The Natural Power of Turmeric – የእርድ የተፈጥሮ ሀይል

The Natural Power of Turmeric – የእርድ የተፈጥሮ ሀይል

እርድ የሚያቃጥል፣ ሞቃታማ እና መራራ ቃና እና በትንሹ ብርቱካን እና ዝንጅብል እንደሚሰጡት ለስለስ ያለ ሽታ ያለው ሲሆን ማጣፈጫን ለመስራት ከሚጠቅሙ በጣም ታዋቂ ቅመማቅመሞች አንዱ እና ለሰናፍጭ ነጣ ያለ ከለር የሚሰጥ ነው፡፡

እርድ ኩርኩማ ሎንጋ ከተባለው ተክል ስር የሚመጣ ሲሆን ጠንካራ ቡናማ ቆዳ እና ጥልቅ የሆነ ብርቱካናማ ስጋ ያለው ነው፡፡ እርድ በሁለቱም በቻይናውያን እና ህንዳውያን ለረጅም ጊዜ  የሰውነት መቆጣትን ለመከላከል የሚጠቀሙበት ሀይለኛ የህክምና ዘዴ ነ ው፡፡ እርድ በጥልቅ ቢጫ ብርቱካናማ ከለሩ እና ለመፈወሻ መፍትሔ እና ለጨርቃጨርቅ ማቅለሚያ እንደ ቅመም በታሪክ ሁሉ የሚጠቀሙበት ስለሆነ በተለምዶ “የህንድ ሳፍሮን” ይባል ነበር፡፡

ነጣ ያለ ቢጫማው የቅመም ቀስተደመና፣ እርድ (ኩርኩማ ሎንጋ) በቻይናውያን እና ህንዳውያን ለረጅም ጊዜ እንደ ህክምና ዘዴ የሚጠቀሙበት ሀይለኛ መድሀኒት ሲሆን የሰውነት መቆጣትን በመከላከል የተለያዩ ሰፊ ሁኔታዎችን እንደ እብጠት፣ የወፍ በሽታ፣ የወር አበባ ዑደት ችግሮችን፣ ደም ያለበት ሽንትን፣ ኪንታሮትን፣ የጥርስ ህመምን፣ የበለዘ አካልን፣ የደረት ህመምን እና የአንጀት ህመምን ለማከም የሚያግዝ ነው፡፡

አቅም ያለው ደህንነቱ የተጠበቀ የሰውነት መቆጣትን ተከላካይ

በተለያዩ የጥናት ማሳያዎች ውስጥ የሚተነው የእርድ የዘይት ክፍል ወሳኝ የሆነውን የሰውነት መቆጣትን የሚከላከል ስራዎችን ሰርቷል፡፡ ኩርኩሚን የተባለው የእርድ ቢጫ ወይም ብርቱካናማ ማቅለሚያ ከሚተነው ዘይት ይልቅ የተሻለ አቅም አለው፡፡ ኩርኩሚን በእርድ ውስጥ የመጀመርያው የመድሀኒት አጋዥ ተብሎ ይታሰባል፡፡ የኩርኩሚን የሰውነት መቆጣትን የመከላከል ውጤት አቅም ካላቸው ሀይድሮኮርቲሶን እና ፌናይልቡታዞን መድሀኒቶች እንደዚሁም ደግሞ ያለ ሀኪም ትዕዛዝ የሚወሰደውን የሰውነት መቆጣትን የሚከላከል አጋዥ መድሀኒት እንደ ሞትሪን ጋር እንደሚወዳደር በብዙ ጥናቶች ተመልክቷል፡፡ ከፍተኛ የመርዛማ ጉዳቶች (የቁስል መፈጠር፣ የነጭ የደም ህዋስ ቁጥር መቀነስ፣ የአንጀት መድማት)እንደተያያዙት መድሀኒቶች ሳይሆን ኩርኩሚን ምንም መርዛማነት የለውም፡፡

ለአንጀት በሽታ የሰውነት መቆጣት ውጤታማ ህክምና

የቅርብ ጥናት እንደጠቆመው ለአንጀት በሽታ የሰውነት መቆጣት (አይቢዲ) እንደ ክሮህንስ እና የኮሊቲስ ቁስለት ኩርኩሚን ርካሽ የሆነ፣ በቀላሉ ሊወሰድ የሚችል እና ውጤታማ ህክምና ሊሰጥ ይችላል፡፡ በዚህ ጥናት ውስጥ ኮሊቲስን የሚያነሳሳው ለሰውነት መቆጣት አጋዥ ለተሰጣቸው አይጦች ጥናቱ ከመገባደዱ 5 ቀን በፊት በምግባቸው ውስጥ ኩርኩሚን ሲጨመርበት ከችግሩ ተጠብቀዋል፡፡ ኩርኩሚን የተሰጣቸው አይጦች ካልተሰጣቸው እንስሳቶች አነስተኛ የሰውነት ክብደት የቀነሱ ብቻ ሳይሆን ተመራማሪዎች የአንጀታቸውን የህዋስ ስራ ሲያጣሩ ሁሉም የኮሊቲስ የተለዩ ምልክቶች (የዝልግልግ ፈሳሽ ቁስለት፣ የአንጀት ግድግዳ ውፍረት እና የሰውነት መቆጣት ህዋስ መስረግ) ቀንሰዋል፡፡ ኩርኩሚን የጥበቃውን ስራዎች እንዴት አድርጎ እንዳከናወነ ተመራማሪዎቹ እስከአሁን ድረስ በትክክል ባያረጋግጡም ጠቀሜታዎቹ የተገኙት በአንቲኦክሲዳንት ስራዎች ብቻ ሳይሆን ኤንኤፍ ካፓ የተባለውንና የህዋሳቶችን መቆጣት  አጋዥ እንዳይገባ የመከልከል ውጤት እንደሆነ ያስባሉ፡፡ በተጨማሪም በዚህ ጥናት ጥሩ ዜና ተብሎ የተገለፀው ምንም እንኳን ኩርኩሚን በብዙ መጠን ቢወሰድ ችግር የሌለው እንደሆነ የታወቀ ቢሆንም ይህ የእርድ ንጥረ ነገር  በትንሹም እስከ 0.25 በመቶ ይዘት ማለትም ለማጣፈጫው ቃናነት በቀላሉ ለማጣጣም የምንጨምረው የእርድ መጠን ውጤታማ ነበር፡፡

ለሪህ ህመም ማስታገሻ

የክሊኒካል ጥናት እንዳረጋገጠው ኩርኩሚን በጣም ከፍተኛ ሀይል ያለው የአንቲኦክሲዳንት ውጤታማነትን አስመዝግቧል፡፡ እንደ አንቲኦክሲዳንት ኩርኩሚን ቆሻሻ ነገሮችን ማለትም በሰውነታችን ውስጥ በመጓዝ የጤናማ ህዋሶች እና የህዋሰ መሸፈኛዎችን ከፍተኛ ጉዳት እንዲደርስ ምክንት የሚሆኑትን ኬሚካሎችን ሊያስወግድ ይችላል፡፡ እንደ ሪህ ማለትም ቆሻሻ ነገሮች የመገጣጠሚያ ቦታ መቆጣት ህመም እና ለመገጣጠሚያ ጉዳቶች ምክንያት ሲሆኑ ይህ ለብዙ በሽታዎች አስፈላጊ ነው፡፡ የእርድ የአንቲኦክሲዳንት እና የሰውነት መቆጣት መከላከያ ውጤቶች ድብልቅ ለምን ብዙ ሰዎች ለመገጣጠሚያ በሽታቸው ቅመሙን በመደበኛነት ሲጠቀሙ እረፍት እንደሚያገኙ ያስረዳል፡፡ በሪህ ህመም በሽተኞች ላይ በተካሄደ የቅርብ ጊዜ ጥናት ኩርኩሚን ከፌናይልቡታዞን ጋር በመወዳደር የአጭር ጊዜ የጠዋት ጥንካሬን በማምጣት፣ የመራመጂያ ጊዜ በማስረዘም እና የመገጣጠሚያ እብጠት በመቀነስ ተመጣጣኝ መሻሻሎች አከናውኗል፡፡

