Mexican food – የሜክሲኮ ምግብ

Mexican food – የሜክሲኮ ምግብ

የሜክሲካኖች ምግብ ቅመማ ቅመም ያለበት ሲሆን የሚያስደስት እና በቃና የተሞላ ነው፡፡ የአሜሪካን ቴክስ ሜክስ የፈጣን ምግብ ቦታዎች፣ በእርግጥ ብዙ ቢሆኑም፣ በሜክሲኮ ውስጥ በትክክል የሚበላውን የሚወክሉ አይደሉም፡፡ ስለ ሜክሲካኖች ምግብ ጥቂት መረጃ ከዚህ በታች ቀርበዋል፡፡

ለአንድ ሺህ አመታት በሜክሲካኖች አመጋገብ ውስጥ በቆሎ መሰረታዊ ነገር ነው፡፡ በሁሉም አይነት ምግብ ውስጥ ሊገኝ የሚችል ሲሆን በተለምዶ በቶርቲላ (በሚጋገር ዳቦ) መልክ ይሰራል፡፡ አጥጋቢ የበቆሎ ወጥ የሆነውን ፖዞልን ለመስራት በቆሎ ሊቀቀል ይችላል፡፡ ቲማቲሞች፣ ቶማቲሎስ (አረንጓዴ ቲማቲሞች)፣ ዱባ፣ ስኳር ድንች፣ አቮካዶ፣ ማንጎ፣ አናናስ፣ ፓፓያ እና ኖፓልስ (እሾሀማው የቁልቋል ፍሬ) የታወቁ ፍራፍሬዎች እና አትክልቶች ናቸው፡፡ የበሬ ስጋን የሚጠቀሙ ቢሆንም የዶሮ እና የአሳማ ስጋ የተለመዱ ናቸው፡፡ የቃርያ ዝርያዎች የሚያካትቱት በሰፊው የሚታወቀው ጃላፔኖ፣ እንደዚሁም ደግሞ ፖብላኖ፣ ሴራኖ እና ቺፖትል ናቸው፡፡ ቃርያዎች ለሜክሲካኖች ምግብ የተለየ ቃና የሚሰጡ ሲሆን ብዙውን ጊዜ የበለጠ የሚሆነውም እንደ ድምብላል እና ጦስኝ ባሉ ተክሎች እና እንስላል፣ ቀረፋ እና ቁሩንፉድ ባሉ ቅመሞች ነው፡፡ አይብ እና እንቁላሎችም በምግብ ዙርያ የሚቀርቡ ናቸው፡፡ የባህር ምግቦች በብዛት በባህር ዳርቻ ምግቦች ውስጥ የተለመዱ ናቸው፡፡

የሜክሲካኖች ምግብ በሀገር በቀል (የህንዶች) እና በስፔን ተፅዕኖዎች የተደባለቀ ቢሆንም ብዙ ሜክሲካኖች የሀገር በቀል የሆኑት ምግቦችን እንደ በቆሎ፣ ባቄላዎች እና ቃርያዎችን መመገብ ቀጥለዋል፡፡ እነዚህ ምግቦች ርካሽ እና በሰፊው የሚገኙ ናቸው፡፡ ዳቦዎች እና ኬኮች የሚሸጡ ቢሆንም ለዋና ምግባቸው መሰረታዊ የሆነው በቤት የሚጋገረው ወይም የሚገዛው ቶርቲላ በየቀኑ በቶርቲሌራ (በቶርቲላ መሸጫ) ይገኛል፡፡ የቶርቲላዎች ዱቄት በተለይ በሰሜን ሜክሲኮ የሚበሉ ሲሆን የበቆሎ ዘር ግን በጣም ይታወቃል፡፡

ቶርቲላዎች

የትክክለኛ ሜክሲካኖች ትውልዶች የዘወትር ምግቦች፣ ቶርቲላዎች ከዱቄት (በሰሜን በጣም በተለመደው) ወይም ከበቆሎ (በባህላዊ መንገድ የሆነ እና በደቡብ እጅግ በጣም በተለመደው) ሊሰራ ይችላል፡፡ እንደ ዳቦ ከምግብ ጋር ጎን ለጎን የሚቀርቡት ቶርቲላዎች በብዙ ዋና ምግቦች ውስጥም ተጠቅልሎ እና ተጋግሮ ለኢንቺላዳሶች፣ ተጠብሰው ለታኮዎች  ወይም ተጠብሰው ለኴሳዲላሶች ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡

