Ginger – The healing Power – ዝንጅብል _ የማዳን ሀይል

Ginger – The healing Power – ዝንጅብል _ የማዳን ሀይል

ዝንጅብል ከስኬታማ የቤት ውስጥ ተፈጥሯዊ ፈዋሾች ዋናውን ስፍራ የሚይዝ ነው:: በመላው አለም ታሪክ በተለያየ ባህል ውስጥ ሲጠቀሙት የኖረ ነው፣ ዝንጅብል ለጥገኛ ተዋስያን ህመሞች አስደናቂ የፈውስ ሀይል መሆኑ የተረጋገጠ ሀቅ ነው:: ይህ ቅመም እጅግ ጠቃሚ በሆኑ ንጥረነገሮች እና የማደስ አቅም ባላቸው ውህዶች የታጨቀ ነው:: ምንም እንኳ ዝንጅብል ለብዙ ትንሽ ለሚባሉ የጤና ችግሮች ልክ እንደ ሆድ ቁርጠት ፈውስ መሆኑ ቢታወቅም፣ አስደናቂነቱ ግን ካንሰርን ከፋርማሲ መድሀኒቶች የበለጠ መከላከል የሚችል መሆኑ ነው::

ዝንጅብል በውጤታማነት ካንሰርን የሚከላከል ነው::

ምንም እንኳ ዝንጅብል ለተለመዱ በሽታወች ፈውስ ቢሰጥም፣ በጽኑ የጤና ችግሮች ላይ ያለው መልካም ተጽዕኖ የሚዘነጋ መሆን የለበትም:: ከነዚህም ጽኑ የጤና ችግሮች ውስጥ ለአመታት ዝንጅብል እንደ መድህን ሊሆን የሚችለው ለማህጸን ካንሰር በሽታ ነው:: የሚቺጋን ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ የካንሰር ማእከል በምርምራቸው እንዳገኙት ዝንጅብል የማህጸን ካንሰርን ሴሎች የማውደም አቅም ያለው ነው:: ከዚህም በበለጠ ዝንጅብል ሁለት አይነት የሴል አሟሟት መነሻ ምክንያት እንደሆነ አግኝተዋል፣ እነዚህም _ አፖፕቶሲስ እና አውቶፋጊ ናቸው:: “አፖፕቶሲስ …የምንለው የካንሰር ሴሎች ከመሰረቱ ራሳቸውን ሲያጠፉ ሲሆን፤ ሌላው አይነት የሴሎች ሞት አውቶፋጊ ይባላል ይህም ሴሎች ራሳቸውን ሲያዋህዱ ወይም ራሳቸውን ሲያጠቁ ያለው ውጤት ነው::”

“ከተለያዩ የማህጸን ካንሰር የሴል መስመሮች እንደተረዳነው፣ ዝንጅብል ከኬሞ ቴራፒ ጋር በተመሳሳይ ወይም በተሻለ ደረጃ የሴሎችን ሞት የሚያፋጥን ነው” በማለት የዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሚቺጋን ሜዲካል ስኩል የጋይናኮሎጂክ ኦንኮሎጂ ሜዲካል ዶክተር ጄኒፈር ሮህዴ ገልጸዋል:: ኬሞ ቴራፒ ከፕላቲኒየም የተመሰረት የመድሀኒት አይነት ሲሆን በአብዛኛው የማህጸን ካንሰርን ለማከም ጥቅም ላይ ይውላል

የማህጸን ካንሰርን ለማከም ከመርዳት ውጭ፣ ዝንጅብል የትልቁ አንጀት ካንሰርን የሚከላከሉ የተለያዩ አይነት ጥቅሞች አሉት:: ዩኒቨርሲቲው እንዴት ዝንጅብል የትልቁን አንጀትና የፊንጢጣ የካንሰር ሴሎች እድገት ሊያዘግመው እንደሚችል አጥንተዋል:: በጆርናል ኦፍ ክሊኒካል ኦንኮሎጂ የታተመው አንድ ሙከራ እንደሚያሳየው የዝንጅብልን ስር የሚመገቡ፣ በትንሹ የ ትልቁ አንጀት መቆጣት እና የአንጀት መቆጣት እንዲኖር ያደርጋል፣ ይህም በትልቁ አንጀት ካንሰር የመያዝ አደጋን ይቀንስልናል:: ሌሎች ጥናቶች እንደሚያሳዩት፣ ዝንጅብል ለካንሰር መንስኤ ለሆኑ ኬሚካሎች የተጋለጡትን እጢ እንዲፈጥሩ ይረዳል::

