Injera

We will start by asking – What is Injera?

Injera is a type of flatbread made in Ethiopia and several other East African nations. The bread is a staple food in Ethiopia, where it is served with almost every meal.

True injera is made with teff flour, a gluten free flour produced from teff but it can be made without, below we have several recipes to demonstrate this.

Injera has a distinctive sour flavour and spongy texture which makes it ideally suited to sopping up curries, stews, and other wet dishes.

እንጀራ

በመጀመሪያ በመጠየቅ እንጀምራለን _ እንጀራ ምንድን ነው?

እንጀራ ስስ ዳቦ የሚመስል በኢትዮጵያና ባብዛኞቹ የምስራቅ አፍሪካ ሀገሮች የምናገኘው ነው:: ይህ ስስ ዳቦ የኢትዮጵያ መሰረታዊ ምግብ ነው፣ ከሁሉም የምግብ አይነቶች ጋር የሚቀርብ ነው::

ትክክለኛ እንጀራ የምንለው ከጤፍ የሚጋገረውን ሲሆን ካለጤፍም ልናዘጋጅው እንችላለን፣ ጤፍ ከ ግለተን ነጻ የሆነ አዝዕርት ነው:: ከዚህ በታች የተለያዩ ያሰራር መምሪያዎች አሉን::

እንጀራ ለየት ያለ ኮምጣጣ ባህሪ ያለው ሰፍነግ ያለ ሲሆን የተለያዩ ወጦችን እያጠቀስን ለመመገብ ተመራጩ ነው::


Making Injera

It does take a little skill and several goes to get your Injera right. Do not this put you off as once you master it you will be so happy with yourself. The other issue to consider is that it takes several days to complete the task (see below).

To make injera, cooks ferment ground teff at room temperature, much like cooks producing sourdough in other parts of the world.

The fermentation collects natural yeasts, which provide some loft for the bread and impart a classically sour flavour. It is possible to over ferment the teff, potentially creating a borderline alcoholic dough or simply a sour, distasteful dough which will not be pleasant to eat.

Variations on the flatbread can be made with different types of teff flour, or with flour blends.  Once the dough is fermented, it is lightly salted and then fried, either on a griddle or in a large pan.  Since teff has no gluten, the bread will not rise, but it will acquire a dense, spongy texture.

In Ethiopia, injera often lines serving dishes and pans, with diners tearing small pieces off to scoop up food as needed. In regions where teff is expensive or unavailable, other grains may be used as substitutes, sometimes to the great detriment of general flavour.

Injera is made with teff, a tiny, round grain that flourishes in the highlands of Ethiopia. While teff is very nutritious, it contains practically no gluten. This makes teff ill-suited for making raised bread, however injera still takes advantage of the special properties of yeast. A short period of fermentation gives it an airy, bubbly texture, and also a slightly sour taste.

Teff is the smallest grain in the world. It takes about 150 teff seeds to equal the weight of a kernel of wheat!


የእንጀራ ዝግጅት

ጥሩ እንጀራ ለመጋገር ባለሙያ መሆን እና ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ማድረግ ያስፈልጋል:: አልሆነልኝም ብሎ መተው አያስፈልግም ምክንያቱም አንዴ በደንብ ከቻላችሁበት በሙያችሁ ትደሰታላችሁ:: ሌላው መገንዘብ ያለባችሁ ጠንቅቆ ለማዘጋጀት ጥቂት ቀናትን እንደሚወስድ ነው:: (ከታች ይመልከቱ)

እንጀራን ለማዘጋጀት በረድ ባለ ሙቀት ውስጥ የጤፉን ዱቄት በማቡካት እንዲብላላ ማድረግ፣ ልክ በሌላው አለምም እርሾን እንደሚጠቀሙት ማለት ነው::

መብላላቱ የተፈጥሮ እርሾ ይሰብስብልናል፣ ይህም ለምንጋግረው እንጀራ ለየት ያለ ኮምጣጣነት ጣዕም ያላብሰዋል::

የምንጋግረው እንጀራ እንደምንጠቀመው የዱቄት አይነት ወይም የዱቄት ድብልቅ ሊለያይ ይችላል:: አንዴ ቡኬቱ ከተብላላ በኋላ በትንሹ ጨው ይጨመርና ሰፋ ባለ መጥበሻ ወይም በምጣድ እንጋግረዋለን:: ጤፍ ከግለተን ነጻ ስለሆነ ስንጋግረው የማይነፋ ሲሆን ግን ጥቅጥቅ ያለ እና ስፍንግ ያለ ባህሪ አለው::

በኢትዮጵያ እንጀራ ከስር ሆኖ ከላይ ወጥ በማድረግ ይቀርባል፣ ተመጋቢወችም ትንሽ ቁራሽ እየቆረሱ በወጥ በማጣቀስ ይመገባሉ:: በአንዳንድ አካባቢወች ጤፍ ውድ በሆነበት ወይም በማይገኝበት አካባቢ በለሎች አዝዕርቶች ተክተን ልንጠቀም እንችላለን፤ እንደዚህ ስናደርግ ለአጠቃላይ ጣዕም አሪፍ ነው::