ለሲስቲክ ፋይብሮሲስ በሽተኞች ይጠቅማል

በ(ሚያዝያ 2004) በሳይንስ ውስጥ የታተመው የእንስሳት ጥናት እንደሚጠቁመው በእርድ ውስጥ የሚገኘው ዋነኛው እና ቢጫ ከለር የሚሰጠው ኩርኩሚን ቅመም በጣም በተለመደ ሁኔታ የጀነቲክ ችግርን የሚገልፀውን እና ለሲስቲክ ፋይብሮሲስ መፈጠር ምክንያት የሆነውን ሊያስተካክል ይችላል፡፡ ሲስቲክ ፋይብሮሲስ በወፍራም ዝልግልግ ፈሳሽ ሳምባዎችን የሚያጠቃ፣ ህይወትን አደጋ ላይ የሚጥል እና 30,000 አሜሪካውያን ልጆች እና አዳጊ ወጣቶችን እንዲሁም ዕድሜያቸው ከ 30 በላይ ከሆነ ሊዳን የማይቻልበት ገዳይ በሽታ ነው፡፡ ዝልግልግ ፈሳሹ ጣፊያን የሚጎዳ በመሆኑ የሰውነትን ንጥረነገሮች የመሳብ እና የመፍጨት ችሎታን ያዛባል፡፡

ሲስቲክ ፋይብሮሲስ የሚከሰተው በጂን ውስጥ ፕሮቲንን ኮድ በሚያደርገው (ትራንስሜምብራንስ ኮንዳክታንስ ሬጉሌተር ወይም ሲቲኤፍአር) ጂን ለውጥ ምክንያት መሆኑን ተመራማሪዎች አሁን አውቀውታል፡፡ የሲቲኤፍአር ፕሮቲን ወደ ህዋሶች ገፅ ላይ እንዲጓዝ እና ክሎራይድ አየኖች ህዋሱን የሚለቁበት ቦይ የመፍጠር ስራ ያከናውናል፡፡ ልክ ባልሆነ ጂን ምክንያት ፕሮቲኑን የተሳሳተ ቅርፅ ሲይዝ ይህ ሊሆን ስለማይችል ክሎራይድ በህዋስ ውስጥ ስለሚከማች ዝልግልግ ፈሳሽ እንዲመረት ያደርጋል፡፡

ዴልታኤፍ508 የሚባለው በጣም የተለመደው የጂን ለውጥ ልክ ያልሆነ ፕሮቲን እንዲመረት ያደርጋል፡፡ ክብደትን መሰረት ያደረገ የኩርኩሚን መጠን የዴልታኤፍ508 ችግር ላለባቸው አይጦች ተሰጥቷቸው የነበረው በሰዎች በደንብ ሊሰራ የሚችል ሲሆን ኩርኩሚን ችግሩን በማስተካከል ዴልታኤፍ508 ፕሮቲን ትክክለኛ ገፅታ እንዲኖረው እና ስራውን እንዲያከናውን ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም ኩርኩሚንን ያጠናው የያሌ ሳይንቲስት እንዳመለከተው ኩርኩሚን የካልሺየም መለቀቅን በመከላከል በካልሺየም ቦዮች በኩል ጂኑ የተለወጠው ሲቲኤፍአር ከህዋሶቹ እንዲለቅ የሚያደርግ ሲሆን በክሎራድ መሪነት የሚከማቸውን ዝልግልግ ፈሳሽ እንዲቆም ይረዳል፡፡ በሲስቲክ ፋይብሮሲስ ህክምና ዘርፍ ያሉት ስፔሻሊስቶች በሲስቲክ ፋይብሮሲስ ታካሚዎች የተወሰዱት ብዙ በሀኪም የታዘዙ መድሀኒቶች ላይ ትክክለኛው መጠን እስኪታወቅ እና ማንኛውም የጎንዮሽ ጉዳቶች እስኪለዩ ድረስ ታካሚዎች ኩርኩሚንን በያዙ ተጨማሪ ምግቦች ራሳቸውን እንዳያክሙ አስጠንቅቀዋል፡፡

ካንሰርን ይከላከላል

የኩርኩሚን አንቲኦክሲደንት ስራዎች ከፍተኛ ጠቀሜታ ካለው በተለይም በአንጀት ውስጥ በግምት በየሶስት ቀናት ፈጣን የህዋስ መጥፋት በሚኖርበት የህዋሳቶች ዲኤንኤን ሊያጠፉ ከሚችሉ ቆሻሻ ነገሮች የአንጀት ህዋሶችን ለመጠበቅ ያስችለዋል፡፡ በተደጋጋሚ መተካካቶች ምክንያት በአንጀት ህዋሶች ዲኤንኤ ውስጥ የሚኖረው የጂን ለውጥ የካንሰር ህዋሶች በፍጥነት እንዲፈጠሩ ሊያደርግ ይችላል፡፡ ኩርኩሚን ሰውነታችን የጂን ለውጥ ያለባቸውን የካንሰር ህዋሶችን እንዲያጠፋ ስለሚረዳ የበለጠ ጉዳት ሳያደርሱ በሰውነት ውስጥ እንዳይሰራጩ ያደርጋል፡፡ ኩርኩሚን ይህን የሚያደርግበት የመጀመርያው መንገድ የጉበትን ስራዎች በማሻሻል ነው፡፡ በተጨማሪም ከካንሰር መፈጠር የሚከላከልበት ሌሎች የተጠቆሙ መንገዶች የሚያካትቱት ለእጢ መፈጠር አስፈላጊ ተብለው የታሰቡትን የፕሮቲን መዋሀድን መከልከል እና ለካንሰር ህዋስ እድገት አስፈላጊ የሆነውን ተጨማሪ የደም አቅርቦትን በመከልከል ናቸው፡፡

የካንሰር ህዋስ እድገትን እና ሜታስቴሲስን ይከላከላል

የጡት፣ የወንድ አባላዘር፣ የሳምባ እና የአንጀት ካንሰርን ለመቀነስ የተላላፊ በሽታዎች ጥናት በተደጋጋሚ እርድን ከመጠቀም ጋር  የተያያዘ ሲሆን የላቦራቶሪ ሙከራዎች እንደሚያሳዩት ኩርኩሚን ዕጢዎች እንዳይፈጠሩ ሊከላከሉ ይችላሉ፤ እንዲሁም በቴክሳስ ዩኒቨርስቲ የተካሄደው ጥናት እንደሚጠቁመው በአይጦች ውስጥ የጡት ካንሰር ቢኖር እንኳን ኩርኩሚን ወደ ወደ ሳምባዎች የሚሰራጨውን የጡት ካንሰር ህዋስ መቀነስ እንዲችል ይረዳል፡፡

በ(መስከረም 2005) በባዮኬሚካል ፋርማኮሎጂ በታተመው በዚህ ጥናት ውስጥ የሰው ልጅ የጡት ካንሰር ህዋሶች ወደ አይጦች የተጨመረ ሲሆን ጡትን በቀዶ ጥገና ከሚወጣው ጋር ለማመሳሰል የተፈጠሩትን ዕጢዎች እንዲወጡ ተደርጓል፡፡

ከዚያም አይጦቹ በአራት ቡድኖች ተከፋፍለዋል፡፡ አንዱ ቡድን ምንም አይነት ተጨማሪ ነገር ሳይደረግበት እንደ መቆጣጠርያ አገልግሏል፡፡ ሁለተኛው ቡድን ፓክሊታክስል (ታክሶል) የካንሰር መድሀኒት የተሰጠው ሲሆን ሶስተኛው ቡድን ኩርኩሚን እና አራተኛው ቡድን ሁለቱም ታክሶል እና ኩርኩሚን ተሰጥቶታል፡፡

ከአምስት ሳምንት በኋላ በኩርኩሚን ብቻ ባለው ቡድን ውስጥ ያሉት ግማሽ የሚሆኑት አይጦች እንዲሁም ከኩርኩሚን እና ታክሶል ምድብ 22% የሚሆነው ወደ ሳምባዎች የተሰራጩ የጡት ካንሰር ማስረጃ ነበሩ፡፡

ነገር ግን ታክሶል ብቻ ካገኙት አይጦች 75% የሚሆኑት እና ከመቆጣጠርያው ምድብ 95% የሚሆነው የሳምባ ዕጢዎችን ሰርተዋል፡፡

ኩርኩሚን እንዴት ረድቶ ነበር? የተመራማሪዎች መሪ ብሀራት አግዋል እንዳሉት ”ልክ እንደ ማብሪያ እና ማጥፊያ መቆጣጠርያ፤ ኩርኩሚን ከቅጂው ወሳኝ ጉዳዮች በተቃራኒው ነው የሚሰሩት”፡፡ ” ዕጢዎችን ለመፍጠር የሚያስፈልጉ ሁሉንም ጂኖች የሚቆጣጠሩት የቅጂው ወሳኝ ጉዳዮች ናቸው፡፡ ስናጠፋቸው የካንሰር ህዋሶችን እድገትና ወረራ ላይ የሚሳተፉትን አንዳንድ ጂኖችን እንዘጋቸዋለን፡፡”

