ ሶዳ ነው፣ ይህም በብዙ ቦታወች ዘንድ አዲስ የሎሚ ሶዳ በመባል ይታወቃል:: የአሰራር ዘዴውም፣ የሎሚ ጭማቂ፣ ቀዝቃዛ ውሀ፣ ሶዳ፣ ጨው(የዘወትር ጨው ወይም አሞሌ ጨው) እና ለማጣፈጫ ስኳር ወይም ማር:: እንዲሁም ደግሞ ለጣዕምና የተወሰነ የሚንት ቅጠል ወይም የተወቀጠ የፌንል ዘር መጨመር ያስፈልጋል:: ከበድ ያለ ምሳ ወይም ራት ከተመገባችሁ ይህን መጠጥ ተጠቀሙ::

ትኩሳት: ሎሚ በጉንፋን፣ በኢንፍሉዌንዛ ወይም በትኩሳት የተጠቃን ሰው ለማከም ይችላል:: የሰውነታችንን ላብ በመጨመር ትኩሳቱን ለማጥፋት ይረዳል::

ጥርስን ለመንከባከብ: በአብዛኛው ለጥርስ ክብካቤ ጥቅም ላይ ይውላል:: አዲስ የተቀጠፈን የሎሚ ጭማቂ ህመም በሚሰማን የጥርሳችን ቦታ ብናስቀምጠው፣ ህመሙን ለማስወገድ ይረዳናል:: ጭማቂውንም በድዳችን ላይ ብናሸው የድድ መድማትን ሊያስቆም ይችላል፣ እንዲሁም መጥፎ ሽታወችንና ልዩ ልዩ የድድ በሽታወችን ያስወግድልን ዘንድ ይችላል::

በተጨማሪም፣ በተለምዷዊ ጥርስን የማጽዳት ሂደት ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል:: የጥርስ ሳሙናችንም ከተቀመመበት ነገሮች አንዱ ሎሚ መሆኑን ማስተዋል ይገባል፣ ወይም ጥቂት የሎሚ ጭማቂ በጥርስ ሳሙናችን ላይ መጨመር:: አንዳንዶችም ከሎሚው ጭማቂውን ካስወገዱ በኋላ ጥርሳቸውን በሎሚው የውጨኛ አካል ይፈገፍጋሉ(የውስጠኛው አካል ጥርሳችንን ይነካል):: ግን ተጠንቀቁ፣ ሎሚ በከፍተኛ ደረጃ አሲዳማ ሊሆን ይችላል፣ ስለዚህም አፋችሁን ማቃጠል ከጀመረ፣ በፍጥነት አፋችሁንና ድዳችሁን በውሀ ተጉመጥመጡት::

ጸጉርን ለመንከባከብ: የሎሚ ጭማቂ ጸጉርን ለመንከባከብ በስፋት ጥቅም ላይ የሚውል ነው:: ጭማቂውንም በራስ ቆዳ ላይ በምናደርግበት ጊዜ እንደ ፎረፎር፣ የጸጉር መሳሳት እንዲሁም ሌሎች ከጸጉር እና ከራስ ቆዳ ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለማስወገድ ይረዳናል:: የሎሚ ጭማቂንም በቀጥታ ጸጉር ላይ ብታደርጉት፣ ተፈጥሯዊ የሆነ አንጸባራቂ መልክ ይሰጠዋል::

ቆዳን ለመንከባከብ: የሎሚ ጭማቂ፣ በተፈጥሯዊ መልኩ ከመበስበስ የሚያክም እንዲሁም ሌሎች ከቆዳ ጋር የተያያዙ ችግሮችን ማዳን የሚቻለው ነው:: ጭማቂውም የፀሀይ ቃጠሎን ለመቀነስ የሚደረግ ሲሆን እንዲሁም ንብ ስትነድፈን ህመሙን ለማስታገስ ይረዳል:: ለብጉር እና ለቆዳ መጉረብረብም መፍትሄ ነው:: ለፀረ-ማርጀት መድህንነት የሚያገለግልና የቆዳ መሸብሸብንና መኮማተርን ለማስወገድ የሚረዳ ነው:: የሎሚ ጭማቂን ከ ውሀ እና ከማር ጋር በመቀላቀል መጠጣትም ለቆዳችን ልዩ የሆነ ውበትን የሚያጎናጽፍ ነው እንዲሁም በኮስሞቲክሱ ገበያ ያለመታከት ብታፈላልጉ፣ የሎሚ ጭማቂ በውስጣቸው የሚገኝ አንዳንድ ሳሙናወችን ታገኛላችሁ፣ ግን በቀላሉ የሚገኙ አይደሉም!

