The Pure Natural Magic of Aloe Vera / የንፁህ ተፈጥሯዊ እሬት ተዓምር

The Pure Natural Magic of Aloe Vera / የንፁህ ተፈጥሯዊ እሬት ተዓምር

የተለያዩ የተፈጥሮ የውበት ምርቶችን ይመልከቱ እና በአብዛኛው ምርቶች ውስጥ አንድ የተለመደ ግብዓት ሲያዩ ይደነቃሉ፡፡ ግብዓቱ እሬት ሲሆን በአብዛኛው የዓለም ክፍል ውስጥ በጓሮ አትክልቶች ውስጥ የተለመደ ተክል ነው፡፡

እሬት በጣም ብዙ የህምና ባህርያቶች ያሉት ሲሆን የጥንት ግብፃውያን ህያው ተክል ብለው ይጠሩታል፡፡

ዛሬም እንኳን ቢሆን በውበት ኢንዱስትሪ ውስጥ በጣም በሰፊው እና በተስፋ ሁኔታ እሬት ጥቅም ላይ ይውላል፡፡

በእሬት ቅጠል ውስጥ ያለው ጄል ለቆዳ እና ለፀጉር ጥሩ በሆኑት ንጥረ ነገሮች፣ ማዕድናት፣ እና ቫይታሚኖች የተሞላ ነው፡፡ ይህን ተክል በውጭም በውስጥም ለመጠቀም ደህንነቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 1. ያለ ዕድሜ የማርጀት ምልክቶችን ይከላከላል

የማርጀት ምልክቶች እንደ መሸብሸብ፣ ቀጭን መስመሮች እና የቆዳ መርገብ ከዕድሜ ጋር የሚከሰቱ ናቸው፡፡ ነገር ግን በሆነ ወቅት እነዚህ ምልክቶች ቀድመው ይከሰታሉ፡፡ እሬቶች በከፍተኛ የፀረ ኦክሲዳንት ይዘቶቹ ምክንያት በውበት መጠበቂያ መመርያዎች ውስጥ በማካተት ያለዕድሜ የማርጀት ምልክቶችን መከላከል ይቻላል፡፡

የእሬት ጄል በጥልቅ ወደ ቆዳ ውስጥ በመዝለቅ እርጥበቱን ይጠብቃል፡፡ እንደ ቫይታሚን ኤ፣ ቢ፣ ሲ እና ኢ የሆኑ ንጥረ ነገሮች የተሟላ ምንጭ ስለሆነ ቆዳዎን ይመግባል፡፡ ጄሉ የቆዳ ድጋሚ ማደግን የሚያነቃቃውን ፖሊሳካራይድን የያዘ ነው፡፡

በማረጋገጫ ላይ የተመረኮዘ አጋዥ እና አማራጭ ህክምና ላይ የታተሙ የ2013 ጥናት እንደገለፀው ያለ ዕድሜ የማርጀት ምልክቶችን ለመዋጋት አስፈላጊ የሆኑት በተለያዩ ይዘቶች ውስጥ ያሉት የትኩስ እሬት ጄል የቆዳን የመሸብሸብ እና የእርጥበት ባህርያቶችን ሲያሻሽል ታይቷል፡፡

ጥናቱ የቅጠል ተክሉን ፀረ ኦክሲደንት፣ ፀረ የቆዳ መቆጣት እና አልትራ ቫዮሌትን የመጠበቅ ባህርያቶች ላይ በጋራ ለሚያመጡት ውጤት ብርሀን የሰጠ ነው፡፡

ቆዳዎ ሳያረጅ እንዲቆይ ሳምንቱን መሰረት በማድረግ መቀንጠስ አስፈላጊ ነው፡፡

የተቀነጠሰ መዋቢያ ለመስራት፡

 1. 1 የሻይ ማንኪያ በቅርብ የተቆረጠ የእሬት ጄል ይደባልቁ
 2. 1 የሻይ ማንኪያ የተፈጨ አጃ እና ½ የሻይ ማንኪያ የወይራ ዘይት በውስጡ ይደባልቁ
 3. ይህንን ውህድ በፊትዎ እና በአንገትዎ አካባቢ ያድርጉ
 4. ለ 30 ደቂቃዎች እንዲቀመጥ ይፍቀዱ
 5. ከዚያም በእርጥብ እጆችዎ በቀስታ ውህዱን ይቀቡት
 6. በመጨረሻም ፊትዎን እና አንገትዎን በቀዝቃዛ ውሀ ይጠቡት
 7. ይህንን መዋቢያ በሳምንት አንድ ጊዜ ይጠቀሙ
 1. ቆዳዎ እንደረጠበ ይቆያል