በ(መስከረም 2005) በባዮኬሚካል ፋርማኮሎጂ በታተመው እና በሆጅኪን ሊምፎማ ህዋሶች ባልሆነ በሌላ በሰው ልጅ የላቦራቶሪ ጥናት የቴክሳስ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች እንዳመለከቱት ኩርኩሚን የካንሰር ህዋስ እድገትን የሚያፋጥኑ እንደ ቲኤንኤፍ፣ ሲኦኤክስ-2 እና አይ ኤል-6 አቅጣጫ ቀያሪ የሰውነት መቆጣትን የሚያመጡ ሞለኪዩሎችን ጂኖች እንዲሰሩ ምልክትን የሚሰጠው ኤንኤፍ-ካፓቢ ተቆጣጣሪ ሞለኪዩልን እንዳይሰራ ይከለክላል፡፡ በተጨማሪም ኩርኩሚን የካንሰር ህዋስ ስርጭትን የሚገታ እና በሳምባ ካንሰር ህዋስ ውስጥ የህዋስ ዑደትን በመቆጣጠር ህዋሶች ራሳቸውን እንዲገሉ ያደርጋል፡፡ በቴክሳስ ዩኒቨርስቲ የምዕራፍ I መጀመርያ የክሊኒካል ሙከራዎች አሁን የኩርኩሚንን ኬሚካላዊ የመከላከል እና በሽታን የመፈወስ ጥበብን ባህርያት ከብዙ የአጥንት ካንሰር እና የጣፊያ ካንሰር አንፃር እየተመለከቱት ሲሆን ሌሎች ተመራማሪ ቡድኖች የኩርኩሚንን የአፍ ካንሰር የመከላከል ብቃት እየተመራመሩ ነው፡፡

እርድ እና ሽንኩርቶች የትልቁ አንጀት ካንሰርን ለመከላከል ሊረዱ ይችላሉ

በክሊኒካል ጋስትሮኢንትሮሎጂ እና ሄፓቶሎጂ ጉዳይ ላይ በነሐሴ 2006 ውስጥ የታተመው ምርምር እንደሚያሳየው በማጣፈጫ የእርድ ቅመም ውስጥ የሚገኘው ኩርኩሚን ንጥረነገር እና በሽንኩርት ውስጥ የሚገኘው ኩዌርሲቲን አንቲኦክሲደንት በሰው ልጅ የአንጀት አካባቢ ውስጥ ከካንሰር በፊት ያሉትን ሁለቱንም የቁስሎችን መጠን እና ቁጥር ይቀንሳል፡፡

ፋሚሊያል አዴኖማቶስፖሊፖሲስ (ኤፍኤፒ) የተባለው በታችኛው አንጀት ውስጥ ከቤተሰብ የተወረሰ ከካንሰር በፊት ያሉ ቁስሎች ያሉባቸውን አምስት ታማሚዎች የኩርኩሚን እና የኩዌርሲቲን መደበኛ መጠን በአማካይ ለስድስት ወራት ወስደው ነበር፡፡ አማካይ የቁስሎቹ ቁጥር በ 60.4 % የወረዱ ሲሆን አማካይ የቁስሎቹ መጠን በ50.9 % ወርደዋል፡፡

ኤፍኤፒየሚከሰተው በቤተሰቦች ውስጥ ሲሆን የሚታወቀውም በመቶዎች የሚቆጠሩ ቁስሎች (ኮሎሬክታል አዴኖማስ) ሲፈጠሩ እና የአንጀት ካንሰር ሲሆን ነው፡፡ በቅርቡ በሰውነት ውስጥ የማይመነጩ የሰውነት መቆጣትን የሚከለክሉ መድሀኒቶች (ኤንኤስኤአይዲ እንደ አስፕሪን፣ ኢቡፕሮፊን) በዚህ በሽታ የተያዙ አንዳንድ በሽተኞችን ለማከም ጥቅም ላይ የዋሉ ቢሆንም እነዚህ መድሀኒቶች ብዙውን ጊዜ የአንጀት እና የጨጓራ ቁስለት እና መድማት ከፍተኛ የጎንዮሽ ጉዳቶችን እንደሚያመጡ በጆን ሆፕኪን ዩኒቨርስቲ በጋስትሮኢንትሮሎጂ ክፍል በመሪ ተመራማሪ ፍራንሲስ ኤም. ጊያርዴሎ ኤም.ዲ. ተጠቁሟል፡፡

ብዙ መጠን ያላቸውን ማጣፈጫ የሚጠቀሙ ሰዎች ላይ ከአሁን በፊት በተደረገው የምልከታ ጥናቶች እንደዚሁም የእንስሳት ምርምር በጥብቅ እንደሚመክሩት በእስያ ውስጥ ከዋና ቅመማቅመሞች ውስጥ አንዱ የሆነው ኩርኩሚን የታችኛው የአንጀት ውስጥ ካንሰርን ለመከላከል እና/ወይም ለማከም ውጤታማ ሊሆን ይችላል፡፡ በተመሳሳይ  በተለያዩ ምግቦች ውስጥ እንደ ሽንኩርቶች፣ አረንጓዴ ሻይ እና ቀይ ወይን ውስጥ የሚገኘው ፍሌቮናይድ አንቲኦክሲደንት የሆነው ኪዩዌርሴቲን በሰው ልጆች ውስጥ የአንጀት ካንሰር ህዋስ መስመሮች እድገትን እና በእንስሳት ውስጥ ልክ ያልሆነ የታችኛው አንጀት ህዋሶችን የሚከለክል እንደሆነ ታይቷል፡፡

በዚህ ጥናት ውስጥ ከአምስቱ በሽተኞች ውስጥ አራቱ በሦስት ወር ውስጥ እና ከአራቱ በሽተኞች ውስት አራቱ በስድስት ወራት ውስጥ የቁስል ቁጥር መቀነስ ታይቷል፡፡

እያንዳንዱ በሽተኛ ኩርኩሚን (480 ሚሊግራም) እና ኪዩዌርሴቲን (20 ሚሊግራም) በቀን 3 ጊዜ ለ 6 ወራት ወስደዋል፡፡ ምንም እንኳን የኪዩዌርሴቲን መጠን ብዙ ሰዎች በቀን ከሚወስዱት ጋር ተመሳሳይ ቢሆንም የኩርኩሚን ፍጆታ ከመደበኛው አመጋገብ የበለጠ የሆነበት ምክንያት እርድ የሚይዘው በአማካይ ከ 3-5 % ኩርኩሚን በክብደት ብቻ ነው፡፡

በቀላሉ ማጣፈጫን እና ሽንኩርቶችን መጠቀም ልክ በዚህ ጥናት እንደተከናወነው አፋጣኝ ውጤት ላይኖረው የሚችል ሲሆን ይህ ጥናት በግልፅ እንዳስቀመጠው እርድ እና ሽንኩርትን በነፃነት መጠቀም የታችኛው አንጀት ካንሰር መፈጠር ላ የመከላከል ሚና መጫወት ይችላል፡፡ በተጨማሪም እርድን ለማጣፈጫነት ብቻ መጠቀም የለብንም፡፡ ይህ ቅመም በጤናማ የአፕል ማጣፈጫ ውስጥ  እና በጤናማ እርጥብ የአበባ ጎመን እና/ወይም አረንጓዴ ባቄላዎች እና ሽንኩርቶች ውስጥ ጣፋጭ ነው፡፡ ወይም በጥሩ ቃና የበለፀገ፣ አነስተኛ ካሎሪ ባለው የክሬም እርጎ ላይ እርድ እና የደረቀ ሽንኩርት ለመጨመር ይሞክሩ፡፡

እርድ ከአበባጎመን ጋር በመቀናጀት የወንድ አባላዘር ካንሰርን ይከላከላል

የወንድ አባላዘር ካንሰር በአሜሪካን ውስጥ ሁለተኛው ገዳይ ካንሰር ምክንያት እና በየአመቱም 500000 አዲስ ሰው በበሽታው የሚያዙ ሲሆኑ በህንድ ውስጥ ግን የሚያዙት ወንዶች አነስተኛነው፤ ይህም የአደጋው መከሰት አነስተኛ የሆነበት ምክንያት የብራሲካ ቤተሰብ በሆኑት አትክልቶች እና የማጣፈጫ ቅመም በሆነው እርድ የበለፀገው ምግባቸው ነው፡፡

ይዘቱ ከፍተኛ የሆነ የኩርኩሚን ንጥረነገር ምንጭ የሆነውን እርድን በክሩሲፈረስ አትክልቶችን እንደ የአበባ ጎመን፣ ጎመን፣ ጥቅል ጎመን፣ የብራስልስ ጎመን፣ ቆስጣ፣ ኮህልራቢ እና ፍጁል የበለፀገውን ፌንኢታይል አይዞቲዮሲያኔት የተክል ኬሚካልን ሳይንቲስቶች ሙከራ አድርገዋል፡፡

