Olive Oil Health Benefits and Nutrition – የወይራ ዘይት የጤና ጥቅሞች እና ንጥረ ነገር

Olive Oil Health Benefits and Nutrition – የወይራ ዘይት የጤና ጥቅሞች እና ንጥረ ነገር

የወይራ ዘይት የጤና ጥቅሞች አስገራሚ የሆኑ ሲሆን የምርምር ጥናቶችም የሚያረጋግጡት በየቀኑ ተጨማሪ ጥቅሞች እንደሚገኙ ነው፡፡ በእርግጥ ወይራ ዘይት ጤናችንን እና ኑሯችንን ሊያሻሽል የሚችልበት መንገዶችን ለመረዳት ገና ጅማሮ ላይ ነን፡፡ የወይራ ዘይት የሜዲትራኒያን ምግብ የማዕዘን ድንጋይ ሲሆን በአለም ረጅም ጊዜ ለመኖር አስፈላጊ የንጥረ ነገር መገኛ ነው፡፡

የጡት ካንሰር መከሰትን እና ተደጋጋሚነቱን መቀነስ የሚችለውን የሰውነት መቆጣትን የሚቀንሰውን የኢቡፕሮፊን የስራ ውጤት በወይራ ዘይት ውስጥ ያለው ኦሊዎካንታል የተክል ንጥረ ነገር ይተካዋል፡፡ ስኳሊን እና ሊግናኖች ሌሎች በወይራ ዘይት ውስጥ የሚገኙ ንጥረ ነገሮች ሲሆኑ በካንሰር ላይ ስለሚኖራቸው ውጤታማነት በመጠናት ላይ ያሉ ናቸው፡፡

የወይራ ዘይት ምግብ የስኳር በሽታ 2 አይነት መከሰትን ይቀንሳል

ብዙውን ጊዜ አነስተኛ ቅባት ያላቸው ምግቦች የተለያዩ በሽታዎችን እንደ የልብ እና ስኳር በሽታዎችን ለመከላከል ይታዘዛሉ፡፡ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከፍተኛ ቅባት ያላቸው ምግቦች የተወሰኑ በሽታዎች እንደ ካንሰር እና የስኳር በሽታ መከሰትን ሊጨምሩ የሚችሉ ሲሆን፤ ከቅባቱ መብዛት ይልቅ የቅባቱ አይነት ተፅዕኖው የጎላ ነው፡፡ በእርግጥ አሁን በወይራ ዘይት፣ ለውዝ እና ሌሎች ዘሮች ውስጥ እንደሚገኘው በሞኖሳቹሬትድ የበለፀገ የቅባት ምግብ ከብዙ የተለያዩ አደገኛ በሽታዎች እንደሚከላከሉ  እናውቃለን፡፡

በሳይንሳዊ የስኳር በሽታ መከላከያ መፅሔት ላይ የታተመው ጥናት ላይ እንደተመለከተው የሜዲትራኒያን የአመጋገብ ስርዓት የሆነው እና በወይራ ዘይት የበለፀገው ምግብ የስኳር በሽታ 2 አይነት መከሰትን ከአነስተኛ የቅባት ምግብ አንፃር ሀምሳ በመቶ ይቀንሳል፡፡ የስኳር በሽታ 2 አይነት በጣም የተለመደ እና ሊከላከሉት የሚቻል የስኳር በሽታ ነው፡፡

የወይራ ዘይት ስትሮክን ለመከላከል ሊረዳ ይችላል

በቀጥታ ኢንተርኔት በነርቭ ስርዓት ጉዳዮች ላይ በታተመው አዲስ የፈረንረሳይ ጥናት ላይ እንደተገለፀው የወይራ ዘይትን በየቀኑ የሚጠቀሙ በዕድሜ የገፉ ሰዎች ራሳቸውን ከስትሮክ መከላከል ይችላሉ፡፡ ቦርዶ፣ ሊዮን እና ሞንፔሌ በተባሉ የፈረንሳይ ከተሞች ውስጥ ዕድሜያቸው ከ65 ዓመት በላይ የሆናቸው 7,625 ሰዎች ላይ ተመራማሪዎች የህክምና መረጃዎችን  አሰባስበዋል፡፡ ከተሳታፊዎች ውስጥ ማንም የስትሮክ ታሪክ አልነበራቸውም፡፡ ከዚያም እንደ ወይራ ዘይት አጠቃቀማቸው ሰዎቹን በሦስት ቡድን መድበዋቸዋል፡፡ ተሳታፊዎቹ በፈረንሳይ የሚገኙትን አዲስ የተተከሉ የወይራ ዘይቶችን በብዛት እንደሚጠቀሙ ተገንዝበዋል፡፡