ፍሪጆሎች (ባቄላዎች)

ጥሩ የፕሮቲን ምንጭ የሆኑት የተለያዩ አይነት የባቄላዎች ዝርያዎች ብዙውን ጊዜ ይቀቀሉ እና ይጠበሳሉ፡፡ በምግብ ወይም በሚያምር መልኩ በተዘጋጀው ውስጥ ዋና ይዘት ሊሆኑ ይችላል፡፡

ቃርያዎች

በአጠቃላይ ቃርያው ትልቅ ከሆነ ቃናው አነስ ይላል፡፡ ትልቅ የፖብላኖ ቃርያዎች እንደ ዋና ምግብ ተሞልተው ቢቀርቡ ትንሹ ሀባኔሮ በአደገኛ ሁኔታ ያቃጥላል፡፡ምግቡ ቅመም ያለበት መሆኑን ለመጠየቅ “ኤስ ፒካንቴ?”ይበሉ – የሆቴል የምግብ ዝርዝሮች አንዳንድ ጊዜ የቱሪስት የምግብ ፍላጎት ሊዘጋ የሚችል ምግቦችን ይገልፃሉ፡፡

ጓካሞል

አቮካዶ ከሽንኩርቶች፣ ከቃርያዎች እና ከድምብላል ጋር ይፈጫል፡፡ በሚያምር መልኩ ለማጥቀሻ ይቀርባል፡፡

ሳልሳ

ምንም እንኳን የቲማቲሞች፣ የሽንኩርት፣ የቃርያ እና የድምብላል ቀይ ወይም አረንጓዴ ድብልቅ ጋር ብዙውን ጊዜ የተያያዘ እና በምግ ጠረጴዛ በሚያምር መልኩ እንደ ማጥቀሻ ቢቀርብም ሳልሳ በትክክል ወጥ ነው፡፡ በደህና ጠርሙሶች ውስጥ  እንደ ትንሽ የካችአፕ መያዣዎች ያሉትን “ሳልሳ ሃባኔሮ” በማስተዋል እና መጀመርያ ለጥንቃቄ ትንሽ ሳልሳ ሁልጊዜ ይሞክሩ፡፡

ተኩይላ

ይህ የማይታወቅ ከባድ ምግብ ብዙውን ጊዜ ማርጋሪታ በጨው በተሞላ ብርጭቆዎች ውስጥ ከሎሚ ጭማቂ ጋር በመደባለቅ፣ ለቱሪስቶች ይቀርባል፡፡ በሜዳዎች ላይ በቅሎ ከሚታየው እሾሀማው ቁጥቋጦ ከሆነው ማጔይ ተክል በትክክል የተወሰደ ነው፡፡ መዝካል አደገኛው የተኩይላ አይነት ሲሆን በጠርሙስ ውስጥ ካለ ትል ጋር በባህላዊ መንገድ የሚቀርብ ነው፡፡ ጠርሙስ ውስጥ ያለው ሲያልቅ ትሉ መበላት አለበት፡፡

ቼርቬዛ

የሜክሲካኖች ቢራዎች አሁን በአለም ላይ ይታወቃሉ፡፡ ኮሮና፣ ሶል፣ እና ዶስ ኢኵስ የተለመዱ ብራንዶች ሲሆኑ የተለመዱት በቀዝቃዛነታቸው  ሲጠጡ እና በጣም የሚያድሱ ለበረዶ መጠጦች ጥሩ አማራጮች ናቸው፡፡

ቼቪቼ

ጥሬ አሳ በሎሚ ጭማቂ ውስጥ ብዙውን ጊዜ በተቆራራጠ ሳላድ ውስጥ ይቆያል፡፡

የቃርያዎች ሬኔሎስ

ትላልቅ የፓብላኖ ቃርያዎች በአይብ ወይም በተቀመመ ስጋ (ፒካዲሎ) ይቀርባሉ፡፡ ወጡ ሊሆን ባይችልም ቃርያዎቹ አነስተኛ ናቸው፡፡

ኢንቺላዳስ

በአትክልቶች፣ በዶሮ ስጋ ወይም በአሳማ ስጋ በተሞሉ በቲማቲም እና ቃርያ የተቀቡ ቶርቲላዎች ከዚያም የሚጠቀለሉ እና የሚጋገሩ ናቸው፡፡ እንደ ቃርያው ይዘት ሳይሆን ኢንቺላዳስ ብዙም አቃጣይ አይደለም፡፡ ኢንቺላዳስ ሱይዛስ እላዩ ላይ ኮምጣጣ ክሬም ይደረጋል፡፡