2. በብዙ ሁኔታወች የሚረዳ የፀረ_መቆጣት ባህርይው

ከዚህ በፊት እንደተጠቀሰው፣ ዝንጅብል ጥሩ የሆነ የፀረ_መቆጣት ባህርይን የተላበሰ ነው:: በእርግጥ፣ ይበልጥ የሚታወቅበትም በዚህ ነው:: የፀረ_መቆጣት ውህዱ ውጤታማ በሆነ መልኩ የሚያስቆጣን ነገር ለመቀነስ ኋላፊነቱን የሚወስደው ጂንጂሮልስ በመባል ይታወቃል:: እነዚህ ውህዶች ዝንጅብልን ለተለያዩ ከሰውነታችን መቆጣት ጋር ለተያያዙ የጤና ችግሮች አስደናቂ መድህን የሚያደርጉት ናቸው::

በብዙ ጥናቶች ውስጥም፣ ምርምሮች እንዳገኙት ህመምን ለመቀነስ እና በሪህ እና በመገጣጠሚያ ቁርጥማት በሽታ የሚሰቃዩትን በእንቅስቃሴ ረገድ መሻሻል እንዲያሳዩ ውህዶቹ ኋላፊነቱን ይወስዳሉ:: በሁለቱ የህክምና ጥናቶች እንደተገኘው፣ 75% የመገጣጠሚያ ቁርጥማት በሽተኞች እና 100% የጡንቻ መሸማቀቅ በሽተኞች ከህመማቸው ፈውስ አግኝተዋል:: ከህመም ደረጃው መቀነስ በተጨማሪም፣ ውህዱ እብጠትን ለመቀነስ ይረዳል::

ከመገጣጠሚያ ቁርጥማት በሽተኞች በተጨማሪም፣ ዝንጅብል ሌላ አይነት በሰውነት መቆጣት የሚባባሱ በሽታወችን ጥቂቶችን ለመጥቀስ እንደ ስኳር፣ ከልክ ያለፈ ውፍረት፣ አልዝሀሚር፣ የተለያዩ የካንሰር አይነቶች፣ እና የልብ በሽታ ያለባቸውን ሰወች የሚጠቅም ነው:: ግን የዝንጅብል የጤና ጥቅም እዚህ ላይ የሚያቆም አይደለም::

3. በዝንጅብል የልብ ቃጠሎን/የአሲድ መደፋትን ማከም

በልብ ቃጠሎ እና በምግብ አለመፈጨት ጋር በተያያዙ በሽታወች የሚሰቃዩት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰወች፣ ከብዙ_ቢሊዮን ዶላር የመድሀኒት ኢንዱስትሪው የአሲድ ተካላካይ መድሀኒት ይልቅ ዝንጅብልን እንደ መድሀኒት ቢጠቀሙ ብዙ ገንዘባቸውን በቆጠቡ ነበር:: የአሲድ ተከላካይ መድሀኒቶች ፕሮቶን ፐምፕ ኢንሂቢቶርስ ወይም ፒፒአይ በመባል ይታወቃሉ የነዚህ መድሀኒቶች ዋጋም ከጥቅሙ ይልቅ ውድነቱ ያመዝናል:: እነዚህ መድሀኒቶችም ለአጥንት መሳሳት፣ ለማልአብዞርፕሽን ችግሮች፣ ለብርድ፣ ለካንሰር፣ እና ኮሎስትሪዱም ዲፌክታይል የሚያጋልጡ ናቸው::

መድሀኒት ለመጠቀም ከመፍጠን ይልቅ ዝንጅብልን መሞከሩ የተሻለ ነው:: በ2007 በጆርናል ኦፍ ሞለኪዩላር ሪሰርች እና ፉድ ኒውትሪሽን ላይ በታተመ ጥናት፣ ተመራማሪወች ለማነጻጸር የሞከሯቸው የዝንጅብልን ፀረ_አልሰር እና ፀረ_ሄሊኮባክተር ፓይሎሪ(ከአልሰር ጋር የሚያያዝ ባክቴሪያ) ባህርይ እና በብዛት አሲድ ተከላካይ መድሀኒቶችን እንደ ላንሶፕራዞል፣ ወይም ፕሪቫሲድ ናቸው:: አስደናቂ የሚያደርገውም፣ ዝንጅብል ከክኒን መድሀኒቶች ከስድስት እስከ ስምንት ጊዜ የበለጠ የተሻለ ሆኖ ተገኝቷል:: ጣልቃ ከመግባት ወይም በሆድ ውስጥ የአሲድ ገደብን ከማስወገድ(በመቀጠልም ፕሮቶላይቲክ ኢንዛየሞችን በማስቆምና ለመመረዝ የመጋለጥ አደጋን ይጨምረዋል)ውጭ፣ ዝንጅብል የአሲድ መደፋት አደጋን በመገደብ ጠንካራ ፕሮቶላይቲክ ኢንዛየሞችን ያጠራቅማል::