ከ5 ዓመት በኋላ 148 ስትሮኮች ነበሩ፡፡ ውጤቱ እንደሚያሳየው “በከፍተኛ ሁኔታ” ለምግብነት እና ለመልበስ የወይራ ዘይትን የሚጠቀሙት 41 በመቶ ሙሉ ለሙሉ የወይራ ዘይትን ከማይጠቀሙት አንፃር አነስተኛ በስትሮክ የመጠቃት ዕድል አጋጥሟቸዋል፡፡ ክብደትን፣ አመጋገብን፣ የአካል እንቅስቃሴ ስራዎችን እና ሌሎች አደጋ አምጪ ጉዳዮችን ከግምት ከገቡ በኋላም እነዚህ ውጤቶች ታውቀዋል፡፡

የወይራ ዘይት ልብን አዲስ እንደሆነ ያቆያል

በእርግጥ በወይራ ዘይት የበለፀገ ምግብ የልብን እርጅና ማዘግየት ይችላል፡፡ በሀቅ እንደሚታወቀው እያረጀን በምንሄድበት ወቅት ልባችንም በተለመደው በእርጅና ሂደት ይጓዛል፡፡ ደም ቅዳዎች ልክ እንደበፊቱ በትክክል ስራቸውን ማከናወን ስለማይችሉ ወደተለያዩ የልብ ችግሮች ሊያመሩ ይችላሉ፡፡ ይሁን እንጂ የስፔን ተመራማሪዎች በወይራ ዘይት ወይም በሞኖሳካራይድ ቅባት የበለፀጉ ምግቦች ያረጁ ሰዎችን የደም ቅዳ ስራዎችን እንደሚያሻሽሉ በቅርብ ጥናታቸው አግኝተዋል፡፡

የወይራ ዘይት የአጥንት መሳሳትን ይዋጋል

የአጥንት መሳሳት የአጥንት ጡንቻ አወቃቀር በቀላሉ ሊጎዳ የሚችል እየሆነ እንዲመጣ የሚያደርገው በአጥንት ክብደት መቀነስ  የሚገለፅ በሽታ ነው፡፡ ይህ የመሠንጠቅ ሁኔታውን በመጨመር ትናንሽ ምቶች በሽተኛውን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲሰቃይ ያደርጋል፡፡

የወይራ ዘይት ተጨማሪ ምግብነት በአጥንት ውፍረት ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ እንዳለው ታውቋል፡፡ የወይራ ዘይት ከማረጥ በኋላ ላለው የአጥንት መሳሳት ላይ ቀጣይነት ላለው ውጊያ ብቸኛ መፍትሔ ብቻ ሳይሆን ለበሽታውም የወደፊቱም ተስፋ ሰጪ ዕጩ ማከሚያ እንደሚሆን ሳይንቲስቶች አረጋግጠዋል፡፡

የወይራ ዘይት ከድብርት ሊጠብቅ ይችላል

የወይራ ዘይት እና የሜዲትራኒያን ምግብ ብዙ የጤና ጠቀሜታዎች እንዳሉት በተለምዶ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን ስሜታዊ የጤና ጠቀሜታዎቹስ?

ከናቫራ እና ላስፓልማስ ደግራን ካናሪያ ዩኒቨርስቲ እንደ ስፔን ተመራማሪዎች፣ በወይራ ዘይት የበለፀጉ ምግቦች ከአዕምሮ ህመም ሊጠብቁ ይችላሉ፡፡

በቅርቡ ተመራማሪዎች እንዳገኙት የወይራ ዘይትን እና በቅባታማ አሳዎች እና የአትክልት ዘይቶች ውስጥ የሚገኙትን ፖሊአንሳቹሬትድ ቅባቶችን በብዛት መውሰድ በድብርት የመያዝ አደጋን ከመቀነስ ጋር ይያያዛል፡፡

ግኝቶቹ እንደጠቆሙት የልብ በሽታ እና ድብርት ከሰው አመጋገብ ጋር የተገናኘ አንዳንድ የጋራ ዘዴዎች ሊጋሩ ይችላሉ፡፡

የወይራ ዘይት የቆዳ ካንሰርን ለመከላከል ይረዳል

በሌላ የቅርብ ጥናት እንደተገኘው የወይራ ዘይት ከሌላ የሜዲትራኒያን ምግብ ንጥረ ነገር ጋር ነቀርሳን ለመከላከል አስተዋፅኦ ሊያደርግ ይችላል፡፡ ተመራማሪዎች እንዳገኙት በፀረ ኦክስጅን የበለፀገውን የወይራ ዘይት በመጠቀም በጣም አደገኛ አይነት የሆነውን የቆዳ ካንሰር ሊቀንስ ይችላል፡፡

የፀሀይ ቃጠሎን ለመከላከል እና ቆዳን ከፀሀይ አልትራ ቫዮሌንት ኤ እና አልትራ ቫዮሌንት ቢ ጨረሮች አስከፊ ጉዳቶች ለመሸፈን የፀሀይ መከላከያን መጠቀም ምርጡ ዘዴ ነው፡፡ ነገር ግን “ወደ ግሪክ መሄድ” እና የወይራ ዘይት እና ሌላ የሜዲትራኒያን ምግብ ማባያዎች የፀሀይ ኦክሲዳይዚንግ ጉዳቶችን ለመመከት ሊረዳ ይችላል፡፡