ኋቺናንጎ

በባህር ዳርቻ ምግብ ቤቶች የምግብ ዝርዝሮች ላይ በተለመደ ሁኔታ የሚቀርብ ቀይ አሳ ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ በተመረጡ ዘዴዎች የሚቀቀል “አል አጉስቶ” ይገኛል፡፡

ኴሳዲላስ

በአይብ የተሞሉ ቶርቲላዎች የተጠቀለሉ እና የተጠበሱ ናቸው፡፡ ከባቄላዎች ወይም ጥቂት ሳላድ ጋር የሚቀርብ ቀላል ምግብ ሲሆን ማንኛውንም ቅመም ለመካለከል ምቹ ነው፡፡

የሞል ወጥ

በቸኮሌት፣ ቃርያዎች እና ብዙ ቅመሞች ባልተለመደ ስብጥር የተሰራ በአስደናቂ ወጥ የተሞላ ነው፡፡  በይዘቶቹ በመመርኮዝ ቀይ ወይም አረንጓዴ ሊሆን የሚችል ሲሆን ፕዌብላ እና ኦክሳካ ሞሎች በተለየ ሁኔታ የታወቁ እና “የፖብላኖ ሞል” ወይም “የኦክሳኬኖ ሞል” ይባላሉ፡፡ ምንም እንኳን የተርኪ ስጋ ብዙ ባህላዊ ቢሆንም ወጡ ብዙውን ጊዜ በዶሮ ስጋ ላይ የሚቀርብ ነው፡፡

የፒፒያን ወጥ

የኦክሳካ ሌላኛው አይነት ፒፒያን  ወጥ አረንጓዴ እና የሚሰራውም ከዱባ ዘሮች ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ  የሚቀርበውም በዶሮ ስጋ ላይ ነው፡፡

ፖክ ቹክ

የዩካትካን ሌላኛው አይነት ሲሆን የአሳማ ስጋ ፊሊቶ ከቲማቲሞች፣ ሽንኩርቶች እና ቅመሞች ጋር በማብሰል ይዘጋጃል፡፡

ፖሎ ፒቢል

የዩካትካን ሌላኛው አይነት ሲሆን ብዙውን ጊዜ ከዚህ ክልል ውጭ አይገኝም፡፡ የዶሮ ስጋ በብርቱካን እና ቅመም ውስጥ የቆየ እና በሙዝ ቅጠሎች ውስጥ የተጠበሱትን የያዘ ነው፡፡

ታኮስ

ቶርቲላዎች እስኪደርቁ ድረስ በመጥበስ ከተለያዩ ማባያዎች ጋር ማቅረብ ነው፡፡

ታማልስ

የበቆሎ ምግብ በበቆሎ ወይም በሙዝ ሽልቃቂዎች ተጣብቀው የተጠቀለሉ ሲሆን ብዙውን ጊዜ በዶሮ ስጋ፣ በአሳማ ወይም ተርኪ (የቱርክ ዶሮዎች) እና/ወይም አትክልቶች ተሞልቶ ከዚያም ይቀቀላሉ፡፡

ቶርታስ

የሜክሲካኖች ሳንዲውቾች ብዙውን ጊዜ ትላልቅ ጥቅሎች ከጥሩ ማባያዎች ጋር፡፡

ቶስታዳስ

ቀጭን እና የደረቁ ቶርቲላዎች በጒካሞል፣ በሚኮመጥጥ ክሬም፣ በቃርያዎች፣ በዶሮ ስጋዎች እና በመሳሰሉት ተሞልቶ ይቀርባል፡፡

ethiopian-food-recipes-mexican-mexico-blog-injera-tortilla-addis-ababa


Mexican food is spicy, fun and full of flavour. American Texmex fast food places, which there are of course many, do not represent real food served in Mexico. Below is a just a little info on Mexican cuisine.

Corn is the basis of the Mexican diet, as it has been for thousands of years. It can be found in almost every meal, usually in the form of the tortilla (flatbread). Corn can also be boiled to produce pozole , a hearty corn stew. Popular fruits and vegetables are tomatoes, tomatillos (green tomatoes), squash, sweet potato, avocado, mango, pineapple, papaya, and nopales (from the prickly pear cactus). Though beef is consumed, chicken and pork are more common. The variety of chilies includes the widely known jalapeño, as well as the poblano , serrano , and chipotle . Chilies give Mexican cooking a distinctive flavor, which is often enhanced with herbs, such as cilantro and thyme, and spices, including cumin, cinnamon, and cloves. Cheese and eggs round out the diet. Seafood is most common in coastal dishes.

