Health Benefits of Honey – የማር የጤና ጥቅሞች::

Health Benefits of Honey – የማር የጤና ጥቅሞች::

ማር ላለፉት 2500 አመታት ቁጥራቸው በርከት ባሉ ሀገራት ዘንድ ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል:: በበርካታ የጤና ጥቅሞቹ ምክንያት ማር እንደ አዩርቪዲክ ህክምናወች ባሉ ባህላዊ መድሀኒቶች ዘንድ ጠቃሚ ግብዐት ነው፤ ሳይንቲስቶችም ማርን ከዘመናዊ መድሀኒትነት ጋር በተያያዘ በተለይም ደግሞ ቁስልን ለማዳን ባለው ጥቅም ዙሪያ እየተመራመሩ ይገኛሉ::

በጀርመን ሆኒግ ተብሎ ይታወቃል፣ በጣልያን ሜሌ፣ በሂንዲ ሻሃዳ፣ በፈረንሳይ እና በስፓኒሽ ሜኤል፣ በፖርቱጊዝ ሜል፣ በሩስያ ሜ፣ በደች ሆኒንግ በመባል ይታወቃል፤ በየትኛውም የአለም ክፍል ማር በሰፊው የማይጠቀምና እንደ ባህላዊ ምግብ የማያከብረው የለም ማለት ይቻላል::

ማርን ምን ታዋቂ አደረገው? በጣም ትርጉም የሚሰጥ ምክንያት የሚሆነው፣ ለምግብነት የምናውልበት መንገድ ቀላል መሆን ነው፣ ማርን በቀጥታ መመገብ ይቻላል፣ በዳቦ በመቀባት መጠቀም፣ ከጭማቂ ጋር መደባለቅ ወይም በማንኛውም መጠጥ እንደ ስኳር መጠቀም፣ ወይም ከሞቀ ውሀ ጋር መደባለቅ፣ ከሎሚ ጭማቂ ጋር፣ ከቀረፋ እና ከሌሎች ዕጾች ጋር በመደባለቅ ለመድሀኒትነት መጠቀም ይቻላል:: ባለው ጣዕምና የጤና ጥቅም ምክንያት በብዙ ነገሮች ውስጥ ይካተታል፣ ይህም በጣም ጠቃሚ እና ለተለያየ ነገር የምንጠቀምበት ያደርገዋል::

ከማር የጤና ጥቅሞች ውስጥ ከባህላዊ እና ከዘመናዊ የህክምና ባለሙያወች የተወሰዱት የሚከተሉት ይካተታሉ::

ማጣፈጫ: በብዙ መጠጥ እና ምግብ አይነቶች ዘንድ ማር የስኳር ትክ መሆን ይችላል:: ማር ወደ 69% የሚሆን ጉሉኮዝ እና ፍሩክቶዝ ያለው ሲሆን፣ ይህም ከኖርማሉ ነጭ ስኳር በተሻለ መልኩ ለጤና ጥሩ የሆነ ማጣፈጫ ያደርገዋል::

ክብደት ለመቀነስ: ምንም እንኳ ማር ከስኳር የበለጠ ካሎሪ ቢኖረውም፣ ማርን በሞቀ ውሀ ሲጠቀሙት፣ በሰውነት ውስጥ የተከማቸን ስብ ለማቃጠል ይረዳል:: በተመሳሳይ፣ ማር እና ሎሚ ጁስ እንዲሁም ማር እና ቀረፋ ክብደት ለመቀነስ ይረዳሉ::

የጉልበት ምንጭ: ዩኤስዲኤ እንደሚለው አንድ የሻይ ማንኪያ ማር 64 ካሎሪ አለው:: ስለዚህ፣ ማር ለብዙ ሰወች እንደ ሀይል ምንጭነት ያገለግላል:: ከሌላ አንጻር፣ አንድ የሻይ ማንኪያ ስኳር የሚሰጠው 15 ካሎሪ ብቻ ነው:: ከዚህ በተጨማሪ፣ በማር ውስጥ የሚገኘው ካርቦ ሀይድሬት በቀላሉ ወደ ግሉኮስ የሚለወጥ ሲሆን ይሀውም በጨንጓራችን ስሱ ክፍል የሚከወን ይሆናል፣ ይህ የሆነው በሰውነታችን ለመፈጨት የማያስቸግር ንጹህ፣ የተፈጥሮ ንጥረ ነገር ስለሆነ ነው::

