Italian food: The food of Italy – የጣሊያን ምግብ

Italian food: The food of Italy – የጣሊያን ምግብ

የጣሊያን ምግብ ከፒዛ እና ስፓጌቲ የበለጠ ነው፡፡ በቤትዎ ሊሞክሯቸው የሚችሏቸው ሰፊ መጠን ያላቸው ይዘቶች፣ ቃናዎች እና ምግቦች አሉ፡፡ የጣሊያን ምግብ (የኢጣሊያ፡ ኩቺና ኢታሊያና [kuˈtʃiːna itaˈljaːna]) ስራቸው ወደ ድሮ ዘመን የተዘረጋ በክፍለ ዘመናት ውስጥ በማህበረሰብ እና ፖለቲካ ለውጦች ያደገ ነው፡፡

የጣሊያን ምግብ የሚታወቀው በቀላልነቱ፣ ከአራት እስከ ስምንት ባሉ ይዘቶች ብዙ አይነት ምግቦች መኖራቸው ነው፡፡ የጣሊያን ምግብ በአብዛኛው መሰረት ያደረገው በይዘቱ ጥራት እንጂ በሰፊ አዘገጃጀቱ አይደለም፡፡ ይዘቶቹ እና ምግቦቹ በክልል ይለያያሉ፡፡ ክልላዊ የነበሩ ብዙ ምግቦች ከነልዩነታቸው በሀገሪቷ በጠቅላላ ይሰራጫሉ፡፡

አይብ እና ወይን በብዙ ልዩነቶች እና ዲኖሚናዚዮን ዲ ኦሪጂኔ (DOC) (ቁጥጥር ያለው ስም) ህጎች የምግቡ ዋና ክፍል ናቸው፡፡  ሲሆን ቡና በተለይ ስፕሪሶ በጣሊያን ምግብ ውስጥ አስፈላጊ ሆኖ መጥቷል፡፡

በክፍለዘመናት ውስጥ የጣሊያን ምግቦች አድገዋል፡፡ ምንም እንኳን ጣሊያን ተብላ የምትታወቀው ሀገር እስከ 19 ክፍለ ዘመን ያልተዋሀደች ቢሆንም ምግቦቹ ከክርስቶስ ልደት በፊት እስከ አራተኛው ክፍለዘመን ድረስ ወደ ኋላ መታወቅ ሊገባቸው የሚችሉ መነሻዎች ያላቸው ናቸው፡፡ በክፍለዘመናት ውስጥ ቢሆንም ተጎራባች ክልሎች፣ ቅኝ ገዢዎች፣ ከፍተኛ ዕውቀት ያላቸው የምግብ አዘጋጆች፣ የፖለቲካ ሁከት እና የአዲሲቷ ዓለም ግኝት ለምግቦቹ ዕድገት ተፅዕኖ አሳድረዋል፡፡ ከሮማን ኢምፓየር መውደቅ በኋላ የተለያዩ ከተማዎች መለያየት ሲጀምሩ እና የራሳቸውን ባህሎች ሲተገብሩ የጣሊያን ምግብ የራሱን ቅርፅ መያዝ ጀመረ፡፡ በጣም ብዙ የተለያዩ አይነት ዳቦ እና ፓስታ መሰራት የጀመሩ ሲሆን የአበሳሰል መንገዶቹ እና አዘገጃጀቶቹ የተለያዩ ነበሩ፡፡ ሀገሪቷ ተከፋፍላ ነበር፡፡ ለምሳሌ፣ የሰሜን ጣሊያን (ሚላን) በሪሶቶዎቿ ስትታወቅ የሀገሪቷ መሀከለኛ ከተማ (ቦሎኛ) በቶርቴሊኒ የምትታወቅ እና የደቡቧ (ኔፕልስ) በፒዛዎቿ ትታወቃለች፡፡

እያንዳንዱ ቦታ የራሱ የሆነ መለያ በዋናነት በክልል ደረጃ እንዲሁም በአውራጃ ደረጃ አለው፡፡ ልዩነቶቹ ሊመጡ የሚችሉት ክልሉ ወደ ባህር ወይም ተራራ የተጠጋ ቢሆንም ድንበር አካባቢ ካሉት ሀገሮች (ለምሳሌ ፈረንሳይ እና ኦስትሪያ) እና ምጣኔ ሀብቶች ነው፡፡ የጣሊያን ምግብ ወቅታዊ ሲሆን ቅድሚያ የሚሰጠውም በትኩስነቱ ተሰርቶ ጥቅም ላይ የሚውለው ነው፡፡