በሜዲትራኒያን ሀገሮች ከ100,000 ኗሪዎች ውስጥ የቆዳ ካንሰር የተገኘባቸው ሦስት ብቻ ናቸው፡፡ በተለይም የአካባቢውን ሞቃታማ የአየር ፀባይ ከግምት ስናስገባ ቁጥሩ በጣም ትንሽ ነው፡፡ በአውስትራሊያ  ከእያንዳንዱ 100,000 ኗሪዎች ውስጥ ቁጥሩ 50 ነው፡፡


ethiopian-food-blog-olive-oil-recipes-health-diet-amharic-cooking

The health benefits of olive oil are unrivaled, and research reveals more benefits nearly every day. In fact, we are only just beginning to understand the countless ways olive oil can improve our health, and our lives. Olive oil is the cornerstone of the Mediterranean diet — an essential nutritional mainstay for the world’s longest-living cultures.

The phytonutrient in olive oil, oleocanthal, mimics the effect of ibuprofen in reducing inflammation, which can decrease the risk of breast cancer and its recurrence. Squalene and lignans are among the other olive oil components being studied for their possible effects on cancer.

Olive Oil Diet Reduces Risk of Type 2 Diabetes

Traditionally a low-fat diet has been prescribed to prevent various diseases such as heart disease and diabetes. While studies have shown that high fat diets may increase the risk of certain diseases such as cancer and diabetes, it appears that it is the type of fat that counts rather than the amount of fat. We now know that a diet rich in monounsaturated fats such as the ones found in olive oil, nuts and seeds actually protects from many of these chronic diseases.

A study published in the scientific journal Diabetes Care showed that a Mediterranean style diet rich in olive oil reduced the risk of type II diabetes by almost 50 percent compared to a low fat diet. Type II diabetes is the most common and preventable form of diabetes.

Olive Oil Might Help Prevent Strokes

Older individuals who consume olive oil daily may be able to protect themselves from a stroke, according to a new study from France published in the online issue of Neurology.

Researchers gathered information from the medical records of 7,625 individuals over the age of 65 from three cities in France: Bordeaux, Dijon and Montpellier. None of the participants had a history of stroke. They then categorized the individuals into three groups based on their olive oil consumption. The researchers noted that the participants used mostly extra virgin olive oil, as that is what is usually available in France.

After 5 years there were 148 strokes. The results showed that the “intensive” users of olive oil, those that used for both cooking and dressings had a 41 percent lower risk of stroke compared to those that did not use olive oil at all. These results were noted even after considering weight, diet, physical activity and other risk factors.

Olive Oil Keeps the Heart Young

A diet rich in olive oil may actually be able to slow down the aging of the heart.

It is a known fact that as we grow older the heart also goes through a normal aging process. The arteries may not function as well as they did and this can lead to a number of health problems. However, in a recent study, Spanish researchers discovered that a diet rich in olive oil or other monounsaturated fats could improve the arterial function of elderly individuals.

Olive Oil Fights Osteoporosis

Osteoporosis is a disease characterized by a decrease in bone mass, which in turn causes the architecture of bone tissue to become fragile. This can then increase the possibly of fractures, making even the slightest of knocks potentially fatal for sufferers.

Olive oil supplementation was found to positively affect the thickness of bones. Olive oil will not be the only solution in the continuing fight against postmenopausal osteoporosis, hoever scientists have concluded that it is a very promising candidate for future treatments of the disease.

Olive Oil May Protect from Depression

It is common knowledge that olive oil and the Mediterranean diet confer a multitude of health benefits. But what about emotional health benefits?

According to Spanish researchers from the University of Navarra and Las Palmas de Gran Canaria, a diet rich in olive oil can protect from mental illness.

Researchers recently discovered that a higher intake of olive oil and polyunsaturated fats found in fatty fish and vegetable oils was associated with a lower risk of depression.

The findings suggested that cardiovascular disease and depression may share some common mechanisms related to one’s diet.

Olive Oil Found to Help Prevent Skin Cancer

Another recent study found that olive oil, along with other components of a Mediterranean diet, may contribute to the prevention of malignant melanoma. The most dangerous type of skin cancer may be slowed down by consumption of olive oil, which is rich in antioxidants, the researchers found.

The use of sunscreen remains the best way to prevent sunburn and shield the skin from the harmful effects of the sun’s UVA and UVB rays. However, “Going Greek” and consuming olive oil and other Mediterranean food staples, could help counter the oxidizing effect of the sun.

Only three in every 100,000 residents of countries in the Mediterranean develop any form of skin cancer. The figure is low, especially when considering the warm climate in the region. In Australia, the figure is 50 in every 100,000 residents.

Recent Posts