የአትሌቲክስ አቋምን ያሻሽላል፤ የቅርብ ጊዜ ጥናቶች እንደሚያመለክቱትም ማር ምርጥ የ ኢርጎጀኒክ ረዳት እና የአትሌቶችን አጠቃላይ አቋም ለማገዝ የሚረዳ ነው:: ማር የደም ውስጥ የስኳር መመጠንን ለማስተካከል፣ ጡንቻ በቶሎ እንዲያገግም፣ ከልምምድ በኋላ ግላይኮጅንን መልሶ ለመገንባት፣ የሰውነታችን ውስጥ የሚገኘውን የኢንሱሊን መጠን ለማስተካከል እንዲሁም የምናወጣውን ጉልበት ለማስተካከል አይነተኛው መንገድ ነው::

የቫይታሚንና የማዕድን ምንጭነቱ: ማር የተለያዩ አይነት ቪታሚኖችንና ማዕድናትን የያዘ ነው:: የቫይታሚኑና የማዕድኑ አይነት እና ብዛት የሚወሰነው ንቦች በሚቀስሙት የአበባ አይነት ነው:: ማር በብዛት ቫይታሚን ሲ፣ ካልሲየም እና አይረን ይገኙበታል:: በተለምዶ የሚገኘውን ስኳር ወስደን የቪታሚን እና የማዕድን ይዘቱን በምናረጋግጥበት ጊዜ የምናገኘው ውጤት ምንም ወይም ደግሞ ወደ ምንም የተጠጋ ይሆናል::

ፀረ_ባክቴሪያል እና ፀረ_ፈንጋል ባህርይው: ማር ፀረ_ባክቴሪያ እና ፀረ_ፈንጋል ባህርይ ያለው ነው፣ ስለዚህ በባህላዊ ህክምና ዘንድ፣ በአብዛኛው እንደተፈጥሯዊ ፀረመርዝነት ይጠቀሙበታል::

ፀረ_ኦክሲደንት: ማር በተለያዩ የምግብ ንጥረነገሮች የበለጸገ ነው፣ ይህም በሰውነታችን ላይ ጥቃት የሚያደርሱ ነገሮችን ለማስወገድ ስኬታማው መንገድ ነው:: በዚህ ምክንያትም፣ ሰውነታችን ከተለያዩ ሁኔታወች እንዲሁም በአንዳንድ አጋጣሚዎች ገዳይ ከሆኑት እንደ ካንሰር ወይም የልብ በሽታ የመሳሰሉትን የመቋቋም አቅሙ ይሻሻላል::

በወተት እና በማር የቆዳ ክብካቤ: በአብዛኛው ወተት እና ማር በአንድነት የሚቀርቡ ናቸው፣ የእነዚህ ጥምረትም ለስላሳ እና የሚያምር ቆዳ እንዲኖረን ያደርጋል:: በዚህ ምክንያትነትም ማር እና ወተትን ዘወትር ጠዋት መጠቀም በብዙ ሀገሮች ዘንድ የተለመደ ተግባር ነው::

ማርን ቁስልን በማከም መልኩ: ማር ቁስልን በማከም ረገድ ያለውን ጥቅም ለማጥናት ታላላቅ ምርምሮች ተካሂደዋል:: የነርሲንግ ስታንዳርድም ማር ቁስልን በማከም ዙሪያ ያለውን ጥቅም በጥቂቱ ለማብራራት ይሞክራል:: እነዚህም የሚከተሉት ናቸው::

ማር ፀረ_ረቂቅተዋስያን ባህርይ ያለው መሆኑ::

በመርዛማነት የተጎዳ ስጋን ተቀርፍቶ እንዲከላ ይረዳል

መጥፎ ሽታ ያላቸውን ቁስሎች ሽታቸው እንዲጠፋ ያደርጋል::

የተጎዱ ቲሹወችን በፍጥነት እንዲያገግሙ ያነቃቃቸዋል::

የማር የማዳን አቅም አልተጋነነም:: የዋይካቶ የማር ምርምር ዩኒት፣ ማር በመድሀኒት ላይ ስላለው ጥቅም እየተደረጉ ስለአሉት አለም አቀፍ ጥናቶች ዝርዝር መረጃ ያቀርባል:: ከዚህ በተጨማሪም፣ በሀምሌ 2006 እኤአ BBC እንደዘገበው በማንችስተር፣ ዲድስቡርይ በሚገኘው የክሪስቲ ሆስፒታል ዶክተሮች፣ የካንሰር በሽተኞች በፍጥነት እንዲያገግሙ ማርን ለመጠቀም እንዳቀዱ ዘግቧል:: እንዲህ አይነት ምርምሮች በተለምዶ “እምነት” ስለጣልንበት ነገር በሳይንሳዊ መረጃ ሲረጋገጥ የኛን በማር ላይ ያለን እምነት በሌሎች ሰወች ላይም ይኖር ዘንድ ለማስተጋባት ይረዳል::