Though Mexican cuisine is a blend of indigenous (Indian) and Spanish influences, most Mexicans continue to eat more native foods, such as corn, beans, and peppers. Such foods are cheap and widely available. Bread and pastries are sold, but the tortilla, homemade or bought daily at the local tortillería (tortilla stand), is the basis of the typical meal. Flour tortillas are also eaten, especially in northern Mexico, but the corn variety is most popular.

Tortillas

The staple food of generations of ordinary Mexicans, tortillas can be made of flour (more common in the north) or maize (the traditional method and still the most common in the south). Often served alongside a meal as bread would be, tortillas are also used in many typical dishes – rolled and baked for enchiladas, fried for tacos or grilled for quesadillas.

Frijoles (beans)

A good source of protein, beans of different varieties are most commonly boiled and then fried. They can be a main ingredient in a meal or served almost as a garnish.

Chilies

In general, the bigger the chili, the milder the flavor. Large Poblano chilies are stuffed and served as a main course, the small habanero is ferociously hot. To ask if a dish is spicy, say “es picante?” – though hotel menus will often specify dishes that might offend tourist palates.

Guacamole

Avocado mashed with onions, chilies and cilantro (coriander). Served as a dip or as a garnish.

Salsa

A salsa is actually just a sauce, although it is most commonly associated with the red or green mix of tomatoes, onion, chili and cilantro (coriander) served on your table as a relish or a dip. Beware of “salsa habanero” in innocuous bottles like small jars of ketchup, and always try just a little salsa first as a precaution.

Tequila

This infamous spirit is most commonly served to tourists in the form of a margarita – mixed with lime juice in salt-rimmed glasses. It is actually derived from the maguey plant – a spiky bush often seen growing in fields. Mezcal is a cruder form of Tequila traditionally served with a worm in the bottle – the worm should be eaten when the bottle is finished!

Cerveza

Mexican beers are now known all over the world. Corona, Sol and Dos Equis are common brands, usually served cold and a very refreshing alternative to iced drinks.

Ceviche

Raw fish marinated in lime juice, often in a chopped salad.

Chiles Renellos

Large Poblano chilies stuffed with cheese or spicy meat (picadillo). The chilies are mild, though the sauce may not be.

Enchiladas

Tortillas coated in a tomato and chili sauce, stuffed with vegetables, chicken or pork then folded and baked. Despite the chili content, enchiladas are often fairly mild. Enchiladas suizas are topped with sour cream.

Huachinango

Red Snapper, a common feature on the menus at coastal resorts. Often available “al gusto”, cooked in a choice of methods.

Quesadillas

Tortillas stuffed with cheese, folded and grilled. A simple dish often served with beans or a little salad and suitable for those avoiding anything spicy.

Mole sauce

A wonderful rich sauce made with the unlikely combination of chocolate, chilies and many spices. It can be red or green depending on the ingredients and the moles of Puebla and Oaxaca are particularly famous, hence “mole poblano” or “mole oaxaqeno”. The sauce is often served over chicken, though turkey is more traditional.

Pipian sauce

Another of Oaxaca’s specialties, pipian sauce is green and made from pumpkin seeds. It is often served over chicken.

Poc Chuc

Another Yucatecan specialty, where pork fillet is cooked with tomatoes, onions and spices.

Pollo Pibil

A Yucatecan specialty, not often found outside this region. It traditionally consists of chicken marinated in orange and spices then barbecued in banana leaves.

Tacos

Tortillas fried until they are crispy and served with various fillings.

Tamales

Cornmeal paste wrapped in corn or banana husks and often stuffed with chicken, pork or turkey and/or vegetables, then steamed.

Tortas

Mexican sandwiches, often large rolls with generous fillings.

Tostadas

Thin and crisp tortillas served loaded with guacamole, sour cream, chilies, chicken etc.

ethiopian-mexican-amharic-food-blog-recipes-cooking

የሜክሲኮ ዶሮ እና ባቄላ – Amharic Recipes – የአማርኛ የምግብ ዝግጅት መምሪያ ገፅ

አቮካዶ ሰላጣ የሜክሲኮ – Amharic Recipes – የአማርኛ የምግብ ዝግጅት መምሪያ ገፅ

Recent Posts