ታላቅ የተፈጥሮ እርጥበት የሚፈጥረው እሬት ቆዳን በጥሩ ሁኔታ እንደራሰ የሚጠብቁ እና መሳሳብን የሚያሻሽል ነው፡፡ በጥሩ ሁኔታ የራሰ እና የረጠበ ቆዳ ጤናማ እና ለስላሳ ይሆናል፡፡

ከላይ ሲደረጉ በቀላሉ ወደ ቆዳ ዘልቀው የሚገቡ ሲሆኑ የቆዳን የፒ ኤች መጠን ለመመለስ ይረዳል፡፡ በተጨማሪም እሬት ቅባታማ ሆነው እንዲታዩ አያደርግም፤ ይህም ቅባታማ ቆዳ ላላቸው ጥሩ አማራጭ ናቸው፡፡

በቆዳ ምርምር እና ቴክኖሎጂ ውስጥ በ2006 በታተመው ጥናት እንደተገለፀው ቀዝቅዞ ከደረቀው እሬት የሚገኘው በማርጠብ ዘዴዎች በኩል የቆዳን የማራስ ሁኔታ ለማሻሻል ውጤታማ ነው፡፡

በውጤቱም በመዋቢያ ምርቶች ውስጥ የደረቀ ቆዳን ለማከም ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል፡፡

 1. የእሬት ቅጠልን የላይኛውን ሽፋን በስለታማ ቢላ ይላጡ እና በቀስታ ጄሉን ያውጡት፡፡
 2. በፊትዎ፣ በአንገትዎ እና ሌሎች የሰውነትዎ ክፍሎች ላይ ይሹት
 3. ከመተኛትዎ በፊት በየቀኑ ያድርጉ

3. ብጉርን ይቀንሳል

እሬት የተፈጥሮ ፀረ ባክቴሪያን የያዘ ሲሆን ብጉር እንዲከሰት የሚያደርገውን ባክቴሪያን ለመዋጋት ይረዳል፡፡ አዲስ ህዋሳትም እንዲያድጉ ያነቃቃል፡፡

በተጨማሪም የማዳን እና የቆዳ መቆጣት የመከላከል ባህርያት ያሉት ሲሆን ቆዳ በፍጥነት እንዲድን እና የቆዳ መቆጣትን እንዲቀንስ ይረዳል፡፡

በቆዳ ህክምና መፅሀፍ ውስጥ በታተመው የ2014 ጥናት ላይ እንደተገኘው ከጥቂት እስከ መካከለኛ ተራ የሆነ ብጉርን ለማከም በጣም ውጤታማ ነው፡፡

 • አዲስ የተቀጠፈ የእሬት ጄልን በተጎዳው ቦታ ላይ በቀጥታ በቀን ለጥቂት ጊዜ ያድርጉ፡፡
 • የበረዶ ማስቀመጫ ዝርግ ሰሀንን በእሬት ጄል ይሙሉበት እና ያቀዝቅዙት፡ የቆዳውን መቆጣት ለማርገብ የቀዘቀዘውን ሰሀን በብጉሩ ላይ ይሹት፡፡ በቀን 2 ወይም 3 ጊዜ ይድገሙት፡፡
 • በአማራጭነት 1 የሻይ ማንኪያ የእሬት ጄል ከ1/2 የሻይ ማንኪያ ማር እና የሎሚ ጭማቂ ያደባልቁ፡፡ በብጉር በተጠቁት ቦታዎች ያድርጉ፡፡ ለ15 ደቂቃዎች እንዲቀመጥ ይፍቀዱ እና ከዚያም በውሀ ይጠቡት፡፡ ይህንን በቀን ሁለት ጊዜ ያድርጉ፡፡

ብጉርን ከማከም ጎን ለጎን ይህ የተፈጥሮ ቅጠል እንደ ፕሶሪያሲስ እና ችፌ የሚባሉት አደገኛ የቆዳ ችግሮችን በብቃት ለመፈወስ ይጠቅማል፡፡

 1. በፀሀይ የተቃጠለን ያክማል

የእሬት የማቀዝቀዝ እና ቆዳን ከመቆጣት የመከላከል ባህርያቶች የቆዳን የፀሀይ ቃጠሎን ለማከም ይረዳል፡፡ በተጨማሪም ጄሉ የቆዳን የፀሀይ ቃጠሎን ለመፈወስ አስፈላጊ የሆነውን የቆዳ የእርጥበት ደረጃ ለማቆየት ይረዳል፡፡ እሬት የማይፈለጉ በፀሀይ የጠቆሩትን ለማጥፋት ውጤታማ ነው፡፡