ሙከራው ለብቻቸው ሲደረግ ሁለቱም ፌንኢታይል አይዞቲዮሲያኔት እና ኩርኩሚን በሽታን የመቋቋም እጥረት ያሉባቸው አይጦች ላይ የተጨመረውን የሰው ልጆች የወንድ አባላዘር ካንሰር ህዋሶችን ዕድገት በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሰዋል፡፡ የወንድ አባላዘር ካንሰር ዕጢዎች በደንብ በተስፋፋበት አይጥ ውስጥ ሁለቱም ፌንኢታይል አይዞቲዮሲያኔት ወይም ኩርኩሚን በራሳቸው በሽታን የመከላከል አቅም የሌላቸው ቢሆንም ነገር ግን በጋራ አንድ ላይ ሲሆኑ ሁለቱንም የዕጢ ዕድገትን እና የወንድ አባላዘር ካንሰር ህዋሶች ስርጭትን (ሜታስቴሲስን) ሙከራ በተደረገባቸው እንስሳቶች ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳሉ፡፡

ተመራማሪዎች እንደሚያምኑት የክሩሲፈረስ አትክልቶች እና ኩርኩሚን ቅንጅት የወንድ አባላዘር ካንሰርን ለመከላከል ብቻ ሳይሆን የተፈጠሩትን የወንድ አባላዘር ካንሰሮች ስርጭትን ለመግታትም ውጤታማ ህክምና ሊሆን ይችላል፡፡ ከሁሉ በላይ የአበባ ጎመን ቅመም ከእርድ ጋር ያለው ቅንጅት በጣም ቆንጆ ነው፡፡ የወንድ አባላዘር ካንሰርን ለመከላከል የአበባ ጎመን አበባን አራት ቦታ በመቁረጥ እና ለ5-10 ደቂቃ ማስቀመጥ ፌንኢታይል አይዞቲዮሲያኔቶች እንዲመረቱ ጊዜ የሚሰጥ ሲሆን ይህም ክሩሲፈረስ አትክልቶች ሲቆረጡ እንዲሰሩ እና ሲሞቁ እንዲያቆሙ ያደርጋል፡፡ ከዚያም በመሀከለኛ ሙቀት ጤነኛ በሆነ አጠባበስ ጥቂት አትክልት ወይም የዶሮ ሾርባ ለ5 ደቂቃዎች በማቆየት እና እርድን በላዩ ላይ መነስነስ፡፡ ከማብሰያው በማውረድ እላዩ ላይ የወይራ ዘይት፣ የባህር ጨው እና በርበሬ ለማጣፈጫነት መጨመር፡፡

የልጅነት ሊኩሚያ አደጋን ይቀንሳል

በቅርቡ በለንደን በተካሄደው የልጆች ሊኩሚያ ኮንፈረንስ ላይ የቀረበው ጥናት እንደሰጠው መረጃ በእርድ የተቀመሙ ምግቦችን መብላት የልጆች ሊኩሚያ አደጋ መከሰትን ሊቀንስ ይችላል፡፡ በ20ኛው ክፍለዘመን ጊዜ ውስጥ የዚህ ካንሰር መከሰት በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ በ1950 ብቻ አደጋው ከ50 % በላይ የጨመረው ዕድሜያቸው ከአምስት አመት በታች በሆኑ ልጆች ላይ ነው፡፡ ዘመናዊ የአካባቢያዊ እና የአኗኗር ሁኔታ ጉዳዮች በዚህ ጭማሪ ውስጥ ከፍተኛውን ሚና እንደሚጫወቱ ይታሰባሉ፡፡

በአመጋገብ ልዩነት ምክንያት ከነዚህም ውስጥ ተደጋጋሚ እርድን መጠቀም የልጆች ሊኩሚያ ከምዕራባዊያን ሀገሮች ይልቅ በእስያ አነስተኛ እንደሆነ ላለፉት 20 አመታት በተከታታይ ምርምር ከቺካጎ አይኤል ሎዮላ ዩኒቨርስቲ የህክምና ማዕከል በፕሮፌሰር ሙልኪ ናጋብሁሻን ጥናት ተደርጓል፡፡

“ለከፍተኛ የልጆች ሊኩሚያ መከሰት አስተዋፅኦ የሚያደርጉት አንዳንድ ታዋቂ አደጋ አምጪ ጉዳዮች የብዙ የአኗኗር ሁኔታዎች መስተጋብር እና የአካባቢያዊ ጉዳዮች ናቸው፡፡ እነዚህም የሚያካትቱት ከመውለድ በፊት እና ከመውለድ በኋላ ለራዲዬሽን መጋለጥ፣ ቤንዚን፣ አካባቢን የሚበክሉ እና አልካይሌቲንግ የኬሚካል ህክምና መድሀኒቶች ናቸው፡፡ የኛ ጥናት እንደሚያሳየው እርድ እና ከለር የሚሰጠው ኩርኩሚን በምግብ ውስጥ መኖር እነዚህን አንዳንድ አደጋ አምጪ ጉዳዮች ያጠፋል፡፡”

ናጋብሁሻን እንዳመለከተው በእርድ ውስጥ ያለው ኩርኩሚን፡

  • የፖሊሳይክሊክ አሮማቲክ ሀይድሮካርበኖችን (ፒኤኤች) (ካርበንን መሰረት ያደረጉ ነዳጆች በማቃጠል ለምሳሌ ሲጋራ በማጨስ ካርሲኖጄኒክ ኬሚካሎች ይፈጠራሉ፡፡) ጂን ለውጦችን ሊከላከል ይችላል፡፡
  • በራዲዬሽን አማካኝነት የክሮሞዞም መጥፋትን ሊከላከል ይችላል፡፡
  • ጎጂ ሄትሮሳይክሊክ አማይንስ እና ናይትሮሶ ኮምፓውንዶችን መፈጠርን ሊከላከል ይችላል፡፡ ይህም በሰውነት ውስጥ አንዳንድ የተፈጩ ምግቦች ናይትሮሳማይንን የያዙ የተፈጩ የስጋ ውጤቶች ሲበሉ ውጤቱ ሊታይ ይችላል፡፡
  • በህዋስ መራቢያ ውስጥ የሊኩሚያ ህዋሶች መባዛትን እንዳይመለስ በማድረግ ሊከላከል ይችላል፡፡

የጉበት ስራዎችን ያሻሽላል

የእርድን በጉበት ዜኖባዮቲክ (መርዛማ) ኬሚካሎችን የማስወገድ አቅም ላይ ያለውን ውጤታማነት ለመገምገም በቅርብ በአይጥ ላይ በተካሄደው ጥናት የሁለት በጣም አስፈላጊ ቆሻሻ አስወጋጅ ኢንዛይሞች ደረጃዎች (ዩዲፒ ግሉኩሮኒል ትራንስፈራስ እና ግሉታቲዮን-ኤስ- ትራንስፈራስ) ከመቆጣጠርያዎቹ ሲወዳደሩ እርድ የተመገቡት አይጦች በከፍተኛ ሁኔታ ጨምረው ነበር፡፡ ተመራማሪዎቹ እንደሰጡት አስተያየት “ውጤቶቹ እንደሚጠቁሙት ከአንቲኦክሲደንት ባህርያቶቹ በተጨማሪ እርድ ቆሻሻ የማስወገድ ዘዴዎቹን ሊጨምር የሚችል ሲሆን እርድ በሰፊው እንደ ቅመም የሚጠቅም እና ብዙ የምግብ ካርሲኖጅኖችን ሊያስወግድ ይችላል፡፡”