4. ሳል

ከብዙዎቹ የዝንጅብል ጥቅሞች በተጨማሪ፣ ለሳልም በጣም ተመራጩ መድሀኒት ነው:: ዝንጅብልን በመጠኑ ከትፎና አፍልቶ መጠቀም ጠንካራ መድሀኒት ያደርገዋል፣ ከማፍላታችን በፊት በደንብ መክተፍ ያስፈልገናል:: ይህም የንጥረ ነገሮችን ቆይታ ለማራዘም ይረዳል:: የዝንጅብልን ሻይ መጠጣትም ለሚከነክን ጉሮሮ፣ ለማያቋርጥ ሳል እና አክታ ፍቱን ነው::

5. ለሚከነክን ጉሮሮ

ለእነ ሳል፣ ለሆድ ቁርጠት፣ እንዲሁም ደግሞ ለራስ ምታት ፍቱን እንደሆነ ሁሉ ከዝንጅብል የተዘጋጀ ሻይ ለሚከነክን ጉሮሮ ጥሩ መድሀኒት ነው:: በዚህ ገጽ ላይ ከተጠቀሱት የሻይ አይነቶች አንዱን ሞክሩ ወይም 1 ኢንች የዝንጅብል ስሩን ወይም ጥቂት ክታፊውን በማፍላት፣ በመቀጠልም ማር ወይም ሎሚ ጨምሮ መጠቀም::

6. ለታፈነ አፍንጫ

የዝንጅብል ሻይ ከኮኮናት ወተት እና በአካባቢያችሁ ከምታገኙት ማር ጋር በመቀላቀል መጠቀም:: ይህ ለአስደናቂው ጣዕሙ ብቻ አይደለም: ያፈናችሁን ንፍጥ በማስወገድ የመከላከል አቅማችሁንም ያግዛል::

7. ለሆድ ቁርጠት

ብዙ አይነት እጽዋት እና ቅመሞች ለሆድ ቁርጠት ማስታገሻነት ጥሩ ናቸው፣ ቢሆንም ግን የዝንጅብልን ፈዋሽነት የሚስተካከል የለም:: በተለምዶ ሆዱን ለሚያቅለሽልሸው ሰው የዝንጅብል መጠጥ ይሰጣል:: ጥቂት ዝንጅብሎች ወይም የሚንት ቅጠሎችን በሚፈላ ውሀ ውስጥ ለጥቂት ደቂቃወች በመዘፍዘፍ ከአንድ ማንኪያ ማር ጋር መጠቀም ለሆድ ቁርጠት ማስታገሻነት ይውላል::

8. የራስ ምታት/ሚግራይንስ(ከባድ የራስ ምታት)

እንደ ቆንዶ በርበሬ፣ የካይኔ ቃሪይ እና እንደ ዝንጅብል ያሉ እጽዋቶች የራስ ምታትንና ሚግራይንስን ለማስታገስ ይጠቅማሉ:: በተለየ ደግሞ ዝንጅብል በሚግራይንስ ሰበብ የሚከተለውን የማቅለሽለሽ ችግር ለመከላከል ይጠቅማል:: እነዚህን 3 አይነት እጽዋቶች እንደተፈጥሯዊ መድሀኒት በሻይ ለመጠቀም፣ አንድ ኢንች የዝንጅብል ክታፊ ከአንድ የሻይ ማንኪያ ቆንዶ በርበሬ ጋር እና ትንሽ ካይኔ በሚፈላ ውሀ ውስጥ በመነስነስ መቀላቀል:: ከመጠጣታችሁ በፊትም የተቀላቀለው በደንብ እስኪዋሀድ ድረስ ለ 15 ደቂቃ ማቆየት:: ለማጣፈጫ መጠቀም ያለባችሁም ማርን ወይም ስቲቪያን ብቻ ነው::

9. የጥርስ ቁርጥማት

ከሌሎች የዝንጅብል የጤና ጥቅሞች ውስጥ ደግሞ፣ ይህን ቅመም ለጥርስ ቁርጥማት ማስታገሻነት መጠቀም ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የኖረ ነገር ነው:: ለአብዛኛው ሰው የጥርስ ቁርጥማት ህመሙን ወዲያው ያስታግስለታል:: ጥሬ ዝንጅብልን በድድ በማሻሸት መሞከር ወይም የዝንጅሉን ስር በማፍላት፣ ከቀዘቀዘ በኋላ አፋችሁን ለመጉመጥመጥ መጠቀም::