አሁን ስለ ማር ጥቅም አውቃችኋል፣ እና እንዴት አድርጋችሁ ትመገቡታላችሁ? እንዲሁ በጥሬው ልትመገቡት ትችላላችሁ፣ በውሀ ወይም በተለያዩ አይነት መጠጦች ጨምራችሁ እንዲሁም በተለያዩ አይነት የምግብ አይነቶች ልትጠቀሙት ትችላላችሁ:: (organic facts) ተፈጥሯዊ እውነታወች በፈጣንና ቀላል የማር ምግብ ዝግችቶች ላይ ኤሌክትሮኒክ መጽሀፍ አሳትሟል::

ዝንጅብል በ ሎሚ ሻይ – Amharic Ginger Lemon Detox Tea

አማርኛ How to Make Ethiopian Spiced Tea Recipe

አማርኛ Coffee Leaf Tea – Amazing – Antioxidants Diabetes Weight Loss

አማርኛ Ethiopian Coffee Ceremony – Traditional Bunna Drinking explained


ethiopian-recipes-honey-diet-health-blog-injera-cooking-ethiopia-amharic

Honey has been used by countless cultures all around the world over the past 2,500 years. While the numerous health benefits of honey have made it an important element of traditional medicines such as Ayurvedic treatments, scientists are also researching the benefits of honey in relation to modern medicine, particularly in the healing of wounds.

It is known as Honig in German, Miele in Italian, Shahad in Hindi, Miel in French and Spanish, Mel in Portuguese, мед in Russian, Honing in Dutch, and μελι in Greek; there is almost no part in the world where honey is not widely used and celebrated as a part of the cultural diet.

But what makes honey so popular? Most likely, it is the ease with which it can be consumed. One can eat honey directly, put it on bread like a jam, mix it with juice or any drink instead of sugar, or mix it with warm water, lime juice, cinnamon and other herbs to make a medicine. It is savored by all due to its taste as well as health benefits, making it extremely useful and versatile.

The health benefits of honey include the following treatments, taken from both traditional and modern medical experts.

Sweetener: Sugar can be substituted with honey in many food and drinks. Honey contains about 69% glucose and fructose, enabling it to be used as a sweetener that is better for your overall health than normal white sugar.

Weight Loss: Though honey has more calories than sugar, when honey is consumed with warm water, it helps in digesting the fat stored in your body. Similarly, honey and lemon juice as well as honey and cinnamon help in reducing weight.

Energy Source: According to the USDA, honey contains about 64 calories per tablespoon. Therefore, honey is used by many people as a source of energy. On the other hand, one tablespoon of sugar will give you about 15 calories. Furthermore, the carbohydrates in honey can be easily converted into glucose by even the most sensitive stomachs, since it is very easy for the body to digest this pure, natural substance.

Improving Athletic Performance: Recent research has shown that honey is an excellent ergogenic aid and helps in boosting the performance of athletes. Honey is a great way to maintain blood sugar levels, muscle recuperation and glycogen restoration after a workout, as well as regulating the amount of insulin in the body, as well as energy expenditure.

Source of Vitamins and Minerals: Honey contains a variety of vitamins and minerals. The type of vitamins and minerals and their quantity depends on the type of flowers used for apiculture. Commonly, honey contains Vitamin C, Calcium and Iron. If you check the vitamin and mineral content in regular sugar from any other source, you will find it to be completely absent or insignificant.

Antibacterial and Antifungal Properties: Honey has anti-bacterial and anti-fungal properties, so it is often used as a natural antiseptic in traditional medicines.

Antioxidants: Honey contains nutraceuticals, which are very effective for the removal of free radicals from the body. As a result, our body immunity is improved against many conditions, even potentially fatal ones like cancer or heart disease.

Skin Care with Milk and Honey: Milk and honey are often served together, since both of these ingredients help in creating smooth, beautiful skin. Consuming milk and honey every morning is a common practice in many countries for this very reason.

Honey in Wound Management:  Significant research is being carried out to study the benefits of honey in the treatment of wounds. The Nursing Standard explains some of these benefits of honey in wound management in the document. These have been listed below:

  • Honey possesses antimicrobial properties.
  • It helps in promoting autolytic debridement.
  • It deodorizes malodorous wounds.
  • It speeds up the healing process by stimulating wound tissues.

The healing powers of honey are not overstated. The Waikato Honey Research Unit provides details about the world-wide research that is being carried out on the benefits of honey in medicine. Furthermore, BBC reported in July of 2006 that doctors at the Christie Hospital in Didsbury, Manchester are planning to use honey for faster recovery of cancer patients after surgery. Such research will provide scientific evidence for the so-called “beliefs” held by honey lovers all over the world and will help in propagating the benefits of honey to more people.

Now that you know the benefits of honey, how do you eat it? You can eat it raw, add it to water or different beverages and you can also add it to several recipes. Organic Facts has actually published an eBook on quick and easy honey recipes.

Recent Posts