በሮደንት ጥናቶች ውስጥ ኩርኩሚን የአንጀት ካንሰርን እንደሚከላከል ታይቷል፡፡ ተመራማሪዎች ኩርኩሚን እንዴት እንደሚሰራ ለመተንተን ጥናት ሲያከናውኑ የጠፉ ቅባታማ ቆሻሻ ነገሮች (በህዋስ ሽፋኖች እና ኮሌስትሮል ውስጥ የሚገኙትን) እንደሚከላከል፣ የሰውነት መቆጣት ኬሚካሎች ሳይክሎኦክሲጀናስ-2 (ሲኦኤክስ-2 ) መፈጠርን እንደሚከላከል እንዲሁም የመጀመርያው የጉበት ቆሻሻ  ማስወገጃ ኢንዛይም ግሉታቲዮን ኤስ ትራንስፈራስ (ጂኤስቲ) መሰራትን የሚደግፍ መሆኑን አመላክተዋል፡፡ አይጦች ለ14 ቀናት ኩርኩሚን ሲሰጣቸው የጉበታቸው የጂኤስቲ ምርቶች በ16 % እንደሚጨምሩ እና የጠፉ ቆሻሻ ነገሮች ምልክት ከመቆጣጠርያዎቹ ጋር ሲወዳደር በ36 % እንደሚቀንስ ደርሰውበታል፡፡ በዚህ ሁለት ሳምንት ጊዜያቶች ተመራማሪዎቹ ካርበን ቴትራክሎራይድ የተባለውን ካንሰር አምጪ ኬሚካል ለአይጦቹ ሰጥተዋል፡፡ ኩርኩሚን ያልተመገቡ አይጦች የአንጀት ህዋስ የጠፉ ቆሻሻ ነገሮች ምልክት የጨመሩ ሲሆን እርድ የተሰጣቸው አይጦች ግን ይህ ጭማሪ በኩርኩሚን ምግብ ተከልክሏል፡፡ በመጨረሻም ተመራማሪዎች እርን በምግብ ውስጥ መስጠት እና ኩርኩሚንን በአይጦች አንጀት ውስጥ መጨመርን አወዳድረዋል፡፡ ኩርኩሚንንነ መጨመር በደም ውስጥ ብዙ ኩርኩሚን እንደሚኖር ያገኙ ሲሆን በአንጀት ዝልግልግ ፈሳሽ ውስጥ ግን አነስተኛ እንደሚገኝ አመላክተዋል፡፡ “ውጤቶቹም እንደሚያሳዩት ኩርኩሚን ከምግብ ጋር ሲቀላቀል በአንጀት እና ጉበት ውስጥ የመድሀኒቱን ደረጃዎች በማሳካት እና የታዩትን የፋርሞሎጂካል ስራዎች በበቂ ሁኔታ ለመግለፅ እንዲሁም ይህ አይነት የአሰጣጥ ዘዴ የአንጀት ካንሰር ኬሚካልን ለመከላከል ሊመረጥ እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡”

የልብ ስራዎችን ይጠብቃል

ኩርኩሚን በሰውነት ውስጥ የኮሌስትሮል ኦክሲዴሽንን ሊከላከል ይችላል፡፡ የደም ማስተላለፊያ ቱቦዎች መጥፋት እና የቆሻሻ ነገር መከማቸት ወደ ልብ ህመም ወይም ስትሮክ ሊመራ የሚችለው ኦክሲዳይዝድ የሆነ ኮሌስትሮል ስለሆነ የአዲስ ኮሌስትሮል ኦክሲዴሽንን መከላከል የአቲሮስክሌሮሲስ እና ከስኳር ጋር የተያያዘ የልብ በሽታ መጠናከርን ይቀንሳል፡፡ በተጨማሪም የሆሞሲስቲን መጠን ከፍ ከማለት የሚጠብቀው የቪታሚን ቢ6 ጥሩ ምንጭ እርድ ነው፡፡ ሆሞሲስቲን በህዋስ መሰራት ሂደት ውስጥ አስፈላጊው መሀከለኛ ምርት ሲሆን ሚታይሌሽን የሚባል እና የደም ማስተላለፍያ ቱቦ ግድግዳዎችን በቀጥታ የሚያጠፋ ነው፡፡ ከፍተኛ መጠን ያለው ሆሞሲስቲን ለደም ማስተላለፍያ ቱቦ መጥፋት ከፍተኛ አደጋ አምጪ ጉዳይ፣ የአቲሮስክሌሮቲክ ቆሻሻ ነገር መከማቸት እና የልብ በሽታ ሲሆን የቪታሚን ቢ6ን በከፍተኛ መጠን መውሰድ ከልብ በሽታ አደጋ መቀነስ ጋር ይያያዛል፡፡

በኢንዲያን ጆርናል ኦፍ ፊዚዮሎጂ እና ፋርማኮሎጂ በታተመው ጥናት ላይ 10 ጤናማ ፈቃደኞች በቀን 500 ሚሊ ግራም ኩርኩሚን ለ7 ቀናት ሲጠቀሙ ኦክሲዳይዝድ ኮሌስትሮል የሆነው የደም መጠን በ33 % መውረዱ ብቻ ሳይሆን ጠቅላላ የኮሌስትሮል መጠኑም በ 11.63 % የወረደ እና የኤችዲኤል (ጥሩ ኮሌስትሮል) በ29 % ጨምሯል፡፡ (ሶኒ ኬቢ፣ ኩታን አር)

እርድ እንዴት ኮሌስትሮልን ይቀንሳል

የእርድ ኮሌስትሮልን የመቀነስ ብቃቶች የተገኙት ኩርኩሚን በተባለው በማጣፈጫ ቅመሞች ውስጥ ባለው ንቁ ቅመም ሲሆን ተመራማሪዎች እንዳረጋገጡት ኩርኩሚን በጉበት ህዋሶች ውስጥ ካሉት ጂኖች ጋር የሚገናኝ መልዕክት አስተላላፊ ሞለኪዩል በመሆኑ የኤምአርኤንኤ (ሚሴንጀር ፕሮቲን) ምርትን ለመጨመር ኩርኩሚንን የሚመራ እና ለኤልዲኤል (መጥፎ ኮሌስትሮል) ወደ ሪሴፕተሮች መፈጠርን ይመራል፡፡ ብዙ ኤልዲኤል ሪሴፕተሮች ሲኖሩ የጉበት ህዋሶች ኤልዲኤል ኮሌስትሮሎችን ከሰውነት ውስጥ ለማስወገድ ይችላሉ፡፡

የጉበት ህዋሶች 10 ማይክሮን ኤም ይዘት ባለው ኩርኩሚን ሲታከም ካልታከሙት ህዋሶች ጋር ሲወዳደር ሰባት እጥፍ ኤልዲኤል-ሪሴፕተር ኤምአርኤንኤ ይጨምራል፡፡ (የጉበት ህዋሶች ኩርኩሚንን ለ24 ሰዓታት እስከ 12 ማይክሮን ኤም መጠን ድረስ መቋቋም ችሏል፡፡ (ፒሼል ዲ፣ ኮርቲንግ አር ጄ ኑትር ባዮኬም)

የተግባር ምክሮች፡

በእርድ ላይ በመመርኮዝ ኤልዲኤል ኮሌስትሮልን ለማስወገድ የጉበት አቅምን ለመጨመር የሚረዳው ለጣፋጭ አሳ፣ ስጋ ወይም ምስር ማጣፈጫዎች ሳይሆን ለጤናማ የሽንኩርት ወጥ፣ ድንቾች እና/ወይም የአበባ ጎመንን ለማጣፈጥ፤ ወይም ክሬም ያለው አትክልት ላይ ቁልፍ የሆነ ቃናን ለመጨመር ነው፡፡ እርጎን በኦሜጋ-3-በበለፀገ ትንሽ ማዮኔዝ እና እርድ፣ ጨው እና በርበሬ ለማጣፈጥ ይቀላቅሉ፡፡ ከጥሬ የአበባ ጎመን፣ ቃርያ፣ ጂካማ እና ጥቅል ጎመን አበባዎች ያቅርቡ፡፡  ተደባልቆ ከተዘጋጀ ማጣፈጫዎች ይልቅ እርድን መምረጥዎን እርግጠኛ ይሁኑ፡፡ የቅርብ ጥናት እንደሚያመለክተው በተደባለቀ ማጣፈጫ ውስጥ የእርድ መጠን (ማለትም ኩርኩሚን) ብዙውን ጊዜ ትንሽ ነው፡፡ (ታየርን አርኤፍ፣ ኑትር ካንሰር)

ለአብዛኛው ኩርኩሚን ከማጣፈጫ ዱቄት ይልቅ እርድን መጠቀምዎን እርግጠኛ ይሁኑ፡፡ በ 28 የቅመም ምርቶች ውስጥ የኩርኩሚንን ይዘት እንደ እርድ ወይም ማጣፈጫ ዱቄቶች የሚገለፁትን በሚተነትነው ጥናት እንደተገኘው ንፁህ የእርድ ዱቄት ከፍተኛ የኩርኩሚን መጠን እንዳለው እና በአማካይ በክብደት 3.14 % ነው፡፡ የማጣፈጫ ዱቄት ናሙናዎች ከአንዱ በስተቀር በጣም ትንሽ የሆነ ኩርኩሚን መጠን ነው የያዙት፡፡ (ታየርን አርኤፍ፣ ሂዝ ዲዲ፣ ኑትር ካንሰር)

