10 Health Benefits from Eating Tomatoes – ቲማቲምን ከመመገብ የሚገኙ 10 የጤና ጥቅሞች

10 Health Benefits from Eating Tomatoes – ቲማቲምን ከመመገብ የሚገኙ 10 የጤና ጥቅሞች

ቲማቲምን መመገብ ከጥሩ ጣዕማቸው ሌላ፣ ለጤናችንም አስተዋጽኦ ያደርጋሉ:: ይበልጥ እንድንመገበው የሚያደርጉ 10 ምክንያቶች! ቲማቲም ለጤናችን ከፍተኛ ጥቅም ባላቸው ባህርያት የተሞላ ነው፣ ቲማቲም ለጤናዎ መሻሻል ምን ያህል ጥቅም እንዳለው ለማወቅ ከፈለጉ ማንበብዎን ይቀጥሉ::

ቲማቲም በጣም ብዙ በሆኑ የጤና ጥቅሞች የተሞላ ነው:: በእርግጥም ደግሞ፣ ብቻቸውንም ሆነ እጅግ በተለያዩ አይነት የምግብ ዝግጅቶች ውስጥ ልንጠቀምበት እንችላለን:: ቲማቲምን ችላ ማለት ትተው በዘወትር የተመጣጠነ የምግብ አይነትዎ ውስጥ የጎላ ተሳትፎ ሊኖረው እንደሚገባ ለምን እንደሚያስፈልግ ለማወቅ ከፈለጉ ማንበብዎን ይቀጥሉ::

ቲማቲምን ከመመገብ የሚገኙ 10 የጤና ጥቅሞች

1. ቲማቲም ለቆዳችን ጥሩ መሆኑ::

ቲማቲም ከፍተኛ መጠን ያለውን የሊኮፔን(ጠንካራ ፀረ_ኦክሲዴሽን) ንጥረ ነገር ያለው ሲሆን ይህም ለቆዳ ጥራት ይሆናሉ ተብለው እጅግ በውድ ዋጋ የሚሸጡት ኮስሞቲክሶች የሚጠቀሙት ንጥረ ነገር ነው:: ቲማቲምን ለቆዳዎ ክብካቤ ለመሞከር ከፈለጉ፣ ከስምንት እስከ አስራ ሁለት በሚሆኑ ቲማቲሞች መጀመር ያስፈልጎታል፤ ቲማቲሙን በመላጥ የቲማቲሙ የውስጥ ቆዳ ከፊት ቆዳችን ጋር እንዲነካካ በማድረግ ማስቀመጥ:: የቲማቲሙ ልጣጭ በፊት ቆዳችን ላይ እንደተቀመጠ ቢያንስ ለ አስር ደቂቃ መቆየት ይገባዋል፣ በመቀጠልም መታጠብ:: ለፊታችሁም ንጹህ እና አንፀባራቂ ስሜት ይሰጣችኋል:: በአነስተኛ መልኩ ቀይ ቀለም ሊከሰት ይችላል፣ ይሁን እንጂ በቆይታ የሚጠፋ ይሆናል::

2. ቲማቲም ብዙ የካንሰር አይነቶችን ለመከላከል ይረዳናል::

የተለያዩ ጥናቶች እንዳመላከቱት በቲማቲም የሚገኘው ከፍተኛ መጠን ያለው ሊኮፔን በሽንት ፊኛ ቱቦ ካንሰር፣ በትልቁ አንጀት ካንሰር እንዲሁም በጨጓራ ካንሰር የመያዝ እድላችንን ለመቀነስ ያስችላል:: ሊኮፔን ተፈጥሯዊ አንቲ ኦክሲደንት ሲሆን የካንሰር ህዋሶችን እድገት ለማዘግየት ጉልህ ሚና ያለው ነው:: በማብሰል የተዘጋጀ ቲማቲም ደግሞ የበለጠ ሊኮፔን ይኖረዋል፣ ስለዚህም ታዋቂውንና ተወዳጁን የቲማቲም ሾርባ በማዘጋጀት ተጠቀሙ::

3. ቲማቲም ጠንካራ አጥንት እንዲኖረን ይረዳናል::