ቃጠሎ: በቆዩ የቃጠሎ ለምጥ ቦታወች ላይ የሎሚ ጭማቂን መጠቀም ለምጡን ለመቀነስ ይረዳል፣ እንዲሁም ደግሞ ሎሚ እንደማቀዝቀዣ ጥቅም ላይ ስለሚውል፣ በቆዳ ላይ የሚከሰትን የማቃጠል ስሜት ለማብረድ የሚረዳ ነው::

ውስጣዊ የደም መፍሰስ: መመረዝን የሚከላከልና ደምን ለማርጋት የሚረዳ ባህርይ አለው፣ ስለዚህም ውስጣዊ የደም መፍሰስን ሊያስቆም ይችላል:: በትንሽ የጥጥ ድብልብል ላይም የሎሚ ጭማቂ ጨምራችሁ በአፍንጫችሁ ውስጥ ብታስቀምጡት ነስሩን ሊያስቆምላችሁ ይችላል::

ክብደት ለመቀነስ: የሎሚ ጭማቂን ትንሽ ለብ ካለ ውሀና ማር ጋር ቀላቅሎ የሚጠጣ ሰው ክብደቱን ለመቀነስ ይረዳዋል::

የመተንፈሻ መዛባት: የሎሚ ጭማቂ የመተንፈሻ አካላት ችግሮችንና የመተንፈስ ችግሮችን እንደ አስም ባሉ በሽታወች ለሚሰቃይ ሰው ትንሽ እፎይታል ለመስጠት የሚረዳ ነው:: በከፍተኛ ደረጃም የ ቪታሚን ሲ ምንጭ እና፣ በዘላቂነት የመተንፈሻ አካል ችግሮችን ለማስታገስ የሚረዳ ነው::

ኮሌራ: እንደ ኮሌራ እና ወባ ያሉ በሽታወችንም በሎሚ ጭማቂ ማከም ይቻላል፣ ምክንያቱም የደም ማጥራት ተግባር ስለሚፈጽም ነው::

እግርን ለማፍታታት: ሎሚ በርከት ያሉ የኬሚካል ውህዶችን ያካተተና ነገሮች እንዳይበሰብሱ ወይም እንዳይመረዙ በመከላከሉ እግርን ለማፍታት እንደ አንድ ግብዐት ልንጠቀምበት እንችላለን:: ጥቂት የሎሚ ጭማቂ በሞቀ ውሀ መጨመርና እግርን መዘፍዘፍ በአፋጣኝ ፋታ ለማግኘት ይረዳል እንዲሁም ጡንቻን ያፍታታልናል::

ለሪህ: የሽንት መጠንን በመጨመር ለሪህ እና የመገጣጠሚያ ችግሮችን ሊያስታግስ ይችላል:: ባክቴሪያንና መርዛም ነገሮችን ከሰውነታችን ለማስወገድ ይረዳል::

የደነደነ ቆዳ: የሎሚ ጭማቂ በቆዳችን ላይ የሚገኙ አላስፈላጊ ቅርፊቶችን እንዲሟሙ ያደርጋል፣ ስለዚህም በደነደነው የቆዳችን ክፍል ልንጠቀማችው እንችላለን፣ ማለትም በእግር መዳፋችን እና በእጅ መዳፋችን ላይ ልናደርገው እንችላለን:: በተመሳሳይ ምክንያትም የሎሚ ጭማቂን ከውሀ ጋር መጠጣት የሀሞት ጠጠር ይቀንስ ዘንድ ይረዳል::