የአልዛይመርን በሽታዎችን ይከላከላል

እያደገ የመጣው መረጃ እንደሚጠቁመው እርድ ነርቭን ከሚያጠፋ በሽታዎች ሊጠብቅ ይችላል፡፡ የተላላፊ በሽታ ጥናቶች እንዳመለከቱት በምግባቸው ውስጥ እርድ የተለመደ ቅመም ያደረጉ እድሜያቸው የገፉ የህንድ ህዝቦች እንደ አልዛይመር የነርቭ በሸታዎች መጠናቸው በጣም ዝቅተኛ ናቸው፡፡ በቅርቡ በተመሳሳይ ጊዜ የተደረጉት ምርምሮች እንዳገኙት ኩርኩሚን በአይጥ ውስጥ የአልዛይመርን መስፋፋት ይቀንሳል፡፡ በአይጥ ላይ የመጀመርያው ጥናት እንደሚመክረው ኩርኩሚን የብዙ አይነት ስክሌሮሲስ መስፋፋትን ሊገታ ይችላል፡፡ ይህን አጥፊ ሁኔታ እንዴት ሊከላከል እንደቻለ እስከአሁን ግልፅ ያልሆነ ቢሆንም በሰውነት ውስጥ አብዛኛውን ነርቮች ለመጠበቅ የሚያገለግለው ሽፋንን ወይም ማዬሊንን ለማጥፋት ቁልፍ ሚና ሊጫወት የሚችለውን ፕሮቲን ወይም  አይኤል-2 ምርትን ሊያቋርጥ እንደሚችል አንድ ፅንሰ ሀሳብ አለ፡፡

ብዙ ጥናቶች እንደመከሩት በእርድ ውስጥ በተፈጥሮ ንቁ የሆነ መሰረታዊ ነገር ወይም ኩርኩሚን የአንቲኦክሲደንት ፕሮቲኖችን ምርትን የሚቀምረውን ጂን በማስነሳት የአልዛይመርን በሽታ ይከላከላል፡፡ በጣልያን ስነህይወት ኬሚስትሪ መፅሀፍ ውስጥ በታተመው ጥናት (ታህሳስ 2003) ላይ እንደተደረገው ውይይት አዕምሮን ከኦክሲዴቲቭ (ቆሻሻ ነገሮች) ጉዳት የሚጠብቅ፣ በአዕምሮ ጡንቻዎች ውስጥ ሲጀመር፣ አቅም ያለውን የአንቲኦክሲደንት ቢሊሩቢን የመከላከያ ዘዴን ወይም የሂምኦክሲጀኔስ መንገድን በማስጀመር የኩርኩሚን ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ ይህ ኦክሲዴሽን የእርጅና እና እንደ አልዛይመር በሽታ የአዕምሮ መሳትን የሚያካትት የነርቭ መጥፋት ያለመስተካከልን የሚያመጣው ዋናው ምክንያት እንደሆነ የሚታሰብ ነው፡፡ በጣሊያን እና አሜሪካን ቡድን በጋራ የተካሄደው እና በዋሺንግተን ዲሲ ውስጥ በአሜሪካን ሳይኮሎጂካል እና ሶሻል 2004 አመታዊ ኮንፈረንስ ላይ የቀረበው ሌላ ጥናት እንዳረጋገጠው ኩርኩሚን በአዕምሮ ሂፖካምፓል አካባቢ በአስትሮሳይት ውስጥ የሂምኦክሲጀኔስ-1 (ኤችኦ-1) የተባለውን የጂኑን መገለጫ በከፍተኛ ሁኔታ ያነሳሳል፡፡

ኩርኩሚን የጭንቅላት ደም ግድግዳን በማቋረጥ የአልዛይመርን በሽታን ሊከላከል ይችላል

በዩሲኤልኤ የተከናወነው እና በስነህይወት ኬሚስትሪ መፅሄት ውስጥ (ታህሳስ 2004) የታተመው ምርምር እና በእርሻ እና ምግብ ኬሚስትሪ መፅሄት ውስጥ (ሚያዝያ 2006) በመታተም በተጨማሪ ምርምር የተረጋገጠው ከኩርኩሚን የአልዛይመር በሽታ መከላከል ብቃት በስተጀርባ ያሉትን ዘዴዎች ገለፃ ይሰጣል፡፡

የአልዛይመር በሽታ የሚመጣው አሚሎይድ-ቢ የሚባለው የፕሮቲን ክፍል በጭንቅላት ክፍል ውስጥ በመከማቸት ኦክሲዴቲቭ ጫና እና የሰውነት መቆጣትን በመፍጠር እና በጭንቅላት ውስጥ የጭንቅላት ስራዎችን የሚያውኩ በነርቭ ህዋሶች (ኒውሮኖች) መሀከል ንጣፎች ይሰራሉ፡፡

ሰውነታችን በተፈጥሮ የሚሰራው የፕሮቲን ክፍል ጠቅላላ ቃል አሚሎይድ ነው፡፡ አሚሎይድ ፕሪከርሰር ፕሮቲን (ኤፒፒ) ከሚባለው ሌላ ፕሮቲን የሚቆረጠው የፕሮቲን ክፍል አሚሎይድ ቢ ነው፡፡ በጤናማ ጭንቅላት ውስጥ እነዚህ የፕሮቲን ክፍሎች ይሰባበሩ እና ይጠፋሉ፡፡ በአልዛይመር በሽታ ውስጥ የፕሮቲን ክፍሎቹ ይከማቹ እና ጠንካራ የማይሟሟ ንጣፎች በጭንቅላት ህዋሶች ውስጥ ይሰራሉ፡፡

የዩሲኤልኤ ተመራማሪዎች በመጀመርያ ያከናወኑት የሙከራ ቲዩብ ጥናቶች ሲሆን ኩርኩሚን የሰውነት መቆጣትን ከሚከላከሉ ኢቡፕሮፊን እና ናፕሮክሲን መድሀኒቶች የበለጠ የአሚሎይድ-ቢ ክምችትን እንደሚከላከል  እና አሚሎይድ ፋይብሪልን ውጤታማ በሆነ መልኩ እንደሚያሟሟ ታይቷል፡፡ ከዚያም ተመራማሪዎች ህይወት ባለው አይጥ በመጠቀም እንዳገኙት ኩርኩሚን የጭንቅላት ደም ግድግዳዎችን በማቋረጥ እና ከትንሽ አሚሎይድ-ቢ አይነት ጋር ይያያዛል፡፡ የአሚሎይድ-ቢ የፕሮቲን ክፍሎች አንድ ጊዜ ከኩርኩሚን ጋር ከተያያዙ ንጣፎችን ለመስራት እርስበእርስ ሊያያዙ አይችሉም፡፡ ኩርኩሚን ከአሚሎይድ-ቢ ጋር የሚያያዙ ብቻ ሳይሆኑ የሰውነት መቆጣትን የመከላከል እና የአንቲኦክሲደንት ባህርያቶች ያሉት በመሆኑ ለጭንቅላት ህዋሶች ተጨማሪ ጥበቃ ይሰጣል፡፡


ethiopian-turmeric-food-blog-health-diet-recipes-injera

Turmeric has a peppery, warm and bitter flavor and a mild fragrance slightly reminiscent of orange and ginger, and while it is best known as one of the ingredients used to make curry, it also gives ballpark mustard its bright yellow color.

Turmeric comes from the root of the Curcuma longa plant and has a tough brown skin and a deep orange flesh. Turmeric has long been used as a powerful anti-inflammatory in both the Chinese and Indian systems of medicine. Turmeric was traditionally called “Indian saffron” because of its deep yellow-orange color and has been used throughout history as a condiment, healing remedy and textile dye.

Turmeric (Curcuma longa), the bright yellow of the spice rainbow, is a powerful medicine that has long been used in the Chinese and Indian systems of medicine as an anti-inflammatory agent to treat a wide variety of conditions, including flatulence, jaundice, menstrual difficulties, bloody urine, hemorrhage, toothache, bruises, chest pain, and colic.

A Potent, Yet Safe Anti-Inflammatory

The volatile oil fraction of turmeric has demonstrated significant anti-inflammatory activity in a variety of experimental models. Even more potent than its volatile oil is the yellow or orange pigment of turmeric, which is called curcumin. Curcumin is thought to be the primary pharmacological agent in turmeric. In numerous studies, curcumin’s anti-inflammatory effects have been shown to be comparable to the potent drugs hydrocortisone and phenylbutazone as well as over-the-counter anti-inflammatory agents such as Motrin. Unlike the drugs, which are associated with significant toxic effects (ulcer formation, decreased white blood cell count, intestinal bleeding), curcumin produces no toxicity.

An Effective Treatment for Inflammatory Bowel Disease

Curcumin may provide an inexpensive, well-tolerated, and effective treatment for inflammatory bowel disease (IBD) such as Crohn’s and ulcerative colitis, recent research suggests. In this study, mice given an inflammatory agent that normally induces colitis were protected when curcumin was added to their diet five days beforehand. The mice receiving curcumin not only lost much less weight than the control animals, but when researchers checked their intestinal cell function, all the signs typical of colitis (mucosal ulceration, thickening of the intestinal wall, and the infiltration of inflammatory cells)were all much reduced. While the researchers are not yet sure exactly how curcumin achieves its protective effects, they think its benefits are the result of not only antioxidant activity, but also inhibition of a major cellular inflammatory agent called NF kappa-B. Plus, an important part of the good news reported in this study is the fact that although curcumin has been found to be safe at very large doses, this component of turmeric was effective at a concentration as low as 0.25 per cent—an amount easily supplied by simply enjoying turmeric in flavorful curries.