10. ህመም

ዝንጅብል ከሰውነት መቆጣት ወይም ከቁርጥማት ጋር የተያያዙ በሽታወችን መርዳት ብቻ ሳይሆን ለሆድ ቁርጠት፣ ለሚከነክን ጉሮሮ፣ ለጥርስ ህመም እንዲሁም ደግሞ ለጡንቻ መሸማቀቅ ችግሮች ማስታገስ የሚችል ነው:: በጆርናል ኦፍ ፔይን እንደታተመው ጥናታዊ ምርምር ከሆነ በዝንጅብል ውስጥ የሚገኙ ውህዶች እነ ጂንጅሮል፣ ሻጎል፣ እና ዚንግሮኔ አካላዊ መቆጣትን ለማስታገስ (NSAIDS ተብለው ከሚታወቁት) ከተፈበረኩ መድሀኒቶች በተሻለ መድህን ናቸው:: ከልምምድ በኋላ ትንሽ የዝንጅብል ሻይን ይሞክሩ፣ እና ምናልባት ካልሰራላችሁ፣ ሌላ የተፈጥሮ ማስታገሻ መድሀኒቶችን ይሞክሩ::

በመሰረታዊነት፣ ዝንጅብልን በስፋት የሚጠቀሙ ቻይና ውስጥ ነው:: አሁን ላይ ግን፣ በመላው አለም ብዙ እርሻወች አሉ _ በተለይ ደግሞ በ ምስራቅ አፍሪካና በ ካሪቢያን ይገኛሉ:: ለዚህ ነው የዕጽዋት ህክምና፣ የወይባ ህክምና፣ አዩርቪዳ እና ናቱሮፓዚ የመሳሰሉት የተፈጥሮ ህክምና አይነቶች በዝንጅብል ዘርፈ ብዙ ጥቅም ላይ የተመሰረቱት::

ሰወችም በዝንጅብል ዘርፈ ብዙ የጤና ጥቅሞች ለዘመናት ተጠቃሚ ሆነው ኖረዋል፣ ይህን ቅመምም በምግባችሁ ላይ የምትጠቀሙበት ብቻ አለመሆኑንና ጠንካራ የተፈጥሮ መድሀኒት መሆኑንንም ተገንዝባችኋል::

ዝንጅብል በ ሎሚ ሻይ – Amharic Ginger Lemon Detox Tea

አማርኛ How to Make Ethiopian Spiced Tea Recipe

አማርኛ Coffee Leaf Tea – Amazing – Antioxidants Diabetes Weight Loss

አማርኛ Ethiopian Coffee Ceremony – Traditional Bunna Drinking explained


ethiopian-food-recipes-ginger-health-drink-diet-amharic-blog-injera

Ginger truly does top the list of effective natural home remedies. Being used throughout history by different cultures around the world, ginger harnesses an incredible healing power proven for a host of ailments. The spice is packed with essential nutrients and rejuvenating compounds. While ginger has been shown to help countless ‘minor’ problems such as an upset stomach, amazingly the health benefits of ginger also include combating cancer more effectively than pharmaceutical cancer drugs.

1. Ginger is a Powerful Cancer Fighter

While ginger helps common illnesses, it’s positive effect on more serious health conditions can not be disregarded. One such serious health condition that ginger has been known to help treat for years is ovarian cancer. The University of Michigan Comprehensive Cancer Center found out through their research that ginger can also destroy ovarian cancer cells. What’s more, they found that ginger triggered two types of cell death – apoptosis and autophagy. “Apoptosis…results from cancer cells essentially committing suicide. The other type of cell death, called autophagy, results from cells digesting or attacking themselves.”

“In multiple ovarian cancer cell lines, we found that ginger induced cell death at a similar or better rate than the platinum-based chemotherapy drugs typically used to treat ovarian cancer,” says Jennifer Rhode, M.D., a gynecologic oncology fellow at the U-M Medical School.

Aside from helping to treat ovarian cancer, ginger also offers plenty of protective benefits for colon cancer. The University studied how ginger could hinder the progression of colorectal cancer cells. One trial published in the Journal of Clinical Oncology has shown that those consuming ginger root had lower levels of colon inflammation and inflammation of the intestines, thereby helping to reduce the risk of colon cancer. Other studies have also shown that ginger could help tumor formation for those exposed to a cancer-causing chemical.