ለጉሮሮ መታወክ: ሎሚ ከጉሮሮ ኢንፌክሽን ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለመከላከል ተመራጩ ፍራፍሬ ነው፣ ይህም በታወቀው የፀረ_ባክቴሪያ ባህርይው ነው::

ለከፍተኛ ደም ግፊት: የሎሚ ጭማቂን መጠጣት በልብ ችግር ለሚሰቃዩ ሰወች እፎይታን የሚሰጥ ነው፣ ምክንያቱም በውስጡ ፓታሲየም ይገኛል:: ከፍተኛ የሆነ የደም ግፊትን፣ የጭንቅላት ማዞርን፣ የሆድ ቁርጠትን ይቆጣጠራል፣ ምክንያቱም ለአካላችንም ሆነ ለሰውነታችን የሚያረጋጋ መንፈስን ስለሚያላብሰን ነው:: በብዛትም የአዕምሮ መወጣጠርንና ድብርትን ለመቀነስ ይረዳል::

ሎሚ: ሎሚን ለሚጠቀሙ ሁሉ በተፈጥሮ የተባረከ እንደሆነ እርግጥ ነው:: ለብዙ ከጤና ጋር ለተያያዙ ችግሮች ፍቱን መፍትሄ ነው፣ ምክንያቱም በውስጡ የራሱ የሆነ ከመበስበስና ከመመረዝ የሚከላከል መሆኑና ተፈጥሯዊ መድሀኒትነት ስላለው ነው:: በወባ ጉዳይ ላይ ደግሞ፣ ሎሚ ፈውስ ይሰጣል ማለት አይደለም፣ ግን ህክምናውን ያግዛል ማለት ነው:: ከዚህች አነስተኛና ሀይለኛ የፍራፍሬ አይነት ውጤታማ ጥቅም ለማግኘት፣ ጥሩ ልምድ የሚባለው በቀን ውስጥ የሎሚዋን ሩብ ወይም ግማሿን መጠቀም ሲችሉ ነው::


ethiopian-food-recipes-health-lemon-blog-diet-healthy

The health benefits of lemon include treatment of throat infections, indigestion, constipation, dental problems, and fever, internal bleeding, rheumatism, burns, obesity, respiratory disorders, cholera and high blood pressure, while it also benefits hair and skin care. Known for its therapeutic property since generations, lemon helps to strengthen your immune system, cleanse your stomach, and it is considered a blood purifier.

Lemon juice, especially, has several health benefits associated with it. It is well known as a useful treatment for kidney stones, reducing strokes and lowering body temperature. As a refreshing drink, lemonade helps you to stay calm and cool.

The health benefits of lemons are due to its many nourishing elements like vitamin C, vitamin B6, vitamin A, vitamin E, folate, niacin thiamin, riboflavin, pantothenic acid, copper,  calcium, iron,  magnesium, potassium, zinc, phosphorus and protein. Lemon is a fruit that contains flavonoids, which are composites that contain antioxidant and cancer fighting properties. It helps to prevent diabetes, constipation, high blood pressure, fever, indigestion and many other problems, as well as improving the skin, hair, and teeth. Studies conducted at the American Urological Association highlight the fact that lemonade or lemon juice can eliminate the occurrence of kidney stones by forming urinary citrate, which prevents the formation of crystals.

People use lemons to make lemonade by mixing lemon juice and water. Many people also use lemon as a washing agent, because of its ability to remove stains. The scent of lemon can also repel mosquitoes, while drinking lemon juice with olive oil helps to get rid of gall stones. Lemon is well known for its medicinal power and is used in many different ways. As per the results reported in a study by the Annals of the Rheumatic Diseases, lemon provides protection against inflammatory polyarthritis and arthritis.