Relief for Rheumatoid Arthritis

Clinical studies have substantiated that curcumin also exerts very powerful antioxidant effects. As an antioxidant, curcumin is able to neutralize free radicals, chemicals that can travel through the body and cause great amounts of damage to healthy cells and cell membranes. This is important in many diseases, such as arthritis, where free radicals are responsible for the painful joint inflammation and eventual damage to the joints. Turmeric’s combination of antioxidant and anti-inflammatory effects explains why many people with joint disease find relief when they use the spice regularly. In a recent study of patients with rheumatoid arthritis, curcumin was compared to phenylbutazone and produced comparable improvements in shortened duration of morning stiffness, lengthened walking time, and reduced joint swelling.

Help for Cystic Fibrosis Sufferers

Curcumin, the major constituent of turmeric that gives the spice its yellow color, can correct the most common expression of the genetic defect that is responsible for cystic fibrosis, suggests an animal study published in the Science (April 2004). Cystic fibrosis, a fatal disease that attacks the lungs with a thick mucus, causing life-threatening infections, afflicts about 30,000 American children and young adults, who rarely survive beyond 30 years of age. The mucus also damages the pancreas, thus interfering with the body’s ability to digest and absorb nutrients.

Researchers now know that cystic fibrosis is caused by mutations in the gene that encodes for a protein (the transmembrane conductance regulator or CFTR). The CTFR protein is responsible for traveling to the cell’s surface and creating channels through which chloride ions can leave the cell. When the protein is abnormally shaped because of a faulty gene, this cannot happen, so chloride builds up in the cells, which in turn, leads to mucus production.

The most common mutation, which is called DeltaF508, results in the production of a misfolded protein. When mice with this DeltaF508 defect were given curcumin in doses that, on a weight-per-weight basis, would be well-tolerated by humans, curcumin corrected this defect, resulting in a DeltaF508 protein with normal appearance and function. In addition, the Yale scientists studying curcumin have shown that it can inhibit the release of calcium, thus allowing mutated CTFR to exit cells via the calcium channels, which also helps stop the chloride-driven build up of mucus. Specialists in the treatment of cystic fibrosis caution, however, that patients should not self-medicate with dietary supplements containing curcumin, until the correct doses are known and any adverse interactions identified with the numerous prescription drugs taken by cystic fibrosis sufferers.

Cancer Prevention

Curcumin’s antioxidant actions enable it to protect the colon cells from free radicals that can damage cellular DNA—a significant benefit particularly in the colon where cell turnover is quite rapid, occuring approximately every three days. Because of their frequent replication, mutations in the DNA of colon cells can result in the formation of cancerous cells much more quickly. Curcumin also helps the body to destroy mutated cancer cells, so they cannot spread through the body and cause more harm. A primary way in which curcumin does so is by enhancing liver function. Additionally, other suggested mechanisms by which it may protect against cancer development include inhibiting the synthesis of a protein thought to be instrumental in tumor formation and preventing the development of additional blood supply necessary for cancer cell growth.

Inhibits Cancer Cell Growth and Metastases

Epidemiological studies have linked the frequent use of turmeric to lower rates of breast, prostate, lung and colon cancer; laboratory experiments have shown curcumin can prevent tumors from forming; and research conducted at the University of Texas suggests that even when breast cancer is already present, curcumin can help slow the spread of breast cancer cells to the lungs in mice.

In this study, published in Biochemical Pharmacology (September 2005), human breast cancer cells were injected into mice, and the resulting tumors removed to simulate a mastectomy.

The mice were then divided into four groups. One group received no further treatment and served as a control. A second group was given the cancer drug paclitaxel (Taxol); the third got curcumin, and the fourth was given both Taxol and curcumin.

After five weeks, only half the mice in the curcumin-only group and just 22% of those in the curcumin plus Taxol group had evidence of breast cancer that had spread to the lungs.

But 75% of the mice that got Taxol alone and 95% of the control group developed lung tumours.

How did curcumin help? “Curcumin acts against transcription factors, which are like a master switch,” said lead researcher, Bharat Aggarwal. “Transcription factors regulate all the genes needed for tumors to form. When we turn them off, we shut down some genes that are involved in the growth and invasion of cancer cells.”

In another laboratory study of human non-Hodgkin’s lymphoma cells published in Biochemical Pharmacology (September 2005), University of Texas researchers showed that curcumin inhibits the activation of NF-kappaB, a regulatory molecule that signals genes to produce a slew of inflammatory molecules (including TNF, COX-2 and IL-6) that promote cancer cell growth. In addition, curcumin was found to suppress cancer cell proliferation and to induce cell cycle arrest and apoptosis (cell suicide) in the lung cancer cells. Early phase I clinical trials at the University of Texas are now also looking into curcumin’s chemopreventive and therapeutic properties against multiple myeloma and pancreatic cancer, and other research groups are investigating curcumin’s ability to prevent oral cancer.

Turmeric and Onions May Help Prevent Colon Cancer

Curcumin, a phytonutrient found in the curry spice turmeric, and quercitin, an antioxidant in onions, reduce both the size and number of precancerous lesions in the human intestinal tract, shows research published in the August 2006 issue of Clinical Gasteroenterology and Hepatology.

Five patients with an inherited form of precancerous polyps in the lower bowel known as familial adenomatous polyposis (FAP) were treated with regular doses of curcumin and quercetin over an average of six months. The average number of polyps dropped 60.4%, and the average size of the polyps that did develop dropped by 50.9%.

FAP runs in families and is characterized by the development of hundreds of polyps (colorectal adenomas) and, eventually, colon cancer. Recently, nonsteroidal anti-inflammatory drugs (NSAIDs such as aspirin, ibuprofen) have been used to treat some patients with this condition, but these drugs often produce significant side effects, including gastrointestinal ulcerations and bleeding, according to lead researcher Francis M. Giardiello, M.D., at the Division of Gastroenterology, Johns Hopkins University.

Previous observational studies in populations that consume large amounts of curry, as well as animal research, have strongly suggested that curcumin, one of the main ingredients in Asian curries, might be effective in preventing and/or treating cancer in the lower intestine. Similarly, quercetin, an anti-oxidant flavonoid found in a variety of foods including onions, green tea and red wine, has been shown to inhibit growth of colon cancer cell lines in humans and abnormal colorectal cells in animals.

In this study, a decrease in polyp number was observed in four of five patients at three months and four of four patients at six months.

Each patient received curcumin (480 mg) and quercetin (20 mg) orally 3 times a day for 6 months. Although the amount of quercetin was similar to what many people consume daily, the curcumin consumed was more than would be provided in a typical diet because turmeric only contains on average 3-5 % curcumin by weight.

While simply consuming curry and onions may not have as dramatic an effect as was produced in this study, this research clearly demonstrates that liberal use of turmeric and onions can play a protective role against the development of colorectal cancer. And turmeric doesn’t have to only be used in curries. This spice is delicious on healthy sautéed apples, and healthy steamed cauliflower and/or green beans and onions. Or, for a flavor-rich, low-calorie dip, try adding some turmeric and dried onion to creamy yogurt.

Turmeric Teams Up with Cauliflower to Halt Prostate Cancer

Prostate cancer—the second leading cause of cancer death in American men with 500,000 new cases appearing each year—is a rare occurrence among men in India, whose low risk is attributed to a diet rich in brassica family vegetables and the curry spice, turmeric.

Scientists tested turmeric, a concentrated source of the phytonutrient curcumin, along with phenethyl isothiocyanates, a phytochemical abundant in cruciferous vegetables including cauliflower, cabbage, broccoli, Brussels sprouts, kale, kohlrabi and turnips.

When tested singly, both phenethyl isothiocyanate and curcumin greatly retarded the growth of human prostate cancer cells implanted in immune-deficient mice. In mice with well-established prostate cancer tumors, neither phenethyl isothiocyanate nor curcumin by itself had a protective effect, but when combined, they significantly reduced both tumor growth and the ability of the prostate cancer cells to spread (metastasize) in the test animals.

The researchers believe the combination of cruciferous vegetables and curcumin could be an effective therapy not only to prevent prostate cancer, but to inhibit the spread of established prostate cancers. Best of all, this combination—cauliflower spiced with turmeric—is absolutely delicious! For protection against prostate cancer, cut cauliflower florets in quarters and let sit for 5-10 minutes; this allows time for the production of phenethyl isothiocyanates, which form when cruciferous vegetables are cut, but stops when they are heated. Then sprinkle with turmeric, and healthy sauté on medium heat in a few tablespoons of vegetable or chicken broth for 5 minutes. Remove from the heat and top with olive oil, sea salt and pepper to taste.