በእውነቱ ከሆነ ምግብ በጣሊያን ባህል ውስጥ መሰረታዊ ከሆኑት ውስጥ አንዱ ሲሆን ምንም እንኳን ጊዜያቶች ቢለዋወጡ እና ህይወት በጣም በጣም አስቸጋሪ ቢሆንም ጣሊያኖች ደስታን የሚያገኙት በቤት ወይም በምግብ ቤት ውስጥ በጠረጴዛ ዙርያ በመቀመጥ በጋራ ጥሩ ምግብ ተካፍለው ሲመገቡ ነው፡፡ በጣሊያን ህዝብ ይህ የሆነበት ምክንያት የጣሊያን ምግብ እና ወይን የባህላቸው ክፍል ሲሆኑ አንዳንድ ጊዜም የቤተሰባቸው ታሪክም ናቸው፡፡ እያንዳንዱ ጣሊያናዊ ስለ ቤተሰቡ የተለየ ምግብ የአበሳሰል መንገድ ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ የቆየውን የምግብ አዘገጃጀት መመመርያን በመጠቀም ሊነግርዎት ይችላል፡፡ በሌላው ዓለምም ይህ የተለመደ ቢሆን በጣሊያን ውስጥ በእውነት ጥልቅ ጠቀሜታ አለው፡፡ ይህ ጣሊያኖች አዲስ ምግቦች ማግኘትን ወይም የተለመዱ ምግቦችን በአዲስ መንገድ ማዘጋጀትን አይደሰቱበትም ማለት ሳይሆን ምናልባት ከተለያዩ ወይኖች ጋር በማጣጣም፣ ይህም እንደገና ምን ያህል የጣልያን ምግብ እና ወይን ለጣልያን ህዝብ በእያንዳንዱ ህይወታቸው ውስጥ እንዴት አስፈላጊ እንደሆኑ ምልክት ነው፡፡

በመቶዎች የሚቆጠሩ የፓስታ ቅርፆች እና አብረዋቸው ከሚሄዱ ብዙ ስልሶች፣ ፒዛ በሁሉም መጠኖች እና ማለቂያ በሌለው ከላዩ ላይ በሚደረገው ክሬም፣ የጣሊያን ምግብ አስደናቂ ነው፡፡

የጣሊያን አይብን እንዳንረሳው፣ በጣም ብዙ ብዙ እና ሁሉም ጣፋጮች ናቸው፡፡

ትኩስ አሳ፣ ያስታውሱ ጣሊያን ግዙፍ የባህር ዳርቻዎች ያሏት በመሆኑ የአሳ ምግቦች ክምችት አላት፡፡

ጣሊያን በሳላሚ እና ሌሎች የታሸጉ ስጋዎች በአለም በጣም ታዋቂ እና ምርጥ ናት፡፡ የበግ ስጋ፣ የአሳማ ስጋ (ምንም እንኳን እኛ ኢትዮጵያውያን ይህን የማንመገብ ቢሆንም)፣ የበሬ ስጋ እና የዶሮ ስጋ ምግቦች በምግብ ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ ናቸው፡፡

የወይራ ዘይት እና ወይራዎች የጣሊያን ምልክቶች፣ ጤናማ እና በብዛት በጥቅም ላይ የሚውሉ ሲሆኑ ጣሊያኖች የወይራ ዘይትን በጣም በከፍተኛ ሁኔታ የሚወዷቸው እና የሚወስዷቸው ናቸው፡፡

የጣሊያን ምግብ ፓስታ እና ፒዛ ብቻ ሳይሆኑ በጣም ሰፊ እና በእውነትም አስደናቂ መሆናቸውን እንዳንረሳ፡፡

ጥቂት የኛን የጣሊያኖች የምግብ ዝግጅት መመርያዎች የአማርኛ ቪዲዮ ይመልከቱ፡፡

ethiopian-food-recipes-italian-food-blog-amharic-pasta-pizza-salad


Italian food is more than just pizza and spaghetti. There’s a wide range of ingredients, flavors, and dishes to experiment with in your own home.

Italian cuisine (Italian: cucina italiana [kuˈtʃiːna itaˈljaːna]) has developed through centuries of social and political changes, with roots stretching to antiquity.