Health Benefits of Lemon

Various health benefits of lemon are explained below:

Indigestion and Constipation: Lemon juice helps to cure problems related to indigestion and constipation. Add a few drops of lemon on your dish (take care, it does not go well with milk), and it will aid in digestion. It acts as a blood purifier and a cleansing agent, so a good drink after lunch or dinner is fresh lemon soda, which is also called fresh lime soda in many places. The recipe is lemon juice, cold water, soda, salts (common salt or rock salt) and sugar/honey for sweetness. You can also add some mint leaves or crushed fennel seeds for added flavor. Drink this whenever you have a heavy lunch or dinner.

Fever: Lemon juice can treat a person who is suffering from a cold, flu or fever. It helps to break fevers by increasing perspiration.

Dental Care: It is also frequently used in dental care. If fresh lemon juice is applied on the area of a toothache, it can assist in getting rid of the pain. Massaging the juice on the gums can stop gum bleeding, while eliminating the bad odors that can come from various gum diseases and conditions.

Additionally, it can be used in the regular cleansing of your teeth. Keep your eye out for a toothpaste containing lemon as one of the ingredients, or add a drop of its juice onto your normal toothpaste. Some people also rub their teeth with the outer shell (the inner side touching your teeth) of a lemon after removing the juice. But be careful, lemons are highly acidic, so if your mouth starts burning, rinse your gums and mouth quickly with water.

Hair Care: Lemon juice has proven itself in the treatment of hair care on a wide scale. The juice applied to the scalp can treat problems like dandruff, hair loss and other problems related to the hair and scalp. If  you apply lemon juice directly on the hair, it can give your hair a natural shine.

Skin Care: Lemon juice, being a natural antiseptic medicine, can also cure problems related to the skin. The juice can be applied to reduce the pain of sun burn, and it helps to ease the pain from bee stings as well. It is also good for acne and eczema. It acts as an anti-aging remedy and can remove wrinkles and blackheads. Drinking lemon juice mixed with water and honey brings a healthy glow to the skin, and if you thoroughly search the cosmetic market, you will find some soaps containing lemon juice, but they aren’t too easy to find!

Burns: Use lemon juice on the site of old burns can help fade the scars, and since lemon is a cooling agent, it reduces the burning sensation on the skin when you currently have an irritating burn.

Internal Bleeding: It has antiseptic and coagulant properties, so it can stop internal bleeding. You can apply lemon juice to a small cotton ball and place it inside your nose to stop nose bleeds.

Weight Loss: If a person drinks lemon juice mixed with lukewarm water and honey, it can help reduce body weight.

Respiratory Disorders: Lemon juice assists in relieving respiratory problems and breathing problems, such as its ability to soothe a person suffering from an asthma attack. Being a rich source of vitamin C, it helps in dealing with more long-term respiratory disorders.

Cholera: Diseases like cholera and malaria can be treated with lemon juice, because it acts as a blood purifier.

Foot Relaxation: Lemon is an aromatic and antiseptic agent and is useful in foot relaxation. Add some lemon juice to warm water and dip your feet in the mixture for instant relief and muscle relaxation.

Rheumatism: It is also a diuretic and can treat rheumatism and arthritis. It helps to flush out bacteria and toxins from the body.

Corns: Lemon juice can dissolve lumps on the skin, so it can be applied at the places where the skin has hardened up, like the soles of feet and the palms of your hands. Drinking lemon juice with water can help patients reduce gall stones for the same reasons.

Throat Infections: Lemon is an excellent fruit that fights against problems related to throat infections, due to its well-known   antibacterial properties.

High Blood Pressure: Drinking lemon juice is helpful for people suffering from heart problems, because it contains potassium. It controls high blood pressure, dizziness, and nausea, because it provides a calming sensation to both the mind and body. It is commonly employed to reduce mental stress and depression.

Lemon: Lemon has proved to be nature’s boon to everyone who uses it. It provides many valuable solutions to health-related problems, because it contains its own set of antiseptic and natural medications. In case of malaria, lemon will not cure it, but aids in the treatment. A good practice is to eat anywhere from a quarter to a half of a lemon per day to get the maximum benefits from this powerful little fruit!

Leave a reply