በቆዳ ፋርማኪዮሎጂ እና ፊዚዮሎጂ ውስጥ የታተመው የ2008 ጥናት እንደሚያስረዳው የእሬት ጄል አንዳንድ ፀረ የቆዳ መቆጣትን ውጤቶችን የሚያሳይ ሲሆን የቆዳ የመቆጣት ሁኔታዎች እንደ በአልትራ ቫዮሌንት አማካይነት የሚመጣውን የቆዳ መቅላትን ከላይ በማድረግ ለማከም ይጠቅማል፡፡

 • አዲስ የተቀጠፈውን የእሬት ጄል በፀሀይ በተቃጠለው ቦታ ላይ በቀጥታ በማድረግ በራሱ እንዲደርቅ መፍቀድ፡፡ ማጠብ አያስፈልግም፡፡ ጄሉ በፍጥነት በቆዳው ውስጥ የሚዘልቅና ቅባታማ ስሜትም የለውም፡፡
 • በአማራጭነት 2 የሻይ ማንኪያ የእሬት ጄል እና ግማሽ የሎሚ ጭማቂ ይደባልቁ፡፡ በክብ እንቅስቃሴዎች በፀሀይ በተቃጠለ ቦታ ላይ ይሹት፡፡ ለ 15 ደቂቃዎች ይተውት እና በቀዝቃዛ ውሀ ይጠቡት፡፡
 1. የተዘረጉ ምልክቶችን ይቀንሳል

አስቀያሚዎቹ የተዘረጉ ምልክቶች የቆዳዎን ውበት ሊሰርቁ ይችላሉ፡፡ ምንም እንኳን የተዘረጉ መስመሮችን ሙሉ ለሙሉ ለማጥፋት ቢከብድም የመታየታቸውን ሁኔታ በትልቁ በእሬት መቀነስ ይችላሉ፡፡ እሬት የመሸብሸብ ሁኔታን ለመመለስ እና የቆዳን ጉዳት ሊጠግን ይችላል፡፡

 1. እኩል መጠን ያላቸውን የእሬት ጄል እና የፅጌረዳ ውሀን አንድ ላይ ይደባልቁ፡፡
 2. በተዘረጉ ምልክቶች ላይ ያድርጉ እና ለተወሰኑ ደቂቃዎች በክብ ቅርፅ እንቅስቃሴ በቀስታ ይሹት፡፡
 3. ለ15-20 ደቂቃዎች ይጠብቁ፡፡
 4. በመጨረሻም በቀዝቃዛ ውሀ ይታጠቡ፡፡
 5. ይህንን በቀን ሁለት ጊዜ ያድርጉ፡፡

6. እንደ የተፈጥሮ የገፅ ቅቦች ማስለቀቂያነት ያገለግላል

በገበያ ላይ ያሉ የገፅ ቅቦች ማስለቀቂያ ቆዳዎን ሊጎዱ የሚችሉ በጎጂ ኬሚካሎች የተሞሉ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በምትካቸው እንደ የተፈጥሮ የገፅ ቅቦች ማስለቀቂያነት እሬትን መጠቀም ይችላሉ፡፡

የጄሉ የማጣበቅ ተፈጥሮ የገፅ ቅቦች ቆሻሻዎች በቀላሉ በመሰብሰብ እና ቆዳዎን ንፁህ ሆኖ እንዲቆይ ሊያደርግ ይችላል፡፡ ለቆዳ የሚያንፀባርቅ ብርሀን ይሰጣል፡፡

 1. ንፁህ የእሬት ጄል ጠብታዎችን በጥጥ በተሰራ መጥረጊያ ላይ ያስቀምጡ
 2. የገፅ ቅቦችን ለማስለቀቅ በጥጥ የተሰራ መጥረጊያውን ፊትዎን በሙሉ ይጥረጉበት፡፡
 3. በመጨረሻም ፊትዎን በውሀ ይታጠቡ፣ በቀስታ ያድርቁ እና ቀላል ማርጠቢያ ያድርጉበት፡፡


አሎ ቬራ Aloe Vera – Skin Care የቆዳ እንክብካቤ – ፊትህንም ታጠብ; – face wash

Have a look at different natural beauty products and you will be amazed to see one common ingredient in several of the products. The ingredient is aloe vera, which is a common plant in home gardens in many parts of the world.

Aloe vera has so many medicinal properties that ancient Egyptians called it the “plant of immortality.”

Even today, the use of aloe vera is very wide and extensive in the beauty industry.

The gel inside aloe vera leaves is loaded with several nutrients, minerals and vitamins that are good for the skin and hair. This herb is safe to use externally and internally.

1. Prevents Premature Aging Signs

Aging signs like wrinkles, fine lines and sagging skin are bound to appear with age, but at times these signs appear earlier. You can prevent premature aging signs by including aloe vera in your beauty regimen due to its high antioxidant content.

