Ethiopian Food FAQs

Below is a list of FAQs regarding Ethiopian food. We hope they help.

ተደጋግመው የተጠየቁ ጥያቄወች

ከዚህ በታች የኢትዮጵያን ምግብ በተመለከተ ተደጋግመው የተጠየቁ ጥያቄዎችን ያገኛሉ::


What is Berbere?

Berbere is a red powder consisting of the hottest red peppers blended with many other spices including ginger, cardamom, coriander, fenugreek, onion, and garlic. Berbere is a key ingredient in Ethiopian cuisine.

በርበሬ ምንድንነው?

በርበሬ ቀይ ቀለም ያለው ሲሆን በጣም የሚለባለብ ዛላ ከተለያዩ ቅመማት ተደባልቆ የሚዘጋጅ ነው ከእነዚህም ቅመማት ዝንጅብል፣ አዝሙድ፣ ኮረሪማ፣ አብሽ፣ ሽንኩርት እና ነጭ ሽንኩርትን ያካትታል:: በርበሬ በኢትዮጵያ የምግብ ዝግጅት ውስጥ አይነተኛውን ሚና ይይዛል::


What is Injera?

Injera is a crepe like flat bread used to eat Ethiopian food. Injera is primarily made out of teff or tef flour and is one of the smallest grains in the world. Unique to Ethiopia, injera is not eaten as a staple part of a diet in any other country. It has a slight sour taste. It takes about two to three days to prepare and is mixed with yeast and flour then fermented. It is cooked on a hot flat surface on one side only as a pancake type mix.

እንጀራ ምንድንነው?

እንጀራ ስስ ዳቦ የሚመስል የኢትዮጵያ የወጥ ምግቦችን እያጠቀስን እንድንመግብበት ነው:: እንጀራ በመሰረታዊነት የሚዘጋጀው ከጤፍ ነው፤ ጤፍ የአለማችን በጣም ትንሹ አዝዕርት ነው:: ይህም ለኢትዮጵያ ልዩ የሆነ ነው፣ እንጀራን ከኢትዮጵያ ውጭ እንደመሰረታዊ ምግብ የሚጠቀሙ ሀገሮች የሉም:: በመጠኑም ቢሆን ሆምጣጣ ጣዕም ያለው ነው:: ለማዘጋጀት ከ ሁለት እስከ ሶስት ቀናት የሚወስድ ሲሆን ቡኬቱን ከእርሾ ጋር በመደባለቅ እንዲብላላ ማድረግ:: የሚጋገረውም በጋለ ምጣድ ላይ::


What is injera eaten with?

Injera is pretty much eaten with all Ethiopian food. It is the single most staple item in the cuisine. As a bread, mixed, chopped, fried or dried, injera is a must.

እንጀራ በምን ነው የምንመገበው?

እንጀራ ከሁሉም አይነት የኢትዮጵያ ምግቦች ጋር መብላት ይቻላል:: ብቸኛው በሁሉም የምግብ አይነት የምናገኘው ነው:: እንደ ዳቦም፣ ተደባልቆም፣ ተፈትፍቶም፣ በድርቆሽና በሌሎችም መንገዶች መጠቀም የግድ ይለናል::


Whats is Doro?

Simply doro means chicken. Doro wat, wet or wot is a rich dish of chicken, eggs, onions and berbere. Probably the most famous Ethiopian dish.

ዶሮ ምንድንነው?

ዶሮ በእንግሊዘኛው ችክን ብለን እንጠራዋለን፣ ዶሮ ወጥ በ ዶሮስጋ፣በእንቁላል፣ በሽንኩርት እና በበርበሬ የተዋዛ ሲሆን ምናልባትም ከኢትዮጵያ ምግቦች ይበልጥ ተወዳጁ ነው::


What is Ethiopian food like?

Ethiopian food is typically stews and sauces served on injera.
There are of course many other dishes including tis and many vegan dishes.

የኢትዮጵያ ምግብ ምን ይመስላል?