Italian cuisine is characterized by its simplicity, with many dishes having only four to eight ingredients. Italian cooks rely chiefly on the quality of the ingredients rather than on elaborate preparation. Ingredients and dishes vary by region. Many dishes that were once regional, however, have proliferated with variations throughout the country.

Cheese and wine are a major part of the cuisine, with many variations and Denominazione di origine controllata (DOC) (regulated appellation) laws. Coffee, specifically espresso, has become important in Italian cuisine.

Italian cuisine has developed over the centuries. Although the country known as Italy did not unite until the 19th century, the cuisine can claim traceable roots as far back as the 4th century BCE. Through the centuries, neighbouring regions, conquerors, high-profile chefs, political upheaval and the discovery of the New World have influenced its development. Italian food started to form after the fall of the Roman Empire, when different cities began to separate and form their own traditions. Many different types of bread and pasta were made, and there was a variation in cooking techniques and preparation. The country was split. For example, the North of Italy (Milan) is known for its risottos, the central/middle of the country (Bologna) is known for its tortellini and the South (Naples) is famous for its pizzas.

Each area has its own specialties, primarily at a regional level, but also at provincial level. The differences can come from a bordering country (such as France or Austria), whether a region is close to the sea or the mountains, and economics. Italian cuisine is also seasonal with priority placed on the use of fresh produce.

In truth, food is one of the cornerstones of Italian culture and even if times are changing and life is more and more frenetic, Italians still find a great pleasure in sitting at a table, at home or  at the restaurant, and share a good meal together: this is because to the people of Italy, Italian food and wine are part of their culture and, very often, also of their own family history. Each Italian will tell you about their family way to cook a specific dish, using recipes often passed on through generations. If this is somehow common also in the rest of the world, in Italy it truly has a deeper significance. This, however, doesn’t mean that Italians don’t enjoy discovering new foods or new ways of preparing familiar dishes, maybe matching them with a different wine: this is, once again, a sign of how much Italian food and wine mean to the people of Italy, how important they are in their everyday life.

With hundreds of pasta shapes and as many sauces to go with them, Pizza in all sizes and a endless amount of topping, Italian food is just wonderful.

Let us not forget Italian cheese, there are so many many and all are totally delicious.

Fresh fish, remember Italy has a huge coastline, so there are loads of fish dishes. Salami and other cured meats, Italy has probably the most famous and best in the world. Lamb, Pork (even though us Ethiopian do not eat this), Beef and Chicken dishes are also high up on the menu.

Olive oil and olives are are a Italian Icon, healthy and used a lot, Italian love and take olive oil very seriously.

So do not forget the food of Italian is not just Pasta and Pizza but is very diverse and of course truly wonderful.

ethiopian-italian-food-blog-amharic-salad-pizza-pasta

Take a look at some of our Italian video recipes in Amharic.

ፒዛ – Easy Snack Pizza Recipe – Amharic – የአማርኛ የምግብ ዝግጅት መምሪያ ገፅ

ስፒናት ፓስታ – Spinach Pasta Recipe – የአማርኛ የምግብ ዝግጅት መምሪያ ገፅ

LASAGNE – Lasagna – ላዛኛ – Amharic የአማርኛ የምግብ ዝግጅት መምሪያ ገፅ

የነጭ ሽንኩርት ዳቦ – Garlic Bread – Amharic – የአማርኛ የምግብ ዝግጅት መምሪያ ገፅ

እንቁላል ፓስታ ሰላጣ – Egg Pasta Salad – Amharic – የአማርኛ የምግብ ዝግጅት መምሪያ ገፅ

ፓስታ ማብሰል እንዴት ነው – Amharic Recipes – የአማርኛ የምግብ ዝግጅት መምሪያ ገፅ

የዶሮ ፓስታ ሰላጣ – Amharic Food Recipes – የአማርኛ የምግብ ዝግጅት መምሪያ ገፅ

የዶሮ ክሬም ፓስታ – Amharic Recipes – የአማርኛ የምግብ ዝግጅት መምሪያ ገፅ

Zucchini Pasta Amharic Recipe – የአማርኛ የምግብ ዝግጅት መምሪያ ገፅ – Courgette Kusa

የጣልያን ስፓጌቲ ቦሎኝዝ – SPAGHETTI BOLONGSE – Amharic

Recent Posts