2. Anti-Inflammatory Properties Help with Many Conditions

As mentioned earlier, ginger possesses awesome anti-inflammatory properties. In fact, it may be what the root is best known for. The anti-inflammatory compounds responsible for significantly reducing inflammation are called gingerols. These compounds make ginger an amazing beneficial tool for various inflammatory-related health conditions.

In numerous research pieces, researches found that the compounds are responsible for reduction in pain and improvement in mobility for those with osteoarthritis or rheumatoid arthritis. In two clinical studies, it was found that 75% of arthritis patients and 100% of patients with muscular discomfort experienced relief of pain and/or swelling. In addition to pain levels decreasing, the compounds may also lessen swelling.

In addition to helping those with arthritis, ginger can also benefit those experiencing other diseases caused by or fueled by inflammation such as obesity, diabetes, Alzheimer’s disease, numerous cancer types, and cardiovascular disease, to name a few.

But the health benefits of ginger don’t stop there.

3. Treating Heartburn/Acid Reflux with Ginger

Millions suffering from heartburn and indigestion might be saving a pretty penny if they gave ginger a try as a treatment for heartburn instead of the multi-billion dollar drug industry’s many acid-blockers. The costs of pharmaceuticals for acid reflux, known as proton pump inhibitors, or PPIs, may well outweigh any potential benefit. These drugs have been known to increase risks of bone fractures, malabsorption issues, pneimonia, cancer, and Clostridum difficile.

Instead of turning to drugs, just try ginger. In a 2007 study published in the journal Molecular Research and Food Nutrition, researchers compared the anti-ulcer and anti-Helicobacter plyori (a bacteria linked to ulcers) properties of ginger and conventional acid-blockers like Lansoprazole, or Prevacid. Remarkably, ginger performed six to eight times better than the drugs. Rather than interfering with or removing stomach acid barrier (and thereby deactivating proteolytic enzymes and increasing risk of infection), ginger inhibits acid reflux and contains potent proteolytic enzymes.

4. Cough

In addition to the countless other ginger benefits, it is also one of the most famous natural cures for cough. The ginger has to be partially sliced and boiled and to ensure potency, should be crushed a bit before boiling. This will help to draw out the active ingredients. Drinking ginger as a tea will ease sore throat, non-stop coughing and even congestion.

5. Sore Throat

As with cough, upset stomach, and headaches, tea made with ginger is also great for a sore throat. Try one of the tea’s mentioned on this page, or boil a 1 inch piece of ginger root or a few slices, then add honey and/or lemon.

6. Stuffy Nose/Congestion

Try having some ginger tea with coconut milk and local honey. This isn’t only for amazing taste; it breaks up phlegm and gives a boost to the immune system.

7. Upset Stomach / Improved Digestion

Many herbs and spices are great for calming upset stomachs, and ginger is no exception. It’s the logic behind giving someone who’s seasick some ginger ale. Grate some ginger or pluck a few sprigs of mint leaves and steep in boiling water for a few minutes and enjoy with a spoonful of raw honey to subdue a bellyache.

8. Headaches/Migraines

Herbs like peppermint, cayenne pepper and ginger can be beneficial in the treatment of headaches and migraines. Ginger is especially useful to combat the nausea that often accompanies migraine headaches. To use the 3 herbs together in tea as a natural pain reliever, mix a one inch piece of ginger with a teaspoon of dried peppermint and a pinch of cayenne in boiling water. Allow the mixture to seep for 15 minutes before drinking. Sweeten only with  honey or stevia.

9. Toothache

Also among health benefits of ginger, using the spice as a home remedy for toothaches is something that has been passed down from generation to generation. Many people even experience immediate relief from the tooth pain. Try rubbing raw ginger into the gums or boil the ginger root, letting it cool and using it as a mouth rinse.

10. Pain

In addition to helping treat pain associated with inflammation (joint pain), upset stomach, sore throat, and toothache, ginger can also help with muscle soreness. The compounds gingerol, shogaol, and zingerone found in ginger are more effective than drugs for inflammation drugs known as NSAIDS, according to a study published in the Journal of Pain. Try some ginger tea after a workout, and if it doesn’t work, try some other natural pain relievers.

Originally, ginger was mostly used in China. These days, there are many plantations across the globe — particularly in East Africa and the Caribbean. This is why many branches of natural health care like herbal therapy, aroma therapy, ayurveda and naturopathy depend on the multiple gigner benefits.

People have been experiencing the many health benefits of ginger for ages; it is time that you see it as more than just an ingredient for your dishes, but also as a powerful natural remedy.

Recent Posts