Reduce Risk of Childhood Leukemia

Research presented at a recent conference on childhood leukemia, held in London, provides evidence that eating foods spiced with turmeric could reduce the risk of developing childhood leukemia. The incidence of this cancer has risen dramatically during the 20th century, mainly in children under age five, among whom the risk has increased by more than 50% cent since 1950 alone. Modern environmental and lifestyle factors are thought to play a major role in this increase.

Childhood leukemia is much lower in Asia than Western countries, which may be due to differences in diet, one of which, the frequent use of turmeric, has been investigated in a series of studies over the last 20 years by Prof. Moolky Nagabhushan from the Loyola University Medical Centre, Chicago, IL.

“Some of the known risk factors that contribute to the high incidence of childhood leukemia are the interaction of many lifestyle and environmental factors. These include prenatal or postnatal exposure to radiation, benzene, environmental pollutants and alkylating chemotherapeutic drugs. Our studies show that turmeric—and its colouring principle, curcumin—in the diet mitigate the effects of some of these risk factors.”

Nagabhushan has shown that the curcumin in turmeric can:

  • inhibit the mutagenicity of polycyclic aromatic hydrocarbons (PAHs) (carcinogenic chemicals created by the burning of carbon based fuels including cigarette smoke)
  • inhibit radiation-induced chromosome damage
  • prevent the formation of harmful heterocyclic amines and nitroso compounds, which may result in the body when certain processed foods, such as processed meat products that contain nitrosamines, are eaten
  • irreversibly inhibit the multiplication of leukemia cells in a cell culture

Improved Liver Function

In a recent rat study conducted to evaluate the effects of turmeric on the liver’s ability to detoxify xenobiotic (toxic) chemicals, levels of two very important liver detoxification enzymes (UDP glucuronyl transferase and glutathione-S-transferase) were significantly elevated in rats fed turmeric as compared to controls. The researchers commented, “The results suggest that turmeric may increase detoxification systems in addition to its anti-oxidant properties…Turmeric used widely as a spice would probably mitigate the effects of several dietary carcinogens.”

Curcumin has been shown to prevent colon cancer in rodent studies. When researchers set up a study to analyze how curcumin works, they found that it inhibits free radical damage of fats (such as those found in cell membranes and cholesterol), prevents the formation of the inflammatory chemical cyclooxygenase-2 (COX-2), and induces the formation of a primary liver detoxification enzyme, glutathione S-transferase (GST) enzymes. When the rats were given curcumin for 14 days, their livers’ production of GST increased by 16%, and a marker of free radical damage called malondialdehyde decreased by 36% when compared with controls. During this two week period, the researchers gave the rats a cancer-causing chemical called carbon tetrachloride. In the rats not fed curcumin, markers of free radical damage to colon cells went up, but in the rats given turmeric, this increase was prevented by dietary curcumin. Lastly, the researchers compared giving turmeric in the diet versus injecting curcumin into the rats’ colons. They found injecting curcumin resulted in more curcumin in the blood, but much less in the colon mucosa. They concluded, “The results show that curcumin mixed with the diet achieves drug levels in the colon and liver sufficient to explain the pharmacological activities observed and suggest that this mode of administration may be preferable for the chemoprevention of colon cancer.”

Cardiovascular Protection

Curcumin may be able to prevent the oxidation of cholesterol in the body. Since oxidized cholesterol is what damages blood vessels and builds up in the plaques that can lead to heart attack or stroke, preventing the oxidation of new cholesterol may help to reduce the progression of atherosclerosis and diabetic heart disease. In addition, turmeric is a good source of vitamin B6, which is needed to keep homocysteine levels from getting too high. Homocysteine, an intermediate product of an important cellular process called methylation, is directly damaging to blood vessel walls. High levels of homocysteine are considered a significant risk factor for blood vessel damage, atherosclerotic plaque build-up, and heart disease; while a high intake of vitamin B6 is associated with a reduced risk of heart disease.

In research published in the Indian Journal of Physiology and Pharmacology, when 10 healthy volunteers consumed 500 mg of curcumin per day for 7 days, not only did their blood levels of oxidized cholesterol drop by 33%, but their total cholesterol droped 11.63% , and their HDL (good cholesterol) increased by 29%! (Soni KB, Kuttan R).

How Turmeric Lowers Cholesterol

Tumeric’s cholesterol-lowering effects are the result of the curry spice’s active constituent, curcumin, which research reveals is a messaging molecule that communicates with genes in liver cells, directing them to increase the production of mRNA (messenger proteins) that direct the creation of receptors for LDL (bad) cholesterol. With more LDL-receptors, liver cells are able to clear more LDL-cholesterol from the body.

LDL-receptor mRNA increased sevenfold in liver cells treated with curcumin at a concentration of 10 microM, compared to untreated cells. (Liver cells were found to tolerate curcumin at levels of up to 12. microM for 24 hours). (Peschel D, Koerting R, et al. J Nutr Biochem)

Practical Tips: 

Help increase your liver’s ability to clear LDL-cholesterol by relying on turmeric, not just for delicious fish, meat or lentil curries, but to spice up healthy sautéed onions, potatoes and/or cauliflower; or as the key flavoring for a creamy vegetable dip. Just mix plain yogurt with a little omega-3-rich mayonnaise and turmeric, salt and pepper to taste. Serve with raw cauliflower, celery, sweet pepper, jicama and broccoli florets. Be sure to choose turmeric rather than prepared curry blends. Recent research indicates the amount of turmeric (and therefore curcumin) in curry blends is often minimal.(Tayyem RF et al.,Nutr Cancer)

For the most curcumin, be sure to use turmeric rather curry powder—a study analyzing curcumin content in 28 spice products described as turmeric or curry powders found that pure turmeric powder had the highest concentration of curcumin, averaging 3.14% by weight. The curry powder samples, with one exception, contained very small amounts of curcumin. (Tayyem RF, Heath DD, et al. Nutr Cancer)

Protection against Alzheimer’s Disease

Growing evidence suggests that turmeric may afford protection against neurodegenerative diseases. Epidemiological studies show that in elderly Indian populations, among whose diet turmeric is a common spice, levels of neurological diseases such as Alzheimer’s are very low. Concurrently, experimental research conducted recently found that curcumin does appear to slow the progression of Alzheimer’s in mice. Preliminary studies in mice also suggest that curcumin may block the progression of multiple sclerosis. While it is still unclear how it may afford protection against this degenerative condition, one theory is that it may interrupt the production of IL-2, a protein that can play a key role in the destruction of myelin, the sheath that serves to protect most nerves in the body.

A number of studies have suggested that curcumin, the biologically active constituent in turmeric, protects against Alzheimer’s disease by turning on a gene that codes for the production of antioxidant proteins. A study published in the Italian Journal of Biochemistry (December 2003) discussed curcumin’s role in the induction of the the heme oxygenase pathway, a protective system that, when triggered in brain tissue, causes the production of the potent antioxidant bilirubin, which protects the brain against oxidative (free radical) injury. Such oxidation is thought to be a major factor in aging and to be responsible for neurodegenerative disorders including dementias like Alzheimer’s disease. Another study conducted jointly by an Italian and U.S. team and presented at the American Physiological Society’s 2004 annual conference in Washington, DC, confirmed that curcumin strongly induces expression of the gene, called hemeoxygenase-1 (HO-1) in astrocytes from the hippocampal region of the brain.

Curcumin Crosses Blood-Brain Barrier, May Help Prevent Alzheimer’s Disease

Research conducted at UCLA and published in the Journal of Biological Chemistry (December 2004), which has been confirmed by further research published in the Journal of Agricultural and Food Chemistry (April 2006), provides insight into the mechanisms behind curcumin’s protective effects against Alzheimer’s disease.

Alzheimer’s disease results when a protein fragment called amyloid-B accumulates in brain cells, producing oxidative stress and inflammation, and forming plaques between nerve cells (neurons) in the brain that disrupt brain function.

Amyloid is a general term for protein fragments that the body produces normally. Amyloid-B is a protein fragment snipped from another protein called amyloid precursor protein (APP). In a healthy brain, these protein fragments are broken down and eliminated. In Alzheimer’s disease, the fragments accumulate, forming hard, insoluble plaques between brain cells.

The UCLA researchers first conducted test tube studies in which curcumin was shown to inhibit amyloid-B aggregation and to dissolve amyloid fibrils more effectively than the anti-inflammatory drugs ibuprofen and naproxen. Then, using live mice, the researchers found that curcumin crosses the blood brain barrier and binds to small amyloid-B species. Once bound to curcumin, the amyloid-B protein fragments can no longer clump together to form plaques. Curcumin not only binds to amyloid-B, but also has anti-inflammatory and antioxidant properties, supplying additional protection to brain cells.

Recent Posts