እንጀራ ከጤፍ ነው የሚዘጋጀው:: እነዚህ እጅግ ደቃቅ ትንንሽ አዝዕርቶች የሚበቅሉት በኢትዮጵያ ከፍተኛ ቦታወች ነው:: ጤፍ በንጥረ ነገሮች የበለጸገና ምንም አይነት ግለተን የሌለው አዝዕርት ነው:: በዚህ ምክንያት ከጤፍ የሚነፋ ዳቦ ለማዘጋጀት አይሆንም፣ ቢሆንም ግን የእርሾን ልዩ የሆነ ባህሪ በደንብ ይጠቀምበታል:: የአጭር ጊዜ መብላላት እንጀራው ባለ ብዙ አይን እና በመጠኑ ቆምጠጥ ያለ እንዲሆን ያደርገዋል::

ጤፍ የአለማችን ደቃቁ አዝዕርት ነው:: አንድ ፍሬ ስንዴን በክብደት ከጤፍ ጋር ለማመጣጠን 150 ፍሬ ያስፈልጋል

Gursha (feeding fellow diners by hand)

Ethiopians often hand feed their guests during dinner/lunch.
This is to show respect sometimes the person receiving the Gursha responds in kind and in turn feeds his feeder.


ጉርሻ

አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን በምሳ ወይም በእራት ጊዜ እንግዳቸውን በእጃጀው በማጉረስ ይመግባሉ::

ይህ የምናደርገው ለምናጎርሰው ሰው ያለንን ክብር ለመግለጽ ነው ፤ የተቀበለንም ግለሰብ መልሶ በማጉረስ ይገልጽልናል::

A Little Information on Teff

Teff is a grass indigenous to Ethiopia. Its seed can be cooked like a grain, or milled to make flour. Gluten-free, teff can be used as an alternative to the wheat flour used in baked goods. Teff comes in a variety of colours, including ivory, tan and dark reddish brown. It contains significant nutrition and makes a positive addition to any diet.

Teff grain is tiny. In fact, its name means “lost,” meaning if you drop it on the ground, it will be lost forever. Milling it at home is nearly impossible, so it is best to purchase it already ground. It has a mild flavour, with a molasses-like sweetness, that can enhance the texture and nutritional quality of baked goods. Teff is a grass, not a grain, and therefore is gluten free.

Teff provides nine times more iron than wheat and five times more calcium and potassium than cereal grains. A ¼-cup serving of the flour contains 113 calories and only 1g fat. Teff flour provides 4 g fibre per ¼ cup and 5 percent of the recommended dietary allowance for calcium and 13 percent for iron.


ስለጤፍ ትንሽ መረጃ

ጤፍ በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኝ የሳር አይነት ነው:: እንደሌሎቹ አዝዕርቶች በማዘጋጀት ወይም ተፈጭቶ ልንጠቀምበት እንችላለን:: ይህ ከ ግለተን ነጻ የሆነ አዝዕርት የስንዴ ዱቄትን ተክተን ለምንጋግራቸው ምግቦች ልንጠቀምበት እንችላለን:: ጤፍን በተለያየ ቀለም እናገኛዋለን ከነዚህም ውስጥ በነጭ፣ በሰርገኛ ና በቡናማ መልክ እናገኘዋለን:: በንጥረ ነገር የበለጸገ ከመሆኑ አንጻር ከማንኛውም ምግብ ጥሩ ነው::

ጤፍ እጅግ ደቃቃ ከመሆኑ አንጻር የስሙ ትርጉም እንኳ ጠፊ ማለት ነው ምክንያቱም አንዴ መሬት ከወደቀ መቼም አይገኝምና:: ቤት ውስጥ መፍጨት ምንም የማይታሰብ ነው፤ ጣዕምናው ልክ እንደ ሞላሰስ ስለሆነ በውስጡ ያለው በንጥረ ነገር የበለጸገ ባህሪውንና በሚጋገረው ነገር ላይ ያለውን ይዘት እንደጠበቀ ለመያዝ ያገለግላል:: ጤፍ አዝዕርት ነው ለማለት ያስቸግራል ከዛ ይልቅ የሳር ባህሪ ያለው ከግለተን ነጻ የሆነ ዝርያ ነው::

ጤፍ በብረት ንጥረ ነገር ይዘቱ ከ ስንዴ ዘጠኝ እጥፍ ያለው ሲሆን ከጥራጥሬወች ደግሞ አምስት እጥፍ የበለጠ የካልሲየም እና የፖታሲየም ይዘት አለው:: የአንድ ሩብ ኩባያ ዱቄት 113 ካሎሪ የምናገኝ ሲሆን የፋት ይዘቱ ግን 1ግራም ብቻ ነው:: ከሩብ ኩባያ የጤፍ ዱቄት 4ግራም ፋይበር ስናገኝ በሳይንስ ከሚመከረው የካልሲየም ይዘት 5 ፐርሰንት ሲሰጠን ከብረት ይዘት ደግሞ 13 ፐርሰንቱን ይሰጠናል::