Aloe vera gel penetrates keep into the skin to keep it moisturized. Being a rich sourch of nutrients like vitamins A, B, C and E, it nourishes your skin. Also, the gel contains polysaccharides that stimulate skin regeneration.

A 2013 study published in Evidence Based Complementary and Alternative Medicine reports that fresh aloe vera gel in varied concentrations showed improvement of the skin’s visco elastic and hydration properties, which are important for fighting premature aging signs. The study sheds light on the synergistic antioxidant, anti-inflammatory and ultraviolet (UV) protective properties of the herbal plant.

To keep your skin young, it is important to exfoliate on a weekly basis. To make an exfoliating mask:

1.    Blend 1 teaspoon of fresh aloe vera gel.

2.    Mix 1 teaspoon of ground oatmeal and ½ teaspoon of olive oil in it.

3.    Apply this mixture on your face and neck area.

4.    Allow it to sit for 30 minutes.

5.    Then, with wet hands, gently scrub off the paste.

6.    Finally, rinse your face and neck with cold water.

7.    Use this mask once a week.

2. Keeps Skin Moisturized

Being a great natural moisturizer, aloe vera keeps the skin well hydrated and enhances its elasticity. Well-hydrated and moisturized skin looks healthy and smooth.

It easily penetrates into the skin when applied topically and also helps restore the pH balance of the skin. Plus, aloe vera does not give a greasy look, making it a good option for those who have oily skin.

A 2006 study published in Skin Research and Technology reports that freeze-dried aloe vera extract is effective at improving skin hydration, possibly through a humectant mechanism. Consequently, it may be used in cosmetic products for the treatment of dry skin.

1.    Peel off the outer layer of an aloe vera leaf with a sharp knife and gently scoop out the gel.

2.    Massage the gel on your face, neck and other body parts.

3.    Do it daily before going to bed.

3. Reduces Acne

Aloe vera is a natural antibacterial agent that helps fight the bacteria responsible for acne. It also stimulates the growth of new cells.

Plus, it has healing and anti-inflammatory properties that help the skin heal quickly and reduces skin inflammation.

A 2014 study published in the Journal of Dermatological Treatment found aloe vera to be very effective for the treatment of mild to moderate acne vulgaris.

•    Apply fresh aloe vera gel directly on the affected areas a few times a day.

•    Fill an ice cube tray with aloe vera gel and freeze it. Rub a frozen cube on your acne to soothe the inflammation. Repeat 2 or 3 times a day.

•    Alternatively, mix 1 teaspoon of aloe vera gel with ½ teaspoon each of honey and lemon juice. Apply it on the acne-affected area. Allow it to sit for about 15 minutes, then rinse it off with water. Do this twice daily.

Along with treating acne, this natural herb is used to effectively heal chronic skin problems, such as psoriasis and eczema.

4. Treats Sunburns

The soothing and anti-inflammatory properties of aloe vera help treat skin sunburn. Plus, the gel helps retain the skin’s moisture level, which is important for healing sunburned skin.

Aloe vera is even effective at getting rid of an unwanted suntan.

A 2008 study published in Skin Pharmacology and Physiology notes that aloe vera gel displayed some anti-inflammatory effects and is useful in the topical treatment of inflammatory skin conditions, such as UV-induced erythema.

•    Apply freshly extracted aloe vera gel directly on the sunburned area and allow it to dry on its own. There is no need to rinse it off. The gel quickly penetrates into the skin and does not have a greasy feel.

•    Alternatively, mix 2 tablespoons of aloe vera gel and the juice of half a lemon. Massage it on the sunburned skin in circular motions. Leave it on for about 15 minutes, then rinse it off with cold water.

5. Minimizes Stretch Marks

Ugly stretch marks can steal away the beauty of your skin. Though it is difficult to get rid of stretch marks completely, you can minimize their visibility to a great extent with aloe vera.

Aloe vera can help restore the skin’s elasticity and repair skin damage.

1.    Mix together equal amounts of aloe vera gel and rose water.

2.    Apply it on the stretch marks and massage gently in circular motions for a couple of minutes.

3.    Keep it on for 15 to 20 minutes.

4.    Finally, rinse it off with cool water.

5.    Do this twice daily.

6. Works as a Natural Makeup Remover

Commercial makeup removers can be full of harmful chemicals that can be damaging to your skin. Instead, you can use aloe vera as a natural makeup remover.

The slippery nature of the gel can easily collect makeup residue and leave your skin clean. It even gives the skin a radiant glow.

1.    Put a dollop of pure aloe vera gel onto a cotton ball.

2.    Swipe the cotton ball all around your face to remove your makeup.

3.    Finally, rinse your face with water, pat dry and apply a light moisturizer.

Recent Posts