በመሰረታዊነት የኢትዮጵያ ምግብ ወጥ እና የተለያዩ አይነት ስልስ በእንጀራ ላይ ተደርጎ የሚቀርብ ነው::

በርግጥ በጣም ብዙ አይነት ምግቦች አሉ ከነዚህም ውስጥ ጥብስ እና ሌሎች የአትክልት ምግቦችን ያጠቃልላል::


What is Mitmita?

Mitmita is a yellow chilli type powder and runs in a close to second to berbere within the cuisine.

ሚጥሚጣ ምንድንነው?

ሚጥሚጣ ብርቱካናማ ቀለም ያለው ሲሆን በደረጃ ብናስቀምጠው ከበርበሬ ሁለተኛው ነው ማለት እንችላለን::


Is Ethiopian food spicy?

Yes and No. Many dishes are very spicy indeed but not all at all.
Ethiopian food is very well balanced in this regard.

የኢትዮጵያ ምግብ ቅመም የበዛበት ነው እንዴ?

አወም አይደለምም:: በርግጥ አብዛኞቹ ምግቦች ብዙ ቅመም የሚገባባቸው ናቸው ግን ሁሉም ናቸው ማለት አይደለም::

በዚህ አንጻር ካየነው የኢትዮጵያ ምግብ ምጥን ምጥንጥን ያለ ነው::


Do Ethiopians eat pork?

In short NO they also do not eat shellfish, this is due to the fact that most people are Orthodox Christians and abstain for religious reasons.

ኢትዮጵያውያን የአሳማ ስጋ ይበላሉ እንዴ?

በአጭሩ አይመገቡም ከዚህ በተጨማሪ ባለሼል አሳም አይመገቡም፣ ምክንያቱም አብዛኞቹ የኦርቶዶችስ ክርስትና እምነት ተከታይ ስለሆኑና በሀይማኖታዊ ምክንያት ስለሚከለከል ነው::


What is Ethiopian butter?

Ethiopian butter is called Niter Kibbeh and is a spiced clarified butter, Ghee type butter. It is used in amy dishes and is the second most important ingredient behind berbere.

የኢትዮጵያ ቅቤ ምንድንነው?

የኢትዮጵያ ቅቤ በቅመም የተጣራ ነው፣ እንደ በህንድ ጊህ እንደሚባለው ቅቤ አይነት:: በአብዛኞቹ ምግቦች ላይ ጥቅም ላይ ይውላል ከበርበሬ ቀጥሎ በጣም ጠቃሚው ነው ለማለት እንችላለን::


Is Ethiopian coffee good?

Are you kidding me? YES Ethiopian coffee is fantastic.
Coffee is a huge export for Ethiopia and is drank with care and ceremony every where you go in Ethiopia.

የኢትዮጵያ ቡና ጥሩ ነው?

ትቀልዳላችሁ እንዴ? አወ! የኢትዮጵያ ቡና ከአእምሮ በላይ ድንቅ ነው::

ኢትዮጵያ ቡናን በከፍተኛ ሁኔታ ለውጭ ገበያ የምትልከው እና በመላው ኢትዮጵያ ውስጥም በጥንቃቄና በልዩ ስነስርዐት የሚጠጣ ነው::


Are there any Ethiopian vegetarian dishes?

Not only are there lots of vegetarian dish but many vegan dishes.
This is due to religion and the fact that fasting is a huge part of the Ethiopian culture. Fasting in the sense that no meat and or dairy products are eaten and not in the full abstinence of food.

ለአትክልት ተመጋቢወች የሚሆኑ የኢትዮጵያ ምግቦች አሉ እንዴ?

አሉ ብቻ አይደለም በጣም ብዙ ብዙ አለ እንጂ::

ይህ የሆነው ከሀይማኖት ምክንያት ነው ምክንያቱም ጾም የኢትዮጵያውያን ትልቁ አካል ነውና::  በጾም ወቅትም ከማናቸውም የስጋ አይነት እና የእንስሳት ተዋጽዖ ውጤቶች ከሆኑ ምግቦች መታቀብ ስለሚገባ ነው::