ቲማቲም ከፍተኛ መጠን ያለው የካልሲየም እና የቪታሚን_ኬ መገኛ ነው:: እነዚህ ንጥረ ነገሮችም አጥንትንም ሆነ የአጥንት ህዋሳትን ለማጠንከር እና አነስተኛ ጥገና ለማካሄድ በጣም አስፈላጊ ናቸው::

4. ቲማቲም ሲጋራ በማጨስ ምክንያት የተከሰተን ጉዳት ለመጠገን ይረዳል::

ቲማቲምን መመገብ ማጨስ እንድታቆሙ የሚረዳ አዲስ መጣሽ ወረት አይደለም:: ነገር ግን፣ ቲማቲም ሲጋራ በማጨስ በሰውነታችሁ ላይ የደረሰን ጉዳት ለመቀነስ የሚያስችል ነው:: ቲማቲም በውስጡ ኮውማሪክ አሲድ እና ክሎሮጀኒክ አሲድ ይገኙበታል እነዚህም ሰውነታችንን ከሲጋራ ጭስ ከሚመረት ከካርሲኖጅንስ እንዲከላከል ያደርጉታል::

5. ቲማቲም በጣም አስፈላጊ የፀረ_ኦክሲዴሽን መገኛ መሆኑ::

ቲማቲም ቀላል የማይባል ቪታሚን _ኤ እና ቪታሚን_ሲ ይገኝባቸዋል:: ይህም በመጀመሪያ እነዚህ ቪታሚኖች እና ቤታ_ካሮቲን በደም ውስጥ ጉዳት የሚያስከትሉትን ነጻ_ራዲካሎች ለማግለል እንደ ፀረ_ኦክሲዳንት ያገልግላሉ:: በደም ፍሰት ውስጥ የሚገኙ ነጻ ራዲካሎች አደገኛ ናቸው ምክንያቱም ህዋስን እስከማውደም ይደርሳሉ:: አስታውሱ፣ ቲማቲሙ የቀላ ከሆነ፣ የበለጠ ቤታ_ካሮቲን ይገኝበታል:: በተጨማሪም፣ ማብሰል በውስጡ የሚገኘውን ቪታሚን_ሲ እንደሚገለው ማወቅ ይኖርባችኋል፣ ስለዚህ ለእነዚህ ጥቅሞቹ ሲባል ቲማቲምን በጥሬው መመገብ ያስፈልጋል::

6. ቲማቲም ለልባችን ጥሩ መሆኑ::

በቲማቲም የሚገኙት ቪታሚን_ቢ እና ፖታሲየም ምክንያት፣ የኮሌስትሮል መጠንን እንዲሁም የደም ግፊትን ለመቀነስ አይነተኛ ሚና አላቸው:: ስለዚህም፣ ቲማቲምን በዘወትር ጤናማ የተመጣጠነ ምግብ ዝርዝርዎት ውስጥ በመጨመር የልብ ችግርን፣ ስትሮክን እንዲሁም ከልብ ጋር ተያያዥ የሆኑና ለህይወትዎ አስጊ የሆኑ ችግሮችን ለመከላከል ያስችልዎታል::

7. ቲማቲም ለጸጉራችን ጥሩ መሆኑ::

በቲማቲም የሚገኘው ቪታሚን_ኤ ጸጉርዎትን አንጸባራቂ እና ጠንካራ ለማድረግ ብቃት ያለው ነው:: በተጨማሪም፣ ለአይን፣ ለቆዳ፣ ለአጥንት እና ለጥርስ አስደናቂ ውጤት ያለው ነው::

8. ቲማቲም ለኩላሊታችን ጥሩ መሆኑ::

ቲማቲምን ያለፍሬያቸው በምግብዎ ማካተት፣ በአንዳንድ ጥናቶች እንደተረጋገጠው የኩላሊት ጠጠር የመከሰት እድሉን ይቀንሳል::

9. ቲማቲም ለአይናችን ጥሩ መሆኑ::

በቲማቲም የሚገኘው ቪታሚን ኤ የአይን እይታችንን ለማሻሻል አይነተኛ ሚና አለው:: በተጨማሪም፣ ቲማቲምን መመገብ የምሽት መታወርን (ናይት ብላይንድነስ) ለመከላከል ከምንመገባቸው ምርጥ ምግቦች አንዱ ነው::

ቲማቲም ክሮሚየም በተባለው እጅግ ጠቃሚ ማዕድን የተሞላ ነው:: የስኳር በሽተኞችንም የደም ውስጥ የስኳር መጠን በተሻለ መልኩ በቁጥጥራቸው ውስጥ እንዲሆን ይረዳቸዋል::

Ethiopian Food – Timatim Fitfit Recipe Injera Vegan Amharic English Fit tomatoes

አማርኛ Ethiopian Tomato Salad Recipe Timatim – Amharic

Ethiopian Beef & Tomato with Berbere & Mitmita Recipe Injera – Amharic with English subtitles

Ethiopian Food – Sinig recipe vegan long Peppers with Onion & Tomato Amharic English

 


ethiopian-recipe-health-blog-tomatoes-tmatim-diet

There is more to eating tomatoes than good taste, they are great for your health! 10 good reasons to eat more! Tomatoes are full of health enhancing properties, read on to discover how the humble tomato can improve your health.

Tomatoes are loaded with many, many health benefits. In fact, they are incredibly versatile and can be prepared in a seemingly endless number of dishes, as well as being great to eat alone. Keep reading to find out why you need to stop neglecting tomatoes as a part of your regular balanced diet.

10 Health Benefits from Eating Tomatoes

1. Tomatoes are good for your skin.

Tomatoes contain a high level of lycopene, which is a substance that is used in some of the more pricy facial cleansers that are available for purchase over-the-counter.
If you want to try tomatoes for skin care, you need to start with about eight to twelve tomatoes. Peel the tomatoes and then place the skin on your face with inside of the tomato touching your skin.
Leave the tomatoes on your face for a minimum of ten minutes, then wash. Your face will feel clean and shiny. Some redness may occur, but should fade with time.

2. Tomatoes help prevent several types of cancer.

A number of studies have been conducted that indicate that the high levels of lycopene in tomatoes works to reduce your chances of developing prostate, colorectal and stomach cancer.
Lycopene is a natural antioxidant that works effectively to slow the growth of cancerous cells. Cooked tomatoes produce even more lycopene, so go ahead and cook up a batch of your mom’s famous tomato soup.

3. Tomatoes help maintain strong bones.

Tomatoes contain a considerable amount of calcium and Vitamin K. Both of these nutrients are essential in strengthening and performing minor repairs on the bones as well as the bone tissue.

4. Tomatoes help repair damage caused by smoking.

No, eating tomatoes is not the most recent fad to help you quit smoking. However, tomatoes can reduce the amount of damaged done to your body by smoking cigarettes.
Tomatoes contain coumaric acid and chlorogenic acid that work to protect the body from carcinogens that are produced from cigarette smoke.

5. Tomatoes provide essential antioxidants.

Tomatoes contain a great deal of Vitamin A and Vitamin C. This is primarily because these vitamins and beta-carotene work as antioxidants to neutralize harmful free radicals in the blood.
Free radicals in the blood stream are dangerous because it may lead to cell damage. Remember, the redder the tomato you eat is, the more beta-carotene it contains. In addition, you also want to keep in mind that cooking destroys the Vitamin C, so for these benefits, the tomatoes need to be eaten raw.

6. Tomatoes are good for your heart.

Because of the Vitamin B and potassium in tomatoes, they are effective in reducing cholesterol levels and lowering blood pressure. Therefore, by including tomatoes in your regular balanced diet you can effectively prevent heart attacks, strokes as well as many other heart related problems that may threaten your life.

7. Tomatoes are good for your hair.

The Vitamin A in tomatoes works perfectly to keep your hair shiny and strong. In addition, it also does wonders for your eyes, skin, bones and teeth.

8. Tomatoes are good for your kidneys.

Adding tomatoes without seeds to your diet has been proven in some studies to reduce the risk of kidney stones.

9. Tomatoes are good for your eyes.

The Vitamin A found in tomatoes is fantastic for improving your vision. In addition, eating tomatoes is one of the best foods to eat to prevent the development of night blindness.

Tomatoes are packed full of the valuable mineral known as chromium. It works effectively to help diabetics keep their blood sugar levels under